Get Mystery Box with random crypto!

የጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ እውነተኛ ደጋፊዎች

የቴሌግራም ቻናል አርማ abdisira — የጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ እውነተኛ ደጋፊዎች
የቴሌግራም ቻናል አርማ abdisira — የጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ እውነተኛ ደጋፊዎች
የሰርጥ አድራሻ: @abdisira
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.46K

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2022-07-08 23:42:18 በነገው ዕለት ዝግ የሚኾኑ የአዲስአበባ መንገዶች

1443ኛው የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ የፀጥታና የደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አፈስላጊውን ዝግጀት አጠናቆ ወደ ሥራ መግባቱን አስታወቀ፡፡

የኢድ ሶላት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቀ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑም ተገልጿል፡፡

***
በየዓመቱ ከሚከበሩ ሃይማኖታዊ በዓላት የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በአል አንዱ ነው፡፡ በዓሉ በሰላም እንዲከበር ወቅታዊውን የፀጥታ ሁኔታ ያገናዘበ ዕቅድ በማውጣት የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን አስታውቋል፡፡

ሐምሌ 2 ቀን 2014 ዓ.ም የሚከበረውን የዘንድሮው የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል አከባበር አገራችን ካለችበት ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር ልዩ ዝግጅት ከመደረጉም ባሻገር ከእምነቱ አባቶችና ከፈቃደኛ ወጣቶች ጋር በበዓሉ አከባበር ዙሪያ አስቀድሞ ተገቢውን ውይይት በማድረግ ዝግጅት መደረጉ ተገልጿል፡፡

የበዓሉ ታዳሚዎች በየአካባቢያቸው በዓሉን ሲያከብሩም ሆነ ወደ ሶላቱ ሲመጡ እንደወትሮው ሁሉ የፀጥታ ኃይሉን መስተንግዶና ትዕዛዝ በማክበር ተባባሪ እንዲሆኑ የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

ህብረተሰቡ ለፀጥታው ስራ ስኬታማነት እያደረገ ላለው ቀና ትብብር ግብረሃይሉ ምስጋናውን እያቀረበ ትብብሩ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

ከፀጥታ ጋር ተያያዥ መረጃ ወይም ጥቆማ ለመስጠት በ991 ወይም 816 ነፃ የስልክ መስመሮችን እና 01- 11 -11- 01 -11፣ 01- 11- 26- 43- 59፣ 01- 11- 01- 02- 97፣ መጠቀም እንሚቻል ተገልጿል፡፡

በዓሉን አስመልክቶ የሚካሄደው የሶላት ፕሮግራም ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር ፡-

ከቦሌ አየር መንገድ ፣ በሚሊኒዬም አዳራሽ ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ደንበል ሲቲ ሴንተር ወይም ኦሎምፒያ አደባባይ አካባቢ
ከመገናኛ ፣ በሃያ ሁለት ወደ ለገሃር እንዲሁም ከቦሌ መድሃኔአለም ፣ በአትላስ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኡራኤል ቤተ-ክርስቲያን አካባቢ
ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ባሻ ወልዴ ችሎት ወይም ፓርላማ መብራት
ከፒያሣ ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ቸርችል ጎዳና ቴዎድሮስ አደባባይ
ከተክለ ኃይማኖት ፣ በሜትሮሎጂ ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ሜትሮሎጂ መስሪያ ቤት አካባቢ፣
ከተክለ ኃይማኖት ፣ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የሚወስደው መንገድ ጥቁር አንበሳ የኋላ በር አካባቢ፣
ከሲኒማ ራስ በጎላ ሚካኤል ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ጎላ ሚካኤል መስቀለኛ፣
ከጌጃ ሰፈር ፣ ጤና ጥበቃ፣ ብሄራዊ ቲያትር የሚወስደው መንገድ ጎማ ቁጠባ፣
ከባሻ ወልዴ ችሎት ፣ በኦርማ ጋራዥ ወደ ፍል ውሃ መስኪድ የሚወስደው መንገድ ንግድ ማተሚያ ቤት፣
ከጎፋ ፣ በቂርቆስ ቤተ-ክርስቲያን ወደ ለገሃር አዲሱ መንገድ የሚወስደው መንገድ ቂርቆስ ቤተ ክርስቲያን መስቀለኛው ላይ፣
ከጦር ኃይሎች ፣ ልደታ ፣ ፖሊስ ሆስፒታል ሜክሲኮ አደባባይ፣
ከሳሪስ በጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የቀድሞ አራተኛ ክፍለ ጦር፣
ይለፍ ለሌላቸው ተሽከርካሪዎች ከለሊቱ 10፡00 ሰዓት ጀምሮ ዝግጅቱ እስከሚጠናቀቅ መንገዶቹ ዝግ ይሆናሉ፡፡

