Get Mystery Box with random crypto!

የሀሳብ መንገድ

የቴሌግራም ቻናል አርማ yehasab_menged — የሀሳብ መንገድ
የቴሌግራም ቻናል አርማ yehasab_menged — የሀሳብ መንገድ
የሰርጥ አድራሻ: @yehasab_menged
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 979
የሰርጥ መግለጫ

ሀሳብ የየትኛውም ነገር መነሻ ነው፤
ሀሳብን አንዳችም የሚያቆመው ነገር የለም።
ልታገኙ ምትችሏቸው ፅሁፎች #1.አስገራሚ ግለ ታሪኮች
#2. አሁን ላይ ስለምንጠቀምባቸው ነገሮች ታሪካዊ አመጣጥ። #3.የስነ-ልቦና ምክሮች

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-01-28 21:45:24 # የካርል_ማርክስ_ዲያሌክቲክ
# Dialectic
===================
ዳያሌክቲክ በ ፍልስፍና ውስጥ ከፍተኛ ቦታ የሚሰጠው ያስተሳሰብ አይነት
ነው። ይህ ዘዴ በጥንቱ ግሪክ ሲሰራበት ቆይቶ በፈላስፋው ፕላቶ ለፅሁፍ
በቅቷል። መሰረቱም፣ ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የተለያዩ አስተያየት ያላቸው
ሰወች እርስ በርሳቸው በመነጋገር ለመተማመን ከሚያደርጉት ጥረት የሚነሳ
ነው። ይህ ከ ሬቶሪክ ይለያል፤ ምክንያቱም በሬቶሪክ አንድ ግለሰብ ብቻ ብዙ
ጊዜ የወሰደ ንግግር በማድረግ የራሱን ሃሳብ ለሌሎች ማሳመኛነት ሲያቀርብ
ስለሆነ ነው።
-
እንግዲህ በዘመናት ሂደት የተለያዩ አይነት ዲያሌክቲ ዘዴወች ተነስተዋል።
ከብዙ በጥቂቱ የ ማርክስ ፣ ሄግል ፣ፕላቶ ፣ ሶቅራጥስ ና የህንዶቹን
ፍልስፍናወች ይጠቀልላል።
መሪ ሃሳቦች የዲያሌክቲክ አስተሳሰብ እንዲሰራ አስፈላጊ የሆኑ መሪ ሃሳቦች
(ዓለምን የመመልከቻ ዘዴወች ወይም ርዕዮተ አለሞች)፣ ከነዚህም 4ቱ ወሳኝ
አስተሳሰቦች እኒህ ናቸው፦
1)ሁሉም ነገር አላፊና የተወሰነ ነው፣ የሚኖረውም በ ጊዜ ወሰን ውስጥ ነው
2)ሁሉም ነገር ከተጻራሪ ሃይሎች ወይም ጎኖች ነው
የተሰራው
3)ቀስ በቀስ የሚመጣ ለውጥ በስተመጨረሻ ከፍተኛ
ለውጥ ያመጣል በዚህም አንደኛው ሃይል/ጎን ሌላኛውን ያሸንፋልና። (የመጠን
ለውጥ የጥራት ለውጥ ያመጣል)
4)ለውጥ ክብ እየሰራ ሳይሆን የሚንቀሳቀሰው (መለት ለውጥ ወደ ነበርንበት
ሳይሆን የሚመልሰን) እንደ ስፓይራል መንገደ እየከፈተ እና እያደገ ነው ሚሄደው
የጥንቱ ዲያሌክቲክ የመካከለኛው ዘመን ዲያለክቲክ የሄግል ዲያሌክቲክ:-
ይህ ታዋቂው ዘዴ ሲሆን በ3 ደረጃወች ተከፍሎ ይቀርባል። ይኸውም
በመጀመሪያ ደረጃ ተናጋሪ ቴሲስ ወይም እርሱ እውነት ነው ብሎ ያሰበውን
አስተያየት ያቀርባል። በዚህ ጊዜ ተቃውሞ አንታይ ቴሲስን ያስነሳል።
በስተመጨረሻ ይህ የሚያሰነሳው ቅራኔ በሲንቴሲስ ( ውህደት ) ይረግባል።
በዚህ መንገድ ዓለም በየጊዜው እየታደሰችና እየተለወጠች
ትሄዳለች ማለት ነው። የጀርመኑ ሄግል ከላይ የተጠቀሰውን ዘዴ በሌላ መልኩ
አስቀምጦታል። የመጀመሪያውን ሃሳብ ንጥር ሲለው ሁለተኛውን የንጥር ተቃራኒ
እንግዲህ ከሁለቱ ተጨምቆ የሚወጣውን ደግሞ ተጨባጭ ብሎታል። ይህ
የሄግል 3ቱ ቀመር ተብሎ ይታወቃል፦ ንጥር- የንጥር ተቃራኒ-ተጨባጭ።
ለምሳሌ የህልውናን ዲያሌክቲክስ ሲገልጽ ፡ በመጀመሪያ ህልውናን በነጠረ
ህልው ስናስቀምጥ ከባዶ ነገር ጋር ምንም ልዩነት የለውም። ሁሉም ወደ መኖር
የሚመጣ ነገር በሙሉ ወደ አለመኖር እየተጓዘ መሆኑን ስንረዳ (ለምሳሌ
መኖርም መሞት እንደሆነ ስንረዳ) ያንጊዜ ህልውናና ባዶነት በመዋሃድ መሆን
ይሆናሉ። በዚህ ምክንያት መሆን የ ንጥር ህልውና የሚያስከትለውን የባዶነት
ተቃርኖ ያረግባል ማለት ነው።

@yehasab_menged
@yehasab_menged
528 viewsBabi, 18:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-12 16:54:04 በእራስ መተማመን
ከተነበበ በኀላ # share ይደረግ
ለአንድ ግለሰብ ከሚያስፈልጉት መሠረታዊ የስነ-ልቦና እሴቶች መካከል አንዱና
ዋነኛው በራስ መተማመን (self confidence) ነው፡፡ ብዙዎቻችን በራስ
መተማመናችን አነስተኛ ወይም ከነጭራሹ ባለመኖሩ ምክንያት ያጣናቸው ብዙ
ነገሮች አሉ፡፡
በራስ መተማመን ማለት ይለናል በራስ መተማመን ማለት ስለ ራሳችን ችሎታ
በቂ የሆነ እውቀት እና እምነት ኖሮን ከዚህ በመነሳት ደግሞ በግፊት እና በጫና
ውስጥ ስንሆን ጥሩ ውሳኔዎችን መስጠት ነው፡፡ በራስ መተማመን የራስ
እውቀት እና ክብር (self esteem) እና የራስን ችሎታን የማወቅና ውጤታማ
በሆነ መልኩ ነገርን እፈጽማለሁ ብሎ በራስ ላይ እመነት መጣል (self
efficacy) ድምር ውጤት ሲሆን፤ በራስ የሚተማመን ሰው መገለጫዎቹም……..
ስለ ነገ ሲያስብ መልካም መልካሙ ነው የሚታየው፣ በራሱ የሚተማመን ሰው
ምክንያታዊ በመሆን ምን ይመጣልን ከግምት ውጥ በማስገባት እና አደጋን
በመጋፈጥ (risk taker) ኢላማውን ለመምታት የሚታትር ነው ፣ በእራሱ
የሚተማመን ሰው እራሱን በትክክለኛ ደረጃ የሚወድ ነው….. ወዘተ በአንጻሩ
ደግሞ በራሱ የማይተማመን ሰው ደግሞ የሚሞክራቸው ነገሮች የሚሳኩለት
የማይመስሉት፣ ነገን ሲያስብ መጥፎው ብቻ እና ውድቀቱ ፈጥኖ የሚታየው፣
አቅሙን አሟጦ ለመጠቀም የሚፈራ ወዘተ… መገለጫዎች ያሉት ነው፡፡
ዛሬ በራስ መተማመናችን አነስተኛ ስለሆነ ስላጣናቸው ነገሮች ለማውራት
ሳይሆን የተነሳሁት እንዴት በራስ መተማመንን መገንባት እንችላለን ወይም ያለንን
አጠንክረን እንሄዳለን የሚለውን ለማየት ነው፡፡
ስለዚህ በራስ መተማመንን እንዴት መገንባት እንችላለን??
★የሚከተሉትን ነጥቦች እንያቸው
1.በራስ መተማመንህን የሚሸረሽሩ ሃሳቦችን ነቅሰህ አውጣ፡- በአዕምሮህ
ውስጥ ያሉትን አልችልም፣ አይሳካልኝም፣ እወድቃለሁ እና አይሆንልኝም የሚሉ
አሉታዊ ሃሳቦችን ለያቸው፡፡ እነዚህ ሃሳቦች የጨለምተኛነትን ዘር በውስጥህ
በመዝራት የራስ ዕውቀትህን በማሳነስ በእራስ መተማመንህን ይሸረሽሩታል፡፡
2.አሉታዊውን ሃሳቦች ወደ አዎንታዊ ቀይራቸው፡- ከላይ የተጠቀሱትን
አሉታዊውን ሃሳቦች ወደ ምክንያታዊ ወደ ሆኑ አዎንታዊ ሀሳቦች ቀይራቸው
ለምሳሌ እችላለሁ፣ እሞክረዋለሁ ፣ አሳካዋለሁ ወደ ሚሉ ሃሳቦች ቀይራቸው
እነዚህን እራስን የማበረታቻ እና ለራስ ዕውቅና መስጫ ሃሰቦች ቀስ በቀስ
አዳብራቸው፡፡
3.አዎንታዊ ሃሳቦችህን ትኩረት ስጣቸው፡- አዕምሮህ አሉታዊውን ሃሳቦች ብዙ
ትኩረት እንዳይሰጠቸው ለአዎንታዊው ሃሳቦች ሰፊ ቦታና ጊዜ ስጣቸው፡፡
ለማሳካት የምታልመው ን ጉዳይ ትኩረት በመስጠት ይህን ጉዳይ ወደ ትናኝሽ
ሃሳቦች በመቀየር ወደ ተግባር ግባ፡፡
4.ዙሪያህን በጥንቃቄ ቃኘው፡- በዙሪያህ ላሉ አዎንታዊ ሀሳቦችን እንድታስብና
መልካም ድርጊቶችን እንድታከናውን ለሚያደርጉህ እና ለሚያግዙህ ወዳጆችህ
ሰፊ ጊዜ ስጥ፣ በአንጻሩ ስለ ራስህ መጥፎ እንድታስብና ምቾት የማጣት ስሜት
እንዲሰማህ ከሚያደርጉ ሰዎች እና ድርጊቶች በተቻለህ መጠን እራቅ፡፡
5.ችሎታህን ለይተህ አውጣ፡- እያንዳንዱ ሰው ቢያንስ በአንድ ነገር ላይ ጎበዝ
ነው፡፡ ስለዚሀም አንተም ጎበዝ የሆንክበትን ወይም ብሰራው አሳካዋለሁ
የምትለውን ነገር ነቅሰህ በማውጣት ትኩረትህን ወደእዚህ አድርገው፡፡
6.በራስህ ኩራ፡- ባሉህ አዎንታዊ እና በጎ ጎኖች ምክንያት ተገቢ እና መጠነኛ
የሆነ ኩራትን ኩራ፡፡
7.ሁሌም ራስህን ሁን፡- አዳዲስ ሰዎችን ስትተዋወቅ ስለ እራስህ ውሸት
በመናገር ዕውቅናን ለማግኘት አትሞክር፡፡
በራስ መተማመን ሁሌም ሚዛናዊ ሊሆን የሚገባው እሴት ነው፡፡ ዝቅተኛ በራስ
መተማመን ያለው ሰው የሚመጣውን አስቀድሞ በመፍራት ነገሮችን ከመስራት
ወይም ከመሞከር ይቆጠባል አልያም ደግሞ ከመጠን ያለፈ እና ጥግ የያዘ
በራስ መተማመን ያለው ሰው የሚመጣውን ነገር ሁሉ እየሞከረ ራሱን አደጋ
ውስጥ ይከታል፡፡ ስለዚህ በራስ መተማመን ሁለቱን በአመክንዮአዊ ልኬት
ሚዛናዊ አድርጎ መጓዝን አብዝቶ ይጠይቃል፡፡
ሰላማችሁ ይብዛ……….
መልካም ቀን !

@yehasab_menged
@yehasab_menged
576 viewsBabi, 13:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-09 06:26:16 መንፈሳዊነት ከነፍስህ ውስጥ ተፈልቅቆ የሚገኝ እንጂ ከሃይማኖትህ ተቋም
የሚሰጥህ አይደለም!
(Rethinking of your spirituality)
(እ.ብ.ይ.)
ብዙ ሰው በሕይወቱ ለሚገጥመው አስከፊ ሁኔታ አምላኩን ያማርራል፡፡ ሰው
በራሱ ስህተት ተጠያቂ የሚያደርገው ሌላ ሰውን ወይም አምላኩን ነው፡፡ ብዙ
ሰው ለራሱ ጥፋት ሃላፊነት መውሰድ አይፈልግም፡፡ ዓላማውን ሲያሳካና
ፈተናውን ሲያልፍ ራሱን ያደንቃል፤ ፈተናውን ሲወድቅ አልያም ከዓላማው
ሲደናቀፍ ግን ሌላ አካልን ያማርራል፡፡ ሐገራችን ዛሬ ለገጠማት ችግር፤
የእርስበርስ እልቂቱ፤ ለፖለቲከኞች የስልጣን ዙፋን ሲባል የሰው ደም
የሚፈሰው፤ ሐገር የሚተራመሰው ድግምት ስለነበረብን ወይም የአምላክ
ቁጣውን ስለገለፀብን አይደለም፡፡ ይሄ በራሳችን ያመጣነው የራሳችን ክፋት ነው፡፡
ሐቁን ዋጠው ወዳጄ!
ታላቁና ታዋቂው ህንዳዊ አባት ማህተመ ጋንዲ፡-
‹‹እግዚአብሔር ሃይማኖት የለውም›› ይላሉ፡፡
እውነት ነው! ጋንዲ ለዚህ አባባላቸው ምክንያታቸውን ሲያስቀምጡ በየትኛውም
ሃይማኖት ላይ ጥላቻ እንደሌላቸው ይገልጻሉ፡፡ ነገር ግን ሰውን ነፃ የሚያወጣው
ሃይማኖቱ ሳይሆን መንፈሳዊነቱ ነው ለማለት ነው፡፡ ሃይማኖት ጥቅም የለውም
እያሉን ሳይሆን ጥቅሙ ሁሉ መንፈሳዊ ለመሆን ካልሆነ ዋጋ የለውም እያሉን
ነው፡፡ ሰው መንፈሳዊ ሲሆን መንፈሳዊነቱ ውስጥ ምግባርና ግብር አለ፤
በውስጡ የሰውነት ፍሬዎች፣ የሞራል ከፍታዎች፣ የስነምግባር ዕውቀቶች
ሞልተውታል እያሉን ነው፡፡ ሃይማኖት ወደመንፈሳዊነት የሚወስድ መንገድ እንጂ
በራሱ መድረሻ አይደለምና፡፡
ድሮ ድሮ የተማረ ካልተማረው የሚሻለው በአስተሳሰቡ ነበር፡፡ ዛሬ ከተማረው
ይልቅ ያልተማረው የተሻለ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ጥንት ሃይማኖት ያለው ፈሪዓ
እግዚአብሄር እንዳለው ይቆጠራል፤ ስራው ክቡር እሱም የተከበረ ነበር፡፡ ዛሬ
አብዛኛው አማኝ አምላክን የሚፈራው በአፉ ነው፤ በስራው ግን የሚያመልከውን
አምላክ ተዳፍሯል፡፡ ሃይማኖትና አማኝ፤ ፈጣሪና የሰው ፍጥረት አልተገናኝቶም
እየሆኑ ነው፡፡ የሐገራችን ምስቅልቅል የሚያሳየን ይሄንኑ ነው፡፡ ነጋዴው በሸማቹ
ላይ ጨክኗል፡፡ ባለስልጣኑ የሚመራውን ሕዝብ እሱን ለማገልገል ለእሱ
እንደተፈጠሩ ተላላኪዎች አድርጎ ነው የሚያስበው፡፡ ሁሉም ሚናውን ስቶ
ከቦታው የለም፡፡ ሰውነቱን የጣለ ነው ዓለሙን የሞላው፡፡
አስራ አራተኛው የቲቤታውያን የእምነት አባት ሆነው እያገለገሉ ያሉት ዳላይ ላማ
እ.ኤ.አ. በ2011 ዓ.ም. ‹‹Beyond Religion›› በሚል ርእስ መፅሐፍ ፅፈው
ነበር፡፡ ሰውየው የእምነት አባት ቢሆኑም ሃይማኖት ብቻውን ሰውን ሊለውጥ
አለመቻሉን ያሰምሩበታል፡፡ ሰው ከሃይማኖቱ ባሻገር መጀመሪያ ራሱን ማወቅ፤
ሰውነቱን መረዳት እንዳለበት በመፅሐፋቸው አበክረው ይገልፃሉ፡፡ ሳይንስም
ቢሆን ምንም እንኳን የቁሳዊ ሕይወታችንን ችግሮች ቢፈታም የሰውን ውስጣዊ
ክፍተት ሊሞላ እንዳልቻለ ይናገራሉ፡፡ ሰው ለመሆን ሳይንሰም ሆነ ሃይማኖት በቂ
አይደሉም ይላሉ፡፡ ለዚህ ምክንያታቸውን ሲያስረዱ አንደኛ ነገር አብዛኛው ሰው
ሃይማኖቱን በተግባር መከተል አቁሟል፡፡ ስለዚህ የዛሬው አማኝ ሃይማኖቱ
የሚያቀርበውን የስብዕና እና የስነምግባር ፍሬዎች መልቀም አይችልም፡፡ ሁለተኛ
ዓለም እርስበርሱ በሉላዊነት እየተያያዘ ስለመጣ ሰው የራሱን ሃይማኖት ብቻ ይዞ
ተገልሎ መኖር አይችልም፡፡ ለዚህ ጥሩ ምሣሌ አድርገው ያቀረቡት የራሳቸውን
ሕዝብ ትቤታውያንን ነው፡፡ ትቤታውያን ከዓለም ሕብረተሰብ ተነጥለው በተራራማ
ቦታዎች ተወስነው፤ በምንኩስና ዓለማቸው ፀንተው ለዘመናት ኑሯቸውን
ገፍተዋል፡፡ ዛሬ ግን ግሎባላይዜሽን መጥቶ የብቸኝነታቸውን ግርግዳ አፍርሶ
የዓለሙ አካል አድርጓቸዋል፡፡
ዳላይ ላማ በዚሁ መፅሐፋቸው ገፅ 3 ላይ፡-
‹‹እኔ የሃይማኖት ሰው ነኝ፡፡ ነገር ግን ሃይማኖት ብቻውን ችግሮቻችንን ሁሉ
አይፈታም፡፡ (I am a man of religion, but religion alone can not
answer all our problems)›› ይላሉ፡፡
እውነት ነው፡፡ ሰውየው ሃይማኖት አያስፈልግም እያሉ እንዳልሆነ መሰመር
አለበት፡፡ ራሱን የሚያውቅ፣ እምነትና ስራ ያለው፣ ተመራማሪ፣ ለችግሮቹ መፍትሄ
ማመንጨት የሚችል አማኝ፤ ሰውነቱን የተረዳ ሃይማኖተኛ ቢሆን ግን በራሱም
ሆነ በዓለሙ ላይ ከፍተኛ ለውጥ ማምጣት ይችላል ለማለት ነው፡፡ የብዙዎቻችን
ችግር ያለው በግለሰብ ደረጃ ነው፡፡ እያንዳንዱ ሰው ስብዕናውን ካጣ፣ ሞራልና
ስነምግባር ካነሰው፤ ሰውነቱን አውልቆ አውሬ ከሆነ ሃይማኖት ኖረው አልኖረው፤
ተማረ አልተማረ ለውጥ አያመጣም፡፡ የችግራችን አስኳል ያለው በእያንዳንዳችን
አስተሳሰብ ላይ መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል ሲሉን ነው፡፡
እኚሁ አባት ሃይማኖትንና መንፈሳዊነትን ለያይተው ሲናገሩ እንዲህ ይላሉ፡-
‹‹አብዛኛዎቹ የዓለማችን ሐይማኖቶች ስለፍቅር፣ ስለርህራሄ፣ ስለትዕግስት፣
ስለመልካምነት፣ ስለይቅርታና ምህረት ይሰብካሉ ያስተምራሉ፡፡ ሃይማኖቶች
የሰው ልጅ ውስጣዊ ዋጋው ከፍ እንዲል ያበረታታሉ፡፡ ነገር ግን ይሄ ብቻ በቂ
አይደለም፡፡ ዛሬ ከሃይማኖተኝነት የበለጠ ስለመንፈሳዊነት የምናስብበት ጊዜ
ፊትለፊታችን ተደቅኗዋል፡፡ መንፈሳዊነት ከሃይማኖትም ከሳይንስም ከምናገኘው
የበለጠ ከፍ ያለ የስብዕና ከፍታ ላይ የሚያፈናጥጠን ነው፡፡ መንፈሳዊነት ማለት
የሰውነት ዋጋህን አውቀህ ሞራልና ስነምግባር፤ እምነትና ግብር ያለው ሰው
መሆነ ማለት ነው››
ወዳጄ ሆይ..... ሰው በጠፋበት ዓለም ሰው ሆኖ መገኘት ሊያስወግዝ፣ ከመንጋው
ሊነጥል፤ እጅ ሊያስጠቁም ቢችልም ከሰውነት በላይ ምንም የተሻለ ነገር
የለምና ሰው ለመሆን መልሰህ መላልሰህ አስብ፤ ደጋግመህ ራስህን ስራ፡፡
እንደገና ማሰብ ማርፈድ አይደለም፡፡ ከመቅረት ማርፈድ የተሻለ ነውና ራስህን
መልሰህ ለመስራት ትጋ፡፡ ራስን ማወቅ፣ ሰውነትን መረዳት፣ መንፈሳዊነትን
መያዝ፣ እምነትን በተግባር መግለፅ፤ የአፍ ብቻ ሰው አለመሆን ከችግራችን
የሚያላቅቀን፤ ከሐጢያታችን የሚያነጣን፤ ወደከፍታው የሚያወጣን መሰላል
ነው፡፡ ዛሬ ሰው ከቀልቡ አይደለም፡፡ ለመፋጀት የቸኮለ እንጂ ለይቅርታ የፈጠነ
የለም፡፡ ለማውገዝና ለመርገም እንጂ በፍቅር ለመቀበል የተዘጋጀ ሰው
ጠፍቷል፡፡ ዓለሙ በከንቱ ወሬ ጠፍቷል፡፡ አንተ ግን ከመንጋው ራስህን ነጥል፡፡
ሰው መሆንን ተማር፡፡ ሃይማኖትህን መርምር! እምነትህን አፅና፤ መንፈስህን ከፍ
አድርግ! መንፈሳዊነትህን አጥብቀህ ያዝ የዕለቱ ምርጥ መልዕክት ነው!
ራስህንም ዓለምህንም እንደገና አስብ! መንፈስህን አስውብ! መንፈሳዊነት የግል
ችግሮቻችን ሁሉ መፍትሔ ነው!
ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ለዘላለም ይኑሩ!
ቸር መንፈስ!
____________
እሸቱ ብሩ ይትባረክ (እ.ብ.ይ.)

@yehasab_menged
@yehasab_menged
606 viewsBabi, 03:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-04 21:54:11 አስተማሪ አጭር ታሪክ .!
አንድ ቤተሰብ ውስጥ አባት ከሞተ በኋላ የሚመገቡት እስኪያሳስባቸው ድረስ
ይቸገራሉ ። አንድ ጌጣጌጥ መሸጫ ሱቅ ያለው ዘመድ አላቸው እና እናትየው
ለልጇ ያላትን ለረጅም ጊዜ የተቀመጠ የአንገት እና የጣት ዳይመንድ ጌጥ
ሰጥታው እዛ ሱቅ ሄዶ እንዲሸጠው ትሰጠዋለች፡፡
ልጁ የተባለው የዘመድ ጌጣ ጌጥ ሱቅ ሄዶ እናቱ እንደላከችው አስረድቶ
እንዲገዛው ይጠይቃል፡፡ ሰውየውም ከመረመረው በኋላ "አሁን ገበያው