Get Mystery Box with random crypto!

አሜሪካ በማይናማር ላይ ማዕቀብ ልትጥል ስለመሆኑ ተሰምቷል በማይናማር ወታደራዊ ሃይሉ ፕሬዝዳንት | አድማስ ሬድዮ- Admas Radio

አሜሪካ በማይናማር ላይ ማዕቀብ ልትጥል ስለመሆኑ ተሰምቷል

በማይናማር ወታደራዊ ሃይሉ ፕሬዝዳንት ኦንግ ሳንግ ሱ ኪን ከስልጣን በማስወገድ መንበሩን መቆጣጠሩን በትናንትናው እለት መዘገባችን ይታወሳል።

ይህንኑ ተከትሎ ጉዳዩን በርካቶች እየተቃወሙት ሲሆን ፣ አሜሪካም ፕሬዝዳንት ኦንግ ሳንግ ሱ ኪን ከእስር እንድፈታ ትዕዛዝ አስተላልፋለች፡፡ ይህ ካልሆነ ሀገሪቱን በማዕቀብ እንደምትቀጣትም ነው የዛተችው፡፡

ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ‹‹ሃይል የሰዎችን ፍላጎት ሊያሳካ አይችልም ፣ የምርጫውን ውጤትም መፋቅ አይችልም›› ብለዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅቱ እንዲሁም ዩናይትድ ኪንግደም መፈንቅለ መንግስቱ ተቃውመውታል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ ባለፉት ዓመታት የቀድሞዋ ቡርማ ያሁኗ ማይናማር ዲሞክራሲን እየተገበረች ትገኛለች በሚል ከማዕቀብ መዝገብ ፍቃት እንደነበርም ይታወሳል፡፡

ጆ ባይደን ‹‹ይህ ጉዳይ ይታሰብበታል ዩናይትድ ስቴትስ በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ቢሆን ከዲሞክራሲ ጎን ነው የምትሰለፈው›› ብለዋል፡፡

በሀገሪቱ የአስአቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለአንድ ዓመት የታወጀ ሲሆን ፤ ወታደራዊ ሃይሉ ስልጣኑን በምርጫ መጭበርበር ለተሸነፉት ሚን አውንግ ህላይንግ ይተላለፋል ብለዋል፡፡

በሀገሪቱ የተካሄደውን ምርጫ ተከትሎ ህዝብን በሚያስተዳድረው መንግስት እና በወታደራዊ ሃይሉ መካከል ውጥረት ነግሶ ቆይቷል፡፡

የሰላም ኖቤል ተሸላሚዋ ፕሬዝዳንት ኦንግ ሳንግ ሱ ኪን ለ 15 ዓመታት በእርስ መቆየቷ የሚታወስ ሲሆን ፣ የዲሞክራቲክ ለውጥ እስከመጣበት 2011 ዓመት ድረስ ሀገሪቱ በወታደራዊ ሃይሉ ስትመራ ቆይታለች፡፡

(ብስራት ራዲዮ)
@admasradio