Get Mystery Box with random crypto!

በከተማዋ በሁለት ተጨማሪ አካባቢዎች እሳት ለማስነሳት የተደረገው ሙከራ መክሸፋን የአዲስ አበባ ከተ | አድማስ ሬድዮ- Admas Radio

በከተማዋ በሁለት ተጨማሪ አካባቢዎች እሳት ለማስነሳት የተደረገው ሙከራ መክሸፋን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገለፀ።

በከተማዋ ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች እየታዩ ያሉ የእሳት ቃጠሎዎች በከተማው ህዝብና አመራሮች፣ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ሰራተኞች፣ የፀጥታ አካላትና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት የጋራ ርብርብ የከፋ ጉዳት ሳያደርሱ መቆጣጠር መቻሉን የከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል ።

የጥፋት አላማቸው ያልተሳካላቸው አካላት ሆን ብለው ህብረተሰቡን ለማሸበር እያደረጉት ያለው ተግባር እንደማይሳካ ተገልጿል ።

ህብረተሰቡ ሳይደናገጥ ተገቢውን ጥንቃቄ እያደረገ፣ ሳይዘናጋ ነቅቶ አካባቢውን በመከታተል እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መረጃ በመለዋወጥ ያለምንም ስጋት መደበኛ እንቅስቃሴውን ማስቀጠል ይኖርበታል ተብሏል ።

የጥፋት ተግባራትን በማክሸፍና ህብረተሰቡን ከአደጋ በመታደግ ላይ ያላችሁ ባለድርሻ አካላትና ነዋሪዎችን በሙሉ የከተማ አስተዳደሩ አመስግኗል

(AMN)
@admasradio