Get Mystery Box with random crypto!

ከመተከል የሸሹ ታጣቂዎች በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ንጹሐንን እየገደሉ መሆኑ ተጠቆመ። በኦሮሚያ ክልል ሆ | አድማስ ሬድዮ- Admas Radio

ከመተከል የሸሹ ታጣቂዎች በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ንጹሐንን እየገደሉ መሆኑ ተጠቆመ።

በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ከመተከል ሸሽተው የገቡ ታጣቂዎች በየእለቱ በንጹሐን ዜጎች ላይ የግድያና የንብረት ዘረፋ ተግባር እየፈጸሙ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች መግለጻቸወን አዲስ ማለዳ አስነብቧል።

ከጥር 14/2013 እስከ ጥር 17/2013 ድረስ ባሉት ቀናት ብቻ 10 ሰዎችን እንደገደሉ ነው የገለጸው። እንዲሁም ጥር 15/2013 በአመሩ ወረዳ ጉራ ተብሎ በሚጠራ ቀበሌ አምስት ንጹሐን በታጣቂዎች ተገድለዋል ተብሏል።

በአከባቢው ኗሪ የሆኑ ለደህንነታቸው ስለሚሰጉ ስማቸው እንዳይጠቀስ ያሳሰቡ ግለሰብ “የማኅረሰቡን ጭንቀት የሚረዳ ሕግ ያለ አይመስልም በፈጣሪ ጠባቂነት ነው የምንኖረው” ሲሉ መንግሥት ለችግሩ መፍትሔ ከመስጠት ይልቅ ዝምታ መምረጡን ገልጸዋል።

ጫጮ ጫካ ሰፍሯል የተባለው የታጣቂ ኃይል ለአከባቢው ማኅበረሰብ ስጋት እንደሆነ የአካባቢው ኗሪዎች ለመንግሥት አካላት ጥያቄ ማቅረባቸውን ተናግረዋል።

ነገር ግን የመንግሥት አካላትና በአካባቢው በጸጥታ ሥራ ላይ የተሰማሩ የኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይል ጉዳዩ ከአቅማችን በላይ ስለሆነ ምንም ልናደርግ አንችልም የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው ነሪዎቹ አስረድተዋል።

@admasradio