Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ 1443ኛው ዒድ አል አድሃ /አረፋ/ በዓልን አስመልክቶ የእንኳን አደረሳ | የጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ እውነተኛ ደጋፊዎች

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ 1443ኛው ዒድ አል አድሃ /አረፋ/ በዓልን አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላልፋል
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1443ኛው ዒድ አል አድሃ /አረፋ/ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን ሲል መልዕክቱን ያስተላልፏል።
ይህንን ታላቅ በዓል ለየት የሚያደርገው የውስጥና የውጭ ጠላቶቻችን በስተመጨረሻ መሸነፋቸውና መጥፋታቸው አይቀሬ ቢሆንም ሀገር የማፍረስ ዓላማቸውን በጦርነት ማሳካት ሲሳናቸው በየቦታው ባደራጇቸውና ባስታጠቋቸው አሸባሪዎች አማካኝነት ንፁሀንን የጥቃት ኢላማ በማድረግ ላይ በሚገኙበት ወቅት በመሆኑ ነው።
ከዚህ ባሻገር ወቅቱ ጠላቶቻችን የውስጥ ባንዳዎችን ተጠቅመው የማይቀረውን ሦስተኛ ዙር የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ውሃ ሙሌት እንዳይሳካ ለማድረግ የሞት ሽረት ጥረት እያደረጉ የሚገኙበት ጊዜ ነው።
በመሆኑም እኛም የጠላቶቻችንን እንቅስቃሴ በሚገባ ተገንዝበን በአንድነትና በጽናት በመቆም ጠላቶቻችን ላይ ብርቱ ክንዳችንን እያሳረፍን እንገኛለን፡፡
መላው የፌደራልና የክልል ፖሊስ ኃይላችን ከሌሎች የፀጥታና ደህንነት አካላት ጋር በመቀናጀት በዓሉ በመላው ሀገራችን በሰላም እንዲከበር በቂ ዝግጅት ያደረግን መሆኑን እያሳወቅን የእስልምና እምነት ተከታዮች በዓሉ በሰላም እንዲከበር የፀጥታና ደህንነት አካላት ጎን በመቆም የበኩላችሁን ድርሻ እንድትወጡ በዚህ አጋጣሚ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
በድጋሜ ለእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለዒድ አል አድሃ /አረፋ/ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን እያልን በዓሉ የሰላምና የፍቅር እንዲሆንልን መልካም ምኞታችንን እንገልፃለን።
ዒድ ሙባረክ!
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ
ሐምሌ 1 ቀን 2014 ዓ.ም
አዲስ አበባ