Get Mystery Box with random crypto!

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 734 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው፣ 106 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል | አድማስ ሬድዮ- Admas Radio

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 734 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው፣ 106 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 6 ሺህ 216 የላቦራቶሪ ምርመራ 734 ሰዎች ኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 138 ሺህ 384 ደርሷል።

በሌላ በኩል የዛሬውን 106 ጨምሮ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 122 ሺህ 968 ሆኗል።

አሁን ላይ ቫይረሱ ካለባቸው 13 ሺህ 311 ሰዎች መካከል 230 ሰዎች በጽኑ ሕሙማን መከታተያ ክፍል ውስጥ ይገኛሉ።

በተጨማሪም የ10 ሰዎች ሕይወት ማለፉ መረጋገጡን ተከትሎ በበሽታው የሞቱ ሰዎች ቁጥር 2 ሺህ 103 ደርሷል።

በአገሪቱ እስካዛሬ ድረስ በአጠቃላይ ለ1 ሚሊዮን 968 ሺህ 768 ሰዎች የኮሮናቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።

@admasradio