ከሳሪስ በጎተራ ወደ ለገሃር የሚመጡ ከባድ ተሽከርካሪዎች ከአጎና ሲኒማ ማለፍ እንደማይችሉ የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታውቋል፡፡

በመሆኑም አሽከርካሪዎች ከፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል የተሰጠውን መረጃ ተገንዝበው የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚጠቁሙት አማራጭ መንገዶች እንዲጠቀሙ እና ለፀጥታ አካላት አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ ተላልፏል፡፡

በመጨረሻም ለእምነቱ ተከታዮች በዓሉ የፍቅር ፣ የሰላምና የደስታ እንዲሆን የፀጥታና የደህንነት የጋራ ግብረ ኃይሉ መልካም ምኞቱን ገልጿል ፡፡

(አ/አ ፖሊስ)

የቴሌግራም ቻናል https://t.me/abdisira
የፌስ ቡክ ግሩኘ https://facebook.com/groups/1214264802267291/
449 views20:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 23:42:12
390 views20:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 20:11:42 ዛሬ የተላለፉ የጋራ መኖርያ ቤቶችን የተመለከቱ መረጃዎች፡-

አሁናዊ የአንድ ካሬ የቤት ማስተላለፊያ ዋጋ
የሥራ አመራር ቦርዱ ታህሳስ 5 ቀን 2014 ዓ.ም በወሰነው መሠረት አሁን በሥራ ላይ ያለው አሁናዊ የአንድ ካሬ ማስተላለፊያ ዋጋ፡-
 20/80 ቤት ልማት ፕሮግራም 7,997.17 ብር
 40/60 ቤት ልማት ፕሮግራም 11,162.97 ብር ነው፡፡

ለዕጣ የቀረቡ ቤቶች የሚገኙባቸው ሳይቶች፣ የቤት ዓይነትና ብዛት በተመለከተ
 የ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም
o አያት 2፤ ቦሌ በሻሌ፤ ቡልቡላ ሎት 2 ሲሆኑ
 የ20/80 ቤት ልማት ፕሮግራም
o በረከት፤ቦሌ አራብሳ (ሳይት 3፤5፤6)፤ ወታደር፤የካ ጣፎ፤ ጀሞ ጋራ፤ ጎሮ ስላሴ፤ፉሪ ሃና እና ፋኑኤል

በቤት ዓይነትና ብዛት ሲታይ
በ20/80 የቤቱ ብዛት ስቱዲዮ ፡-3318 ባለአንድ መኝታ ፡- 7171 ባለሁለት መኝታ፤- 8159 በድምሩ 18648 ናቸው፡፡
በ40/60 ባለአንድ መኝታ፤- 1870 ባለሁለት መኝታ 4220 እና ባለሶስት መኝታ 753 በአጠቃላይ በድምሩ 25491 ቤቶች ናቸው፡፡

በዚህ ዙር ለዕጣ የቀረቡ ቤቶች የግንባታ አፈጻጸም ሁኔታ በጋራ መኖሪያና ንግድ ቤቶችን ለተጠቃሚዎች ለማስተላለፍ በወጣ መመሪያ ቁጥር 3/2011 በሥራ አመራር ቦርድ በማስወሰን
የ20/80 ከ96% በላይ፣ በ40/60 ከ87% በላይ የግንባታ አፈጻጸም ያላቸው ቤቶች ለዕጣ ቀርበዋል፡፡

