Get Mystery Box with random crypto!

በአሜሪካ ለሁለት ተከታታይ ቀናት በረዶ የቀላቀለ ከባድ ዝናብ ጣለ! በሀገሪቱ ምስራቃዊ ባህር ዳር | አድማስ ሬድዮ- Admas Radio

በአሜሪካ ለሁለት ተከታታይ ቀናት በረዶ የቀላቀለ ከባድ ዝናብ ጣለ!

በሀገሪቱ ምስራቃዊ ባህር ዳርቻ ለሁለት ተከታታይ ቀናት በረዶ የቀላቀለ ከባድ ዝናብ ጥሏል።

በኒውዮርክ ፣ ኒውጀርሲና ፔንሲልቫኒያ መጣል የጀመረው ይህ ከባድ ዝናብ በረራዎችን እያስተጓጐለ ሲሆን ፤ የኮቪድ-19 ክትባት የሚሰጡ ስፍራዎችም እንዲዘጉ አድርጓል።

የኒውዮርክ ከተማ ከንቲባው ቢል ዴ ብላሲዮ አስገዳጅ እስካልሆነ ድረስ በሚል የጉዞ ክልከላዎችን አስተላልፈዋል።

ሁኔታው ከዚህ የከፋ እንዳይሆን መስጋታቸውንም ተናግረዋል።

የኒውጀርሲ አስተዳዳሪ ፊሊፕ መርፊ በተመሳሳይ መንገዶች እንዲዘጉ አድርገዋል።

በጉዳዩ ዙሪያ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ከአማካሪዎቻቸው ጋር ስለመምከራቸውም የቢቢሲ ዘገባ ያሳያል።

(ብስራት ራዲዮ)
@admasradio