Get Mystery Box with random crypto!

አቢሲኒያ - Times

የቴሌግራም ቻናል አርማ abisiniya_times — አቢሲኒያ - Times
የቴሌግራም ቻናል አርማ abisiniya_times — አቢሲኒያ - Times
የሰርጥ አድራሻ: @abisiniya_times
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 38.51K
የሰርጥ መግለጫ

Description
• ፈጣን እና ተዐማኒ መረጃ፣
•በአለማችን የተከናወኑ አስደናቂ ክስተቶች፣
•የስፖርት እና መዝናኛ መረጃዎች፣
•24 ሰዓት ትኩስ እና አዳዲስ መረጃ ያገኛሉ፣
•እንዲሁም ጠቅላላ እውቀት፣
ለማንኛውም መረጃ፦
#ለአስተማማኝ የመረጃ ምንጭ
https://t.me/abisiniya_times

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 20

2022-08-10 20:35:24
@abisiniya_times
5.0K views17:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 08:04:24
ይሄ የሴት አለባበስ የተጠቀመ ግለሰብ ወንድ ነው።ራሱን ቀይሮ በሴት ፖርሳ ድንጋይና ጓንት ይዞ ቤተክርቲያን ፆለት ላይ ረብሻ ለመቀስቀስ አቅዶ ሲንቀሳቀስ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተሰምቷል።
@wasulife

@abisiniya_times
6.8K viewsedited  05:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 08:03:11 አፍሪካ ኅብረት ወደፊት ይጀምራል ተብሎ በሚጠበቀው የመንግሥትና ሕወሃት ድርድር ውስጥ
የአሜሪካ፣
ተመድ እና
አውሮፓ ኅብረት ልዩ መልዕክተኞች እንዲካተቱ ፈቅዷል ሲል እንግሊዝኛው ዘ ሪፖርተር ዘግቧል።

ድርድሩን ለመጀመር በመንግሥትና ሕወሃት መካከል ያሉትን ልዩነቶች ለማጥበብ እንደሆነ ምንጮች መናገራቸውን ዘገባው ገልጧል። ኅብረቱ ዘገባው ስለጠቀሰው ስምምነት ያለው ነገር የለም

@abisiniya_times
5.5K viewsedited  05:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 08:02:01
በአሜሪካ በዋሸንግተን በዋይት ሀውስ (ነጩ ቤተ መንግስት) አቅራቢያ በደረሰ የመብረቅ አደጋ የሰዎች ህይወት አለፈ

በዋሸንግተን ነጩ ቤተ መንግስት አቅራቢያ በተፈጠረ የመብረቅ አደጋ ሶስት ሰዎች ሲሞቱ አንድ ሰው ደግሞ ክፉኛ ቆስሏል ተብሏል።

እንደ ተቋሙ ጥናት ከሆነ በአሜሪካ በዓመት በአማካኝ 40 ሚሊዮን የመብረቅ አደጋ የሚደርሱ ሲሆን አብዛኞቹ በሰዎች ላይ አደጋ አያደርሱም ተብሏል።

የመብረቅ አደጋ ከሚደርስባቸው ሰዎች መካከል 90 በመቶዎቹ ከአደጋው የሚተርፉ ሲሆን ባለፉት 20 ዓመታት ውስጥ 444 ሰዎች በዚሁ መብረቅ አደጋ ህይወታቸውን አጥተዋል።
Al ain

@abisiniya_times
5.2K viewsedited  05:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 07:13:49
@abisiniya_times
4.5K views04:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 19:52:16
የነዳጅ ድጎማ !

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በአዲሱ የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ሥርአት ተጠቃሚ የማይሆኑ ተቋማትና ተሽከርካሪዎች በ4 ወራት ጊዜ ውስጥ ከመንግሥት የሚያገኙት የነዳጅ ድጎማ ሙሉ ለሙሉ ተነስቶ ዋጋውን ራሳቸው እንደሚሸፍኑ አስታውቋል።

ለ3 ወራት ግን መንግስት ከሚገዙት ነዳጅ ውስጥ ከ25 እስከ 75 በመቶ ዋጋ እንደሚደጉም ዛሬ በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተነግሯል።

በሌላ በኩል ፤ ድጎማ የሚደረግላቸው የሕዝብ ትራንስፖርት ሰጪ ተሽከርካሪዎች ድጎማ ደግሞ በቀጣይ 5 ዓመታት ውስጥ እንደሚነሳ ተገልጿል።

በዚህም መንግሥት በየስድስት ወሩ ተፈፃሚ በሚያደርገው ሥርዓት መሰረት 10 በመቶ ድጎማን እያነሳ የሚሄድ ሲሆን በቀጣይ 5 ዓመታት ውስጥ በድጎማ የሚደገፋ የሕዝብ ትራንስፖርት ሰጪ ተሽከርካሪዎች ከድጎማ የሚወጡ ይሆናል ተብሏል።

መረጃው የኢትዮ ንግድ እና ኢንቨስትመንት መድረክ እና WMCC ነው።

@abisiniya_times
5.1K views16:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 19:04:23
@abisiniya_times
4.1K views16:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 07:06:35 ጭፍጨፋውን ለማስቆም ከተፈለገ!