የዚህ ዙር የዕጣ ተሳታፊዎች ሁኔታ (የቤት ፈላጊ ተመዝጋቢ ሁኔታ) የ20/80 ነባር ተመዝጋቢዎች (1997) በመመሪያው መሠረት ዝቅተኛውን የ60 ወራት ቁጠባ መጠን ያሟሉ ለእጣ ውድድር ብቁ የሆኑ እስከ የካቲት 21 2014 ዓ.ም ድረስ እና የ40/60 40% እና ከዚያ በላይ ቁጠባ ያላቸው እስከ የካቲት 21 2014 ዓ.ም የቆጠቡ ናቸው፡፡

በእጣ ውስጥ የተካተቱት ተመዝጋቢዎችን በተመለከተ ከባንክ በተገኘው መረጃ መሠረት በ20/80 የቤት ልማት ፕሮግራም 27,195 እና 40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም 52,599 በአጠቃላይ 79,794 ተመዝጋቢዎች ለዕጣ ብቁ ሆነው በዚህ ዙር ዕጣ እንዲካተቱ ተደርጓል፡፡ የዕጣ ተሳታፊዎች ሁኔታ ለዕጣ ከቀረቡ የቤት ዓይነቶች አኳያ በዝርዝር ሲታይ

በልዩ ሁኔታ ተጠቃሚ የሚደረጉ ማህበረሰብ ክፍሎችን በተመለከተ በመመሪያ ቁጥር 3/2011 በተገለጸው መሠረት ከ20/80 ነባር ተመዝጋቢዎች (1997) እና 40/60 ተመዝጋቢዎች ውስጥ
 የመንግስት ሠራተኞች 20 በመቶ፣
 ሴቶች 30 በመቶ፣
 አካል ጉዳተኞች 5 በመቶ እና አጠቃላይ ተመዝጋቢዎች 45 በመቶ በዕጣ የቤት ተጠቃሚዎች የሚለዩ ይሆናሉ።

በከተማ አስተዳደሩ ፕሮጀክቱን ለመኖር ብቁ ለማድረግ ና ቤቶቹን ለማጠናቀቅ ከባንክ ቦንድ ብድር ብር 18.7 ቢሊዮን እና ለመሠረተ ልማት ግንባታ ከመደበኛ በጀት ብር 2.871 ቢሊዮን በድምሩ ብር 21.571 ቢሊዮን በሥራ ላይ ውሏል፡፡

በ20/80 የቤት ልማት ፕሮግራም 27,195 እና 40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም 52,599 በአጠቃላይ 79,794 ተመዝጋቢዎች ለዕጣ ብቁ ሆነው በዚህ ዙር ዕጣ እንዲካተቱ ተደርጓል፡፡

በዚህ ዙር ከተላለፉ ቤቶች ውስጥ ከዚህ በፊት በማጣራት ሂደት የተገኙ ቤቶች ለልማት ተነሺ ሲስተናገዱበት ቆይተው የቀሩት ተካተዋል፡፡

የቤት ልማት ፕሮግራም ከጀመረበት አንስቶ በ17 ዓመታት ውስጥ ለህብረተሰቡ ማቅረብ የተቻለው 300 ሺህ ያህል ቤቶችን ብቻ ነው፡፡

