Get Mystery Box with random crypto!

ደቡብ አፍሪካ በአልኮል መጠጦች ላይ የጣለችውን ክልከላ አንስታለች የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲ | አድማስ ሬድዮ- Admas Radio

ደቡብ አፍሪካ በአልኮል መጠጦች ላይ የጣለችውን ክልከላ አንስታለች

የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ በኮሮና ቫይረስ ላይ የተቀመጡ አንዳንድ ክልከላዎችን ማንሳታቸው ተደምጧል፡፡ ከነዚሁ መካከል ደግሞ የአልኮል መጠጦች ላይ የተጣለው የሽያጭ ክልከላ ይገኝበታል፡፡

ባህር ዳርቻዎች እንደሚከፈቱና በቤተ እምነት ስፍራዎች ላይ የተጣለው የመሰባሰብ እግድ እንደሚላላም ተገልጿል፡፡

ፕሬዝዳንት ራማፎሳ ይህንን ያስተላለፉት የመጀመሪያ ዙር ክትባት ወደ ሀገሪቱ መግባቱን ተከትሎ ነው፡፡ ይኸውም አንድ ሚሊዮን አስትራዜኔካ ዶዝ ሲሆን ለሃገሬው ዜጎች እፎይታን ይሰጣቸዋል ተብሏል፡፡

ደቡብ አፍሪካ በአህጉሪቱ ከፍተኛው የኮቪድ ተጠቂ እና ሞት ያስመዘገበች ሀገር ናት፡፡ እንደ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ ከወረርሽኙ ጅማሮ 1.4 ሚሊዮን ዜጎቿ በቫይረሱ የተጠቁ ሲሆን ፤ 44,164 ዜጎቿን ደግሞ አሳጥቷታል፡፡

በርካታ ሀገራት ከኮሮና ቫይረስ ወዲህ የተከሰተው አዲሱ ቫይረስ ጅማሮው ከዛው ነው በሚል የጉዞ ማዕቀብን ጥለውባት ይገኛል፡፡

(ብስራትራዲዮ)
@admasradio