Get Mystery Box with random crypto!

ብርጋዴር ጄነራል መአሾ ሀጎስ ስዩም የተመድ የደቡብ ሱዳን ሰላም ማስከበር ተልእኮ አዛዥ ሆኑ! በ | አድማስ ሬድዮ- Admas Radio

ብርጋዴር ጄነራል መአሾ ሀጎስ ስዩም የተመድ የደቡብ ሱዳን ሰላም ማስከበር ተልእኮ አዛዥ ሆኑ!

በኢትዮጵያ አየር ኃይል ውስጥ ለ25 ዓመታት ያገለገሉት ብርጋዴር ጄነራል መአሾ ሀጎስ ስዩም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የደቡብ ሱዳን ሰላም ማስከበር ተልእኮ አዛዥ ሆነው ተሰየሙ።

ብርጋዴየር ጄነራል መአሾ በተመድ የላይቤሪያ እንዲሁም ዳርፉር ሰላም አስከባሪ ኃይል ውስጥ ማገልገላቸውም ታውቋል።

አዲሱን ሹመት ከጥር 04 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ እንደተሰጣቸውም በተመድ መረጃ ላይ ተገልጿል።

(Walta)
@admasradio