Get Mystery Box with random crypto!

በነገው ዕለት ዝግ የሚኾኑ የአዲስአበባ መንገዶች 1443ኛው የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰ | የጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ እውነተኛ ደጋፊዎች

በነገው ዕለት ዝግ የሚኾኑ የአዲስአበባ መንገዶች

1443ኛው የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ የፀጥታና የደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አፈስላጊውን ዝግጀት አጠናቆ ወደ ሥራ መግባቱን አስታወቀ፡፡

የኢድ ሶላት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቀ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑም ተገልጿል፡፡

***
በየዓመቱ ከሚከበሩ ሃይማኖታዊ በዓላት የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በአል አንዱ ነው፡፡ በዓሉ በሰላም እንዲከበር ወቅታዊውን የፀጥታ ሁኔታ ያገናዘበ ዕቅድ በማውጣት የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን አስታውቋል፡፡

ሐምሌ 2 ቀን 2014 ዓ.ም የሚከበረውን የዘንድሮው የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል አከባበር አገራችን ካለችበት ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር ልዩ ዝግጅት ከመደረጉም ባሻገር ከእምነቱ አባቶችና ከፈቃደኛ ወጣቶች ጋር በበዓሉ አከባበር ዙሪያ አስቀድሞ ተገቢውን ውይይት በማድረግ ዝግጅት መደረጉ ተገልጿል፡፡

የበዓሉ ታዳሚዎች በየአካባቢያቸው በዓሉን ሲያከብሩም ሆነ ወደ ሶላቱ ሲመጡ እንደወትሮው ሁሉ የፀጥታ ኃይሉን መስተንግዶና ትዕዛዝ በማክበር ተባባሪ እንዲሆኑ የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

ህብረተሰቡ ለፀጥታው ስራ ስኬታማነት እያደረገ ላለው ቀና ትብብር ግብረሃይሉ ምስጋናውን እያቀረበ ትብብሩ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

ከፀጥታ ጋር ተያያዥ መረጃ ወይም ጥቆማ ለመስጠት በ991 ወይም 816 ነፃ የስልክ መስመሮችን እና 01- 11 -11- 01 -11፣ 01- 11- 26- 43- 59፣ 01- 11- 01- 02- 97፣ መጠቀም እንሚቻል ተገልጿል፡፡

በዓሉን አስመልክቶ የሚካሄደው የሶላት ፕሮግራም ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር ፡-

ከቦሌ አየር መንገድ ፣ በሚሊኒዬም አዳራሽ ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ደንበል ሲቲ ሴንተር ወይም ኦሎምፒያ አደባባይ አካባቢ
ከመገናኛ ፣ በሃያ ሁለት ወደ ለገሃር እንዲሁም ከቦሌ መድሃኔአለም ፣ በአትላስ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኡራኤል ቤተ-ክርስቲያን አካባቢ
ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ባሻ ወልዴ ችሎት ወይም ፓርላማ መብራት
ከፒያሣ ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ቸርችል ጎዳና ቴዎድሮስ አደባባይ
ከተክለ ኃይማኖት ፣ በሜትሮሎጂ ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ሜትሮሎጂ መስሪያ ቤት አካባቢ፣
ከተክለ ኃይማኖት ፣ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የሚወስደው መንገድ ጥቁር አንበሳ የኋላ በር አካባቢ፣
ከሲኒማ ራስ በጎላ ሚካኤል ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ጎላ ሚካኤል መስቀለኛ፣
ከጌጃ ሰፈር ፣ ጤና ጥበቃ፣ ብሄራዊ ቲያትር የሚወስደው መንገድ ጎማ ቁጠባ፣
ከባሻ ወልዴ ችሎት ፣ በኦርማ ጋራዥ ወደ ፍል ውሃ መስኪድ የሚወስደው መንገድ ንግድ ማተሚያ ቤት፣
ከጎፋ ፣ በቂርቆስ ቤተ-ክርስቲያን ወደ ለገሃር አዲሱ መንገድ የሚወስደው መንገድ ቂርቆስ ቤተ ክርስቲያን መስቀለኛው ላይ፣
ከጦር ኃይሎች ፣ ልደታ ፣ ፖሊስ ሆስፒታል ሜክሲኮ አደባባይ፣
ከሳሪስ በጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የቀድሞ አራተኛ ክፍለ ጦር፣
ይለፍ ለሌላቸው ተሽከርካሪዎች ከለሊቱ 10፡00 ሰዓት ጀምሮ ዝግጅቱ እስከሚጠናቀቅ መንገዶቹ ዝግ ይሆናሉ፡፡

ከሳሪስ በጎተራ ወደ ለገሃር የሚመጡ ከባድ ተሽከርካሪዎች ከአጎና ሲኒማ ማለፍ እንደማይችሉ የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታውቋል፡፡

በመሆኑም አሽከርካሪዎች ከፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል የተሰጠውን መረጃ ተገንዝበው የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚጠቁሙት አማራጭ መንገዶች እንዲጠቀሙ እና ለፀጥታ አካላት አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ ተላልፏል፡፡

በመጨረሻም ለእምነቱ ተከታዮች በዓሉ የፍቅር ፣ የሰላምና የደስታ እንዲሆን የፀጥታና የደህንነት የጋራ ግብረ ኃይሉ መልካም ምኞቱን ገልጿል ፡፡

(አ/አ ፖሊስ)

የቴሌግራም ቻናል https://t.me/abdisira
የፌስ ቡክ ግሩኘ https://facebook.com/groups/1214264802267291/