Get Mystery Box with random crypto!

የጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ እውነተኛ ደጋፊዎች

የቴሌግራም ቻናል አርማ abdisira — የጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ እውነተኛ ደጋፊዎች
የቴሌግራም ቻናል አርማ abdisira — የጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ እውነተኛ ደጋፊዎች
የሰርጥ አድራሻ: @abdisira
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.46K

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2022-07-07 21:30:42
" ሃገር ወዳድ የሆናችሁ ኢትዮጵያውያን ሁሉ የምጠይቃችሁ

ኢትዮጵያ የጀመረችው የብልጽግና ጉዞ ቅርብ ቢመስልም ዳገት ሰለሆነ ትብብር ይፈልጋል። ከቻላቹ ወደ ላይ ግፉ፤ ካልቻላቹ ወደ ኋላ እንዳትመለስ ታኮ አስቀምጡ፤ ፍጹም ግን ማድረግ የሌለባችሁ የጠላት ዕቅድ በሆነው የቁልቁለት ጉዞ ላይ አትሳተፉ።"

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ
449 views18:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 19:11:41
480 views16:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 18:43:21
44 views15:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 18:43:15
45 views15:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 18:42:57
44 views15:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 15:24:20
አሳዛኝ ነገር ሲያጋጥም መጀመሪያ የሚጠበቀው መበታተን ሳይሆን መሰባሰብና ጠላትን መመከት ነው!!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ

የቴሌግራም ቻናል https://t.me/abdisira
191 views12:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 15:23:57
በመንግስት መዋቅር ውስጥ ተሸሽገው አገር ለማፍረስ የሚሰሩ አመራሮችን የማጥራትና እርምጃ የመውሰድ ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል!!!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፤ በመንግስት መዋቅር ውስጥ ተሸሽገው አገር ለማፍረስ የሚሰሩ አመራሮችን የማጥራትና እርምጃ የመውሰድ ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

እነዚህ ሃይሎች የግል ጥቅማቸውን በማስቀደም የኢትዮጵያን ለውጥ ለማደናቀፍ ከአሸባሪዎችና ከባንዳዎች ጋር እየሰሩ ስለመሆኑ አንስተዋል።

ጠላቶቻችን በመዋቅር ውስጥ ሰው እየገዙ መሆኑን ደርሰንበታል ይሄንን ለማጥራት እየሰራን ነው እስካሁንም በብዙዎች ላይ እርምጃ ወስደናል ብለዋል።

የቴሌግራም ቻናል https://t.me/abdisira
189 views12:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 15:14:10 “መንግስት አሸባሪ አይደለም፤ አሸባሪን የሚፋለም ኃይል ነው!"

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

#Ethiopia | ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት እየሰጡ በሚገኘው ምላሽ “መንግስት አሸባሪ አይደለም፤ አሸባሪን የሚፋለም ኃይል ነው!!” ብለዋል።

የአሜሪካን ልምድ እንደ ምሳሌ ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለፉት ስድስት ወራት ከ1 ሺህ በላይ አሜሪካውያን በሽብር ምክንያት ሕይወታቸውን አጥተዋል ብለዋል።

ጠቅላ ሚኒትሩ አሸባሪዎችን ከዘር ጋር ማያያዝ ችግር አለበት፤ በድምሩ ሸኔ እና ሌሎች የሽብር ቡድኖች የራሳቸው እግር የላቸውም ነገር ግን እግር የሚገጥምላቸው ሲያገኙ ጥፋት ይፈፅማሉ ነው ያሉት።

አሸባሪዎች የራሳቸው ማሰቢያ ጭንቅላት የላቸውም፤ ታስቦ ስራ ሲሰጣቸው ጥፋት ይፈፅማሉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ንፁሃን ዜጎችን በዚያ ሁኔታ መግደል የሽብር ባህሪ ነው፤ ኢትዮጵያ ለመበተን እና ለማፍረስ የሚፈልጉ ኃይሎች መሻትን በገሃድ የሚያሳይ ነገር ነው ብለዋል።

መንግስት ከዜጎች በተሻለ የሽብር መረጃን ቀድሞ እንደሚያገኝ ማሰብ ጠቃሚ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሳሽ እና ጠያቂ ብቻ ሳይሆን ኃላፊነት የሚወስድ እና የሚጠብቅ ዜጎችም ያስፈልጋሉ ነው ያሉት።

