Get Mystery Box with random crypto!

አድማስ ሬድዮ- Admas Radio

የቴሌግራም ቻናል አርማ admasradio — አድማስ ሬድዮ- Admas Radio
የቴሌግራም ቻናል አርማ admasradio — አድማስ ሬድዮ- Admas Radio
የሰርጥ አድራሻ: @admasradio
ምድቦች: ሙዚቃ
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 1.80K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ከሰሜን አሜሪካዋ ደማቅ ከተማ አትላንታ እየተዘጋጀ በመላው ዓለም የሚተላለፈው
የ አድማስ ሬድዬ የቴሌግራም ቻናል ነው።
www.admasradio.info
melethio23@gmail.com
mike@admasradio.info

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2021-02-02 11:00:02
ከመተከል የሸሹ ታጣቂዎች በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ንጹሐንን እየገደሉ መሆኑ ተጠቆመ።

በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ከመተከል ሸሽተው የገቡ ታጣቂዎች በየእለቱ በንጹሐን ዜጎች ላይ የግድያና የንብረት ዘረፋ ተግባር እየፈጸሙ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች መግለጻቸወን አዲስ ማለዳ አስነብቧል።

ከጥር 14/2013 እስከ ጥር 17/2013 ድረስ ባሉት ቀናት ብቻ 10 ሰዎችን እንደገደሉ ነው የገለጸው። እንዲሁም ጥር 15/2013 በአመሩ ወረዳ ጉራ ተብሎ በሚጠራ ቀበሌ አምስት ንጹሐን በታጣቂዎች ተገድለዋል ተብሏል።

በአከባቢው ኗሪ የሆኑ ለደህንነታቸው ስለሚሰጉ ስማቸው እንዳይጠቀስ ያሳሰቡ ግለሰብ “የማኅረሰቡን ጭንቀት የሚረዳ ሕግ ያለ አይመስልም በፈጣሪ ጠባቂነት ነው የምንኖረው” ሲሉ መንግሥት ለችግሩ መፍትሔ ከመስጠት ይልቅ ዝምታ መምረጡን ገልጸዋል።

ጫጮ ጫካ ሰፍሯል የተባለው የታጣቂ ኃይል ለአከባቢው ማኅበረሰብ ስጋት እንደሆነ የአካባቢው ኗሪዎች ለመንግሥት አካላት ጥያቄ ማቅረባቸውን ተናግረዋል።

ነገር ግን የመንግሥት አካላትና በአካባቢው በጸጥታ ሥራ ላይ የተሰማሩ የኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይል ጉዳዩ ከአቅማችን በላይ ስለሆነ ምንም ልናደርግ አንችልም የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው ነሪዎቹ አስረድተዋል።

@admasradio
6 views08:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-02 11:00:02
ብርጋዴር ጄነራል መአሾ ሀጎስ ስዩም የተመድ የደቡብ ሱዳን ሰላም ማስከበር ተልእኮ አዛዥ ሆኑ!

በኢትዮጵያ አየር ኃይል ውስጥ ለ25 ዓመታት ያገለገሉት ብርጋዴር ጄነራል መአሾ ሀጎስ ስዩም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የደቡብ ሱዳን ሰላም ማስከበር ተልእኮ አዛዥ ሆነው ተሰየሙ።

ብርጋዴየር ጄነራል መአሾ በተመድ የላይቤሪያ እንዲሁም ዳርፉር ሰላም አስከባሪ ኃይል ውስጥ ማገልገላቸውም ታውቋል።

አዲሱን ሹመት ከጥር 04 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ እንደተሰጣቸውም በተመድ መረጃ ላይ ተገልጿል።

(Walta)
@admasradio
7 views08:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-02 11:00:02
ደቡብ አፍሪካ በአልኮል መጠጦች ላይ የጣለችውን ክልከላ አንስታለች

የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ በኮሮና ቫይረስ ላይ የተቀመጡ አንዳንድ ክልከላዎችን ማንሳታቸው ተደምጧል፡፡ ከነዚሁ መካከል ደግሞ የአልኮል መጠጦች ላይ የተጣለው የሽያጭ ክልከላ ይገኝበታል፡፡

ባህር ዳርቻዎች እንደሚከፈቱና በቤተ እምነት ስፍራዎች ላይ የተጣለው የመሰባሰብ እግድ እንደሚላላም ተገልጿል፡፡

ፕሬዝዳንት ራማፎሳ ይህንን ያስተላለፉት የመጀመሪያ ዙር ክትባት ወደ ሀገሪቱ መግባቱን ተከትሎ ነው፡፡ ይኸውም አንድ ሚሊዮን አስትራዜኔካ ዶዝ ሲሆን ለሃገሬው ዜጎች እፎይታን ይሰጣቸዋል ተብሏል፡፡