የቤት እጣ አወጣጡ እንደ ቅደም ተከተል ሲሆን በ20/80 ፕሮግራም የ97 ተመዝጋቢዎች ቅድሚያ አግኝተዋል፡፡

የባለ ሶስት መኝታ ቤት በተመለከተ ፕሮግራሙ ባለፈው ዙር በቦርድ ውሳኔ በመዘጋቱ በቀጣይ በልዩ ሁኔታ የሚስተናገዱ ይሆናል፡፡

የቴሌግራም ቻናል https://t.me/abdisira
የፌስ ቡክ ግሩኘ https://facebook.com/groups/1214264802267291/
428 views17:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 20:11:33
356 views17:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 18:03:16
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ 1443ኛው ዒድ አል አድሃ /አረፋ/ በዓልን አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላልፋል
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1443ኛው ዒድ አል አድሃ /አረፋ/ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን ሲል መልዕክቱን ያስተላልፏል።
ይህንን ታላቅ በዓል ለየት የሚያደርገው የውስጥና የውጭ ጠላቶቻችን በስተመጨረሻ መሸነፋቸውና መጥፋታቸው አይቀሬ ቢሆንም ሀገር የማፍረስ ዓላማቸውን በጦርነት ማሳካት ሲሳናቸው በየቦታው ባደራጇቸውና ባስታጠቋቸው አሸባሪዎች አማካኝነት ንፁሀንን የጥቃት ኢላማ በማድረግ ላይ በሚገኙበት ወቅት በመሆኑ ነው።
ከዚህ ባሻገር ወቅቱ ጠላቶቻችን የውስጥ ባንዳዎችን ተጠቅመው የማይቀረውን ሦስተኛ ዙር የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ውሃ ሙሌት እንዳይሳካ ለማድረግ የሞት ሽረት ጥረት እያደረጉ የሚገኙበት ጊዜ ነው።
በመሆኑም እኛም የጠላቶቻችንን እንቅስቃሴ በሚገባ ተገንዝበን በአንድነትና በጽናት በመቆም ጠላቶቻችን ላይ ብርቱ ክንዳችንን እያሳረፍን እንገኛለን፡፡
መላው የፌደራልና የክልል ፖሊስ ኃይላችን ከሌሎች የፀጥታና ደህንነት አካላት ጋር በመቀናጀት በዓሉ በመላው ሀገራችን በሰላም እንዲከበር በቂ ዝግጅት ያደረግን መሆኑን እያሳወቅን የእስልምና እምነት ተከታዮች በዓሉ በሰላም እንዲከበር የፀጥታና ደህንነት አካላት ጎን በመቆም የበኩላችሁን ድርሻ እንድትወጡ በዚህ አጋጣሚ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
በድጋሜ ለእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለዒድ አል አድሃ /አረፋ/ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን እያልን በዓሉ የሰላምና የፍቅር እንዲሆንልን መልካም ምኞታችንን እንገልፃለን።
ዒድ ሙባረክ!
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ
ሐምሌ 1 ቀን 2014 ዓ.ም
አዲስ አበባ
452 views15:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 17:57:45
"ለመላው እስልምና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን እንኳን ለ1443ኛው የኢድ አል-አደሃ ዐረፋ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
በአሉን ስናከብር መልካም እሴቶቻችንን በማጠናከርና የተቸገሩ ወገኖቻችንን በመርዳት ብሎም የሰላማችን ዋልታ የሆነውን አብሮነታችንን እና ወንድማማችነታችንን በማጠናከር እንዲሆን እመኛለሁ!!

ዒድ ሙባረክ !"
ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

የቴሌግራም ቻናል https://t.me/abdisira
የፌስ ቡክ ግሩኘ https://facebook.com/groups/1214264802267291/
349 views14:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 17:56:15 እንኳን ለ1443ኛው ዓመተ ሒጅራ የዒድ አል-አድሐ ዐረፋ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን!
የዒድ አል-አድሐ ዐረፋ በዓልን ስናስብ ቀድሞ ወደ አዕምሯችን የሚመጣው በመንፈሳዊውም ይሁን በሥጋዊው ዓለም ታላቅነት የሚመጣው በፈተና ውስጥ በጽናት ለማለፍ በመቁረጥ እንደሆነ ነው። ነብዩ ኢብራሒም በአላህ (ሱ.ወ) ታዝዘው ልጃቸው እስማኤልን ለመሰዋት ሲነሱ አጋጣሚው ለአባትም፣ ለልጅም ቀላል አልነበረም። እጅግ ከባድ የሆነ የስሜት ፈተና ሲገጥማቸው ነበር። ከአባትነት ስሜት ከሚመነጨው ፈተና ባለፈ፣ ጠላት ሸይጣንም፣ በእርጅና እድሜያቸው ያገኙትን ልጅ ለመሰዋት መዘጋጀታቸው ጅልነት መሆኑን እየጠቀሰ ከመንገዳቸው ሊያስቀራቸው በተደጋጋሚ ፈትኗቸዋል። ነብዩ ግን አልተረቱለትም። መስዕዋት የሚሆነው ልጃቸው እስማኤልም የገዛ ፍርሃቱን አሸንፎ፣ አባቱ የአላህን ትዛዝ እንዲፈጽሙ ሲያበረታቸው ነበር።

የዘንድሮውን የዐረፋ በዓል የምናከብረው የሥነ ልቦና ጥንካሬአችን በሚፈተኑ አጋጣሚዎች መካከል ሆነን ነው። በአንድ በኩል ሰላማችንን የሚረብሹና ጦራቸውን ሰብቀው ሊወጉን አድብተው የሚጠብቁ ጠላቶች በተራቀቀ ሴራ አቅማችንን ሊያዳክሙ ይተጋሉ። በሌላ በኩል የሕዳሴ ግድብ ግንባታችን ወደ ሦስተኛውና ዋናው ምዕራፍ ለማሸጋገር ከጫፍ ደርሰን ተስፋውንና ጠላቶቻችን የደቀኑብን ስጋት በቅርብ ርቀት እየተመለከትን ነው።

ዐረፋ የመስዕዋት በዓል ነውና ይሄንን በዓል ከሙስሊም ዜጎቻችን ጋር ስናከብር መስዕዋት ለመሆን ፍላጎት ማሳየት ብቻውን እንደ ሀገር የሚገጥሙንን ፈተናና አደጋዎች ሊያስወግድልን እንደማይችል በማሰብ ነው። ያለንበት ወቅት እስከ መጨረሻው ጸንቶ መቀጠልን ይሻል። የእኛ አቋም መወላወል የሚጠቅመው ጠላቶቻችንን ነው። እኛን ለማሸነፍ ሌላ ቦታ መሄድ አይገባቸውም፤ ጦር መስበቅ፣ ነጋሪት መጎሰወም ሳይጠበቅባቸው እኛን ለማሸነፍ የእኛኑ አቋም መዋዠቅ ይጠቀማሉ። በእኛ መካከል የሚፈጠረው አለመግባባት ለእኛ የድክመታችን ምንጭ፣ ለጠላቶቻችን ደሞ አቅማቸውን የሚያሳድግ አጋጣሚን ይፈጥራል።

ለውጥ ስንጀምር አብረውን ሊታገሉ፣ በጉዟችን ጽንተው ሊቆሙ፣ የመስዕዋትነት ጊዜው ሲደርስ አብረውን ሊሰዉ ፍላጎት ያሳዩ ብዙዎች ነበሩ። ሰበብ ፈልገው የተለዩን፣ አኩርፈው የቀሩ፣ የቁርጡ ቀን ሲደርስ ሸርተት ያሉ ሰዎች ቁጥራቸው ቀላል አይደለም። ልክ እንደ እስማኤል በአቋማቸው ጸንተው ዛሬም ለመሰዋት የማያመነቱ፣ በርትተው ሌሎችን የሚያበረቱ እውነተኛ የሀገር ልጆችም አሉ።
ውድ የሀገሬ ልጆች፣
ማንም ሰው በተፈጥሮው ክፉ ሆኖ አይፈጠርም። ከልጅነት እስከ እውቀት ክፋትን እየተማረ፣ ቀስ በቀስ ተንኮልና ጭካኔን እየለመደ ይመጣል እንጂ። በጊዜ ሂደት ከላይ በሚደርባቸው የክፋት ጋቢዎች ምክንያት ቀድመው የነበሩት ደግነትና ጥሩነት በልቡ ጓዳ ውስጥ በጥልቁ ተሰውረው ይቀራሉ። የሐይማኖት አስተምህሮዎች ዓላማም ተዳፍኖ የሚኖረውን ይሄን የሰውን መልካምነትና ደግ ጠባይ ከተደበቀበት ፈልፎሎ ማውጣት ነው።

ለመልካም ተግባር የሚጸኑ ሰዎች በመንፈሳዊውም ሆነ በሥጋዊው ዓለም ትልቅ ሥፍራ ይሰጣቸዋል። ነብዩ ኢብራሒም ለሰው ልጆች ሁሉ አርአያ ከሚሆኑ ጻድቅ ሰዎች መካከል አንዱ ናቸው። በሕይወት ዘመናቸው ከልብ በመነጨ ስሜት ሰዎችን የሚወድዱ፣ ራሳቸውን ለእውነትና ለፈጣሪ የሰጡ፣ በደግነት የሚያስተናግዱና ካላቸው ላይ ከፍለው ለሰዎች የሚያጋሩ ነበሩ። ከነብዩ ኢብራሒም መልካምነትን ተምረን የዐረፋን በዓልና ከዚያ በኋላ ያሉ ቀኖችን በመተጋገዝና መደጋገፍ እንድናሳልፍ ይጠበቃል።

ሕዝበ ሙስሊሙ ብቻ ሳይሆን ሌላውም ሕዝባችን በመረዳዳትና በመተሳሰብ ኢትዮጵያን ከፈተና አውጥተን ወደ ምናስበው ስኬት ልናበቃት ይገባል። በቀና ልቦና አቅማችን የፈቀደውን መልካም ነገር በመፈጸም፣ በየተሰማራንበት ዘርፍ ለኢትዮጵያ የሚመጥነውን በማድረግ፣ ለሰላምና ለብልጽግናዋ በመትጋት፣ ለልጅ ልጅ የሚተርፍ አሻራ በማኖር እውነተኛ ኢትዮጵያዊነታችንን ማስመስከር አለብን።

በድጋሚ መልካም የዐረፋ በዓል እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ፣ ዒድ ሙባረክ!!

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ሀምሌ 2 ቀን 2014 ዓ.ም.

የቴሌግራም ቻናል https://t.me/abdisira
የፌስ ቡክ ግሩኘ https://facebook.com/groups/1214264802267291/
458 views14:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 17:56:12
433 views14:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 21:47:13
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በነገው እለት የ14ኛ ዙር የጋራ መኖሪያ ቤቶች የእጣ አወጣጥ ስነስርዓት ያካሂዳል።

የከተማ አስተዳደሩ በነገው እለት በሚያከናውነው የእጣ አወጣጥ ስነስርዓት 25,491 ቤቶችን ለተጠቃሚዎች በዕጣ የሚያስተላልፍ ይሆናል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ ግንባታቸው ሲካሄዱ የቆዩ በ40/60 ለ3ኛ ጊዜ እና በ20/80 14ኛ ጊዜ በድምሩ 25,491 ቤቶችን ለተጠቃሚዎች በዕጣ ለማስተላለፍ ዝግጅቱን በማጠናቀቅ በነገው እለት በይፋዊ የእጣ አወጣጥ ስነስርዓት ታዛቢዎች የክብር እንግዶችና የተለያዮ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት የሚያከናውን ይሆናል፡፡

የቴሌግራም ቻናል https://t.me/abdisira
የፌስ ቡክ ግሩኘ https://facebook.com/groups/1214264802267291/
520 views18:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 21:31:30
ወለጋ ሂዱና ምን እንደሆነ እወቁት ችግሩን!!
"አሁን የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች እና አክቲቪስቶች እንዲህ ብዬ ነበር ብሎ ለመናገር ካልሆነ በስተቀር፤ ለዕለቱ ለፌስቡክ ወሬ ካልሆነ በስተቀር፤ ለህዝብ ከሆነ መከታተል ነው። ወለጋ ሂዱና ምን እንደሆነ እወቁት ችግሩን!! እዚህ ተቀምጦ መጠየቅማ ማን ይከብደዋል? ከእንደዚህ አይነት ስሜት መውጣት ያስፈልጋል። ለማለት ብቻ ሳይሆን ችግሩ እንዳይፈጠር፣ ሀገር እንድትፀና ነው መረባረብ ያለብን።"

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

የቴሌግራም ቻናል https://t.me/abdisira
የፌስ ቡክ ግሩኘ https://facebook.com/groups/1214264802267291/
456 views18:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