የፀጥታ ኃይሉ በየቀኑ ከአሸባሪ ጋር የህይወት መስዋዕትነት የሚከፍል ኃይል ነው፤ የህዝብ ስራ አሸባሪውን ከለየ በኋላ ከመንግስት ጎን ቆሞ ጥፋት እንዲቀንስ ማድረግ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

***

በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዙር 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን 16ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ከሰጡት ምላሽና ማብራሪያ፡-

በየሰዓቱ፣ በየደቂቃው መርዶና መርዶ የሚያስከትሉ ዜናዎች እንሰማለን፤ በዚህ ምክንያት የጸጥታ ተቋማትና መንግስት ይህንን ነገር ለማስቀረት ከፍተኛ ርብርብ እያደረገ መሆኑን የምታውቁት ቢሆንም እስከመቼ እስከመቼ ላላችሁት የንጹሃንን ደም በከንቱ የሚያፈሱ የትኛውም ስብስብ ሸኔም ይሁን ሌላ አሸባሪው ሃይል በጀመርነው መንገድ ጉዟችንን አጠናክረን የምንቀጥል ከሆነ ይጠፋሉ፤

ዓላማ የላቸውም፣ ግብ የላቸውም እሳቤያቸው ጥፋት ስለሆነ የእኛን ጉዞ ማደናቀፍ አይችሉም፤ መፈተን ይችላሉ፤ ፈትነዋል ግን ማሸነፍ አይችሉም፤

በጥቅሉ የሽብር የክፋት ሃይሎች ኢትዮጵያውያንን መግደል ማጎሳቆል መግፋት ማሸበር ይችሉ እንደሆነ እንጂ ከዋነኛው ዓላማችን ሊያስቀሩን አይችሉም፤

ኢትዮጵያ ውስጥ የሚደረገው ግድያ አንዳንዶች እንደሚገልጹት በቸልታ መንግስት ስራውን ስለማይሰራ ሃላፊነቱን ስለማይወጣ ተደርጎ መወሰድ የለበትም፤

መንግስት 24 ሰዓት የዜጎችን ህይወት ለመታደግ ከፍተኛ ጥረት ያደርጋል፤ በዚህም በጣም በርካታ ህይወት መታደግ ችሏል፤ ያመለጡ የጠፉብን ዜጎች እንዳሉ እንደተጠበቁ ሆኖ፤

በሚፈጠረው ችግር ሁሉ ህይወታቸውን የሚገብሩ የጸጥታ አካላት እንዳሉ መገንዘብ ተገቢ ነው።

በኢትዮጵያ ላይ የተከፈተው ጦርነት የግራጫ ጦርነት ነው፤

ይህ የግራጫ ጦርነት የመረጃ፣ የዲፕሎማሲ፣ የሳይበር እና የተልዕኮ ጦርነቶችን ያካተተ ነው፤

የግራጫ ጦርነትን ቀድመን ስለተገነዘብን መከላከያ እና ፖሊስን አጠናክረናል፤

እነዚህ የፀጥታ ተቋማት ሲገነቡ አራት ጉዳዮች ላይ ትኩረት ተደርጓል። ዜጎች ወደ እነዚህ ተቋማት ሲቀላቀሉ ዘራቸውን፣ እምነታቸውን እና የፖለቲካ አመለካከታቸውን ወደ እነዚህ ተቋማት ይዘው እንዳይገቡ እንዲሁም፥ በጥቅም ተታለው የሀገር ደህንነትን አደጋ ውስጥ የሚጥል መሆን የለበትም ተብሎ የአቅም ግንባታ ተሰርቷል።

ለዛሬ ብቻ ሳይሆን ለነገ የምናስረክበው ተቋም አድርገናቸው እየገነባን ነው።

በዚህ ሂደት መከላከያ 95 በመቶ ተሳክቶለታል። ፖሊስ እና ደህንነት በብዙ አድጓል።

የቴሌግራም ቻናል https://t.me/abdisira
184 views12:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 15:14:06
198 views12:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 14:43:55
እኛ ከዘር በላይ ነን!!
"ፓርቲ እና አመራር በዘርና በሰፈር ለመፈረጅ አታስቡ። እኛ ከዘር በላይ ነን። ከሰፈር በላይ ነን። የኢትዮጵያን ብልፅግና አብዝተን የምንመኝና የምንተጋ ሰዎች ነን። ያልኖራችሁበትን ለኛ ለመስጠት መሞከር ተገቢ አይመስለኝም። ሸኔን አሸባሪ ያልነው ከእናንተ በፊት ነው፤ በየቀኑ እየተዋጋነው ነው።"

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

የቴሌግራም ቻናል https://t.me/abdisira
191 views11:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