ደቡብ አፍሪካ በአህጉሪቱ ከፍተኛው የኮቪድ ተጠቂ እና ሞት ያስመዘገበች ሀገር ናት፡፡ እንደ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ ከወረርሽኙ ጅማሮ 1.4 ሚሊዮን ዜጎቿ በቫይረሱ የተጠቁ ሲሆን ፤ 44,164 ዜጎቿን ደግሞ አሳጥቷታል፡፡

በርካታ ሀገራት ከኮሮና ቫይረስ ወዲህ የተከሰተው አዲሱ ቫይረስ ጅማሮው ከዛው ነው በሚል የጉዞ ማዕቀብን ጥለውባት ይገኛል፡፡

(ብስራትራዲዮ)
@admasradio
8 views08:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-02 11:00:01
አሜሪካ በማይናማር ላይ ማዕቀብ ልትጥል ስለመሆኑ ተሰምቷል

በማይናማር ወታደራዊ ሃይሉ ፕሬዝዳንት ኦንግ ሳንግ ሱ ኪን ከስልጣን በማስወገድ መንበሩን መቆጣጠሩን በትናንትናው እለት መዘገባችን ይታወሳል።

ይህንኑ ተከትሎ ጉዳዩን በርካቶች እየተቃወሙት ሲሆን ፣ አሜሪካም ፕሬዝዳንት ኦንግ ሳንግ ሱ ኪን ከእስር እንድፈታ ትዕዛዝ አስተላልፋለች፡፡ ይህ ካልሆነ ሀገሪቱን በማዕቀብ እንደምትቀጣትም ነው የዛተችው፡፡

ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ‹‹ሃይል የሰዎችን ፍላጎት ሊያሳካ አይችልም ፣ የምርጫውን ውጤትም መፋቅ አይችልም›› ብለዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅቱ እንዲሁም ዩናይትድ ኪንግደም መፈንቅለ መንግስቱ ተቃውመውታል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ ባለፉት ዓመታት የቀድሞዋ ቡርማ ያሁኗ ማይናማር ዲሞክራሲን እየተገበረች ትገኛለች በሚል ከማዕቀብ መዝገብ ፍቃት እንደነበርም ይታወሳል፡፡

ጆ ባይደን ‹‹ይህ ጉዳይ ይታሰብበታል ዩናይትድ ስቴትስ በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ቢሆን ከዲሞክራሲ ጎን ነው የምትሰለፈው›› ብለዋል፡፡

በሀገሪቱ የአስአቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለአንድ ዓመት የታወጀ ሲሆን ፤ ወታደራዊ ሃይሉ ስልጣኑን በምርጫ መጭበርበር ለተሸነፉት ሚን አውንግ ህላይንግ ይተላለፋል ብለዋል፡፡

በሀገሪቱ የተካሄደውን ምርጫ ተከትሎ ህዝብን በሚያስተዳድረው መንግስት እና በወታደራዊ ሃይሉ መካከል ውጥረት ነግሶ ቆይቷል፡፡

የሰላም ኖቤል ተሸላሚዋ ፕሬዝዳንት ኦንግ ሳንግ ሱ ኪን ለ 15 ዓመታት በእርስ መቆየቷ የሚታወስ ሲሆን ፣ የዲሞክራቲክ ለውጥ እስከመጣበት 2011 ዓመት ድረስ ሀገሪቱ በወታደራዊ ሃይሉ ስትመራ ቆይታለች፡፡

(ብስራት ራዲዮ)
@admasradio
9 views08:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-02 11:00:01
በአሜሪካ ለሁለት ተከታታይ ቀናት በረዶ የቀላቀለ ከባድ ዝናብ ጣለ!

በሀገሪቱ ምስራቃዊ ባህር ዳርቻ ለሁለት ተከታታይ ቀናት በረዶ የቀላቀለ ከባድ ዝናብ ጥሏል።

በኒውዮርክ ፣ ኒውጀርሲና ፔንሲልቫኒያ መጣል የጀመረው ይህ ከባድ ዝናብ በረራዎችን እያስተጓጐለ ሲሆን ፤ የኮቪድ-19 ክትባት የሚሰጡ ስፍራዎችም እንዲዘጉ አድርጓል።

የኒውዮርክ ከተማ ከንቲባው ቢል ዴ ብላሲዮ አስገዳጅ እስካልሆነ ድረስ በሚል የጉዞ ክልከላዎችን አስተላልፈዋል።

ሁኔታው ከዚህ የከፋ እንዳይሆን መስጋታቸውንም ተናግረዋል።

የኒውጀርሲ አስተዳዳሪ ፊሊፕ መርፊ በተመሳሳይ መንገዶች እንዲዘጉ አድርገዋል።

በጉዳዩ ዙሪያ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ከአማካሪዎቻቸው ጋር ስለመምከራቸውም የቢቢሲ ዘገባ ያሳያል።

(ብስራት ራዲዮ)
@admasradio
10 views08:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-02 11:00:01
በአሰላ ከተማ ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የድጋፍ ሰልፍ እየተከናወነ ይገኛል!!

"ዶክተር አብይን ለመደገፍ የምንሳሳለት ነፍስም ሆነ ሀብት የለም!" የሚል መፈክር በሰልፉ ላይ ታይቷል።

@admasradio
11 views08:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-02 10:42:46
እንዴት አደራችሁልን

መልካም ቀን መልካም ግዜ በያላችሁበት እንዲሆን ተመኘንላችሁ

እንደተለመደው አዳዲስና ታማኝ የሆኑ መረጃዎቻችንን ወደናንተ ማድረስ ጀመርን ከኛ ጋር ቆዩ

@admasradio
28 views07:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-01 21:33:17
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን በተለያዩ ወረዳዎች በነበረው የጸጥታ ችግር ተፈናቅለው በተለያዩ መጠለያ ጣቢያ ውስጥ ያሉትን ዜጎች መልሶ ለማቋቋምና ለመደገፍ  የሚያስችል ከ14 ሚሊዩን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን  በክልሉ የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመደገፍ  የተቋቋመው የገቢ አሰባሰብ አብይ ኮሚቴ አስታውቋል።

የቤኒንሻጉል ጉሙዝ ክልል የግብርና እና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ እንዳስታወቀው ገቢው የተሰበሰበው በክልል ደረጃ ካሉት ተቋማት እንዲሁም ከዞንና ወረዳ  ደረጃ ካሉት መስሪያ ቤቶች ነው።ከዚህ ቀድም ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለክልሉ ተፈናቃዩች የተላከው ድጋፍ  በአሶሳ ዞን ሆሞሻ በተባለ  ወረዳ ተራግፎ የነበረና በቶሎ ተፈናቃዩች  አልደረሰም የሚል ቅሬታም ሲቀርብ የቆየ ሲሆን ከትናንት ጅምሮ ወደ ስፋራ ማጓጓዝ መጀመሩንም ገልጿል።

(ዶቼቬሌ DW)
@admasradio
176 viewsedited  18:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-01 21:32:33
ሚኒስቴሩ በትግራይ ክልል ትምህርት ለማስጀምር ቅድመ ዝግጅቶች እያደረገ መሆኑን ገለጸ

የትምህርት ሚኒስቴር በትግራይ ክልል ትምህርት ለማስጀምር የሚያስፈልጉ ቅድመ ዝግጅቶች እያደረገ መሆኑን ገለጸ፡፡

በትግራይ ክልል በነበረው ህግ የማስከበር ተግባር በጸረ-ሰላም ሃይሎች የወደሙ ትምህርት ቤቶችን መልሶ የመገንባት ስራ እየተሰራ መሆኑንም አስታውቋል፡፡

በሚኒስቴሩ የትምህርት መሻሻል ዳይሬክተር ጀነራል ዮሐንስ ወጋሶ በተለይ ለዋልታ እንደገለጹት፣ የትመህርት ሚኒስቴር ትምህርት ለማስጀመር የሚያስችሉ ቅድመ ዝግጅቶችን እያከናወነ ይገኛል፡፡

ከክልሉ አስተዳደር ጋር በመሆን በተሰራው ውጤታማ ስራ በቅርቡ ትምህርት የሚጀመርባቸው አካባቢዎች እንደሚኖሩም አቶ ዮሐንስ ጠቁመዋል፡፡

በትግራይ ክልል የሚገኙ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችንም ለመፈተን የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ስራም እየተሰራ ስለመሆኑን ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይም በቤኒሻንጉል ክልል በመተከል ዞን በተከሰተው አለመረጋጋት ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው የተነሱ ተማሪዎች መኖራቸውን ያስታወሱት አቶ ዮሐንስ፣ ከጸጥታ አካላት ጋር ትምህርት ማስጀመር የሚያስችሉ ስራዎች በመሰራት ላይ ናቸው ብለዋል፡፡

የተለያዩ አጋር አካላትን ጭምር በማስተባበር የዝግጅት ምዕራፉ በፍጥነት ተጠናቆ በአካባቢው የመማር ማስተማር ሂደቱ በሚፈለገው ፍጥነት እንዲጀመር ይደረጋልም ነው ያሉት፡፡

@admasradio
154 views18:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-01 21:31:09 ግብፃዊው የአረብ ሊግ ዋና ጸኃፊ አቡል ጌት በሕዳሴ ግድብ ላይ አስገዳጅ ስምምነት እንደሚደረስ ያላቸውን ተስፋ ገለጹ
ሱዳንን ለጦርነት የሚገፋፋ ሌላ አካል መኖሩን ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ስትገልጽ መቆየቷ ይታወቃል

የኢትዮጵያ እና የሱዳን የድንበር ውዝግብ "የሱዳንን ሙሉ ሉዓላዊነት በሚያስጠብቅ መልኩ" ሊፈታ እንደሚገባም ገልጸዋል።

የአረብ ሊግ ዋና ፀኃፊ አቡል ጌት በሕዳሴ ግድብ ላይ የሚደረገው ድርድር ከ“አንድ ወገን እርምጃ” በተለየ መልኩ ወደ ሕጋዊ እና አስገዳጅ ስምምነት ያመራል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡ ግብፃዊው አሕመድ አቡል ጌት ይህን መግለጫ የሰጡት የአረብ ሊግ እና የአፍሪካ ሕብረት ዘጠነኛው የትብብር መድረክ ፣ የሕብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ በተገኙበት ፣ ዛሬ ሰኞ በካይሮ በሚገኘው የአረብ ሊግ ዋና መስሪያ ቤት በተካሔደበት ወቅት ነው፡፡

አቡል ጌት “የግድቡ ድርድሮች ወደ ተፈለገው ግብ ያደርሳሉ ብለን ተስፋ እናደርጋለን ፤ ይህም የሁሉንም ፍላጎት ከግምት ውስጥ የሚያስገባ ሕጋዊ ፣ አስገዳጅ እና ፍትሃዊ ስምምነት ላይ መድረስ እንዲሁም በግድቡ ሙሌትና የአሠራር ሂደት ላይ መስማማት" ነው ያሉ ሲሆን “ስምምነቱ የግብፅ እና የሱዳንን የውሃ መብት በሚያስጠብቅ መልኩ እንደሚደረስ ተስፋ አለኝ" ብለዋል፡፡

ባለፉት ዓመታት ኢትዮጵያ ፣ ግብፅ እና ሱዳን በሕዳሴ ግድቡ ላይ አድካሚ ድርድር ሲያካሂዱ የቆዩ ሲሆን ካይሮ እና ካርቱም በግድቡ የውሀ ሙሌት እና አለቃቀቅ ላይ አስገዳጅ ስምምነት እንዲደረስ ይፈልጋሉ፡፡ አዲስ አበባ ደግሞ አስገዳጅ ስምምነት ላይ የመድረስ ፍላጎት የላትም፡፡

ኢትዮጵያ እና ሱዳን የገቡበትን የድንበር ውዝግብ በተመለከተ ፣ ሁለቱ ሀገራት ወደ ወታደራዊ ግጭት ውስጥ መግባት እንደሌለባቸው የገለጹት አቡል ጌት ችግሩ በሰላማዊ መንገድ መፈታት አለበት ብለዋል፡፡ ይሁንና ለሱዳን ወገንተኝነታቸውን በሚያሳይ መልኩ “በመሬቷ ላይ የሱዳንን ሙሉ ሉዓላዊነት በሚያስጠብቅ ሁኔታ እና ይዞታዋን የማስተዳደር ሕጋዊ መብቷን በሚያስጠብቅ መልኩ ነው ስምምነት መደረስ ያለበት” ብለዋል፡፡

ሱዳን በኢትዮጵያ ላይ ወረራ መፈጸሟ በሁለቱ ሀገራት መካከል አሁን ለተፈጠረው ውጥረት መንስኤ መሆኑን በተደጋጋሚ የገለጸችው ኢትዮጵያ ፣ ሱዳን ወደ ጦርነት እንድትገባ ከኋላ የሚገፋፋትአካል እንዳለ ብታስታውቅም ይህ አካል ማን እንደሆነ ግን በግልጽ ይፋ አላደረገችም፡፡

(አል አይን)
@admasradio
145 views18:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