በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን በተለያዩ ወረዳዎች በነበረው የጸጥታ ችግር ተፈናቅለው በተለያዩ መጠለያ ጣቢያ ውስጥ ያሉትን ዜጎች መልሶ ለማቋቋምና ለመደገፍ የሚያስችል ከ14 ሚሊዩን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን በክልሉ የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመደገፍ የተቋቋመው የገቢ አሰባሰብ አብይ ኮሚቴ አስታውቋል። የቤኒንሻጉል ጉሙዝ ክልል የግብርና እና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ እንዳስታወቀው ገቢው የተሰበሰበው በክልል ደረጃ ካሉት ተቋማት እንዲሁም ከዞንና ወረዳ ደረጃ ካሉት መስሪያ ቤቶች ነው።ከዚህ ቀድም ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለክልሉ ተፈናቃዩች የተላከው ድጋፍ በአሶሳ ዞን ሆሞሻ በተባለ ወረዳ ተራግፎ የነበረና በቶሎ ተፈናቃዩች አልደረሰም የሚል ቅሬታም ሲቀርብ የቆየ ሲሆን ከትናንት ጅምሮ ወደ ስፋራ ማጓጓዝ መጀመሩንም ገልጿል። (ዶቼቬሌ DW) @admasradio 176 viewsedited 18:33