1) በተለይ ወለጋ አካባቢ የሚኖሩ አማራዎችን ለመጠበቅ ምቹ ነው። በርካታ ሕዝብ አንድ አካባቢ ይኖራል። ይህን ሕዝብ መጠበቅ ቀላል ነው። የኦሮሚያ ክልል ፀጥታ ድረሱልኝ ተብሎ አይደርስም። የፌደራል ፀጥታ ማስፈር ነው። ይህ ካልተቻለ ከአካባቢው ነዋሪ ሚሊሻ አሰልጥኖ ማስታጠቅ ብቸኛው መፍትሔ ነው። ይህ ካልተፈለገ ከአንድ ሰፈር ሰላሳና አርባ አማራ ሚሊሻ ከሚታጠቅ ሺህ ህፃናትና እናቶች ይታረዱ የሚል ውሳኔ ተወስኗል ማለት ነው።

2) በአማራ ሕዝብ ላይ አሁንም የሀሰት ትርክቱ ቀጥሏል። በይፋ፣ በሕግ ፀረ አማራ ትርክት የተባሉት ተለይተው መታገድ አለባቸው። ፀረ አማራ ቅስቀሳዎች ማስቀጣት አለባቸው። ማስወገዝ አለባቸው።

3) በኦሮሚያ ክልል መዋቅር ያሉ ኦነግን የሚደግፉ አሰራሮች ወንጀል ሆነው፣ እስካሁን አማራን ያስቀጡ ላይ ሕግ መከበር አለበት። ተጠያቂነት መኖር አለበት።

4) እስካሁን የተፈፀሙት ወንጀሎች ታምነው፣ በዝርዝር ለሕዝብ ተገልፀው፣ በመንግስት ደረጃ ይቅርታ ተጠይቆባቸው፣ ተጠቂዎች ተገቢው የሞራልና ቁሳዊ ካሳ ሊሰጣቸው ይገባል። ጭፍጨፋው የቀጠለው አማራን መግደል መንግስት በዘመቻ የሚያስተክለውን የመንገድ ዳር ችግር ከመርገጥ ያነሰ ወንጀል በመሆኑ ነው። ወንጀሉ ሲገለፅ፣ ይቅርታ ሲጠየቅ፣ ካሳ ሲሰጥ፣ ለአማራ ጥበቃ ሲደረግ፣ አማራን ማጥቃት የምር ወንጀል ሲሆን አማራን መግደል ወንጀል ነው ተብሎ ይታሰባል። በዚህ ወቅት የታጠቀው ብቻ ሳይሆን ሌላውም የአማራን አንገት መቅላት የዕለት ተዕለት ክንውን አድርጎ ለምዶታል። የአማራ ሞት ከመለመድ እንዲወጣ የተለየ እርምጃ ያስፈልጋል።
ጌታቸዉ ሽፈራው
@abisiniya_times
4.8K views04:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 21:38:51
@abisiniya_times
4.4K views18:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 16:15:59
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በ100 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቅ በፍርድ ቤት ብይን ተሰጠ

የ“ፍትሕ” መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ተመስገን ደሳለኝ የ100 ሺህ ብር ዋስትና በማስያዝ ጉዳዩን በውጭ ሆኖ እንዲከታተል የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ብይን ሰጠ። ፍርድ ቤቱ ብይኑን በአብላጫ ድምጽ ያስተላለፈው በዐቃቤ ህግ በኩል የቀረበውን መቃወሚያ ውድቅ በማድረግ ነው። ተከሳሽ በቀረበበት ክስ ላይ የሚያቀርበውን የክስ መቃወሚያ ለመስማትም ፍርድ ቤቱ ለሐምሌ 11፤ 2014 ቀጠሮ ሰጥቷል።

የጋዜጠኛ ተመስገንን የወንጀል ክስ በመመልከት ላይ የሚገኘው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ የሕገ መንግስትና የሽብር ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ለዛሬ ሰኞ ሰኔ 27፤ 2014 ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረው፤ ተከሳሽ በጠበቃው አማካኝነት ያቀረበውን የዋስትና ጥያቄ መርምሮ ውሳኔ ለመስጠት ነበር። የተመስገን ጠበቃ የሆኑት አቶ ሄኖክ አክሊሉ የዋስትና ጥያቄውን ያቀረቡት ባለፈው ረቡዕ ሰኔ 22 በዋለው ችሎት ነበር።

ጠበቃ ሄኖክ በወቅቱ ባቀረቡት ማመልከቻ፤ ደንበኛቸው የተከሰሱባቸው ሶስት የወንጀል አይነቶች የዋስትና መብት የማያስከለክሉ በመሆናቸው በውጭ ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ጥያቄ አቅርበው ነበር። የፌደራል ዐቃቤ ህግ በጋዜጠኛ ተመስገን ላይ ያቀረባቸው ሶስት ክሶች፤ “ወታደራዊ ሚስጥሮችን ላልተፈቀደለት ሰው ወይም ለህዝብ ገልጿል”፣ “የሀሰት ወይም የሚያደናግር መረጃ አሰራጭቷል”፣ “መገፋፋት እና ግዙፍ ያልሆነ የማሰናዳት ተግባር ወንጀሎችን ፈጽሟል” የሚል ነው። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

[በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ ይታከልበታል]
4.9K views13:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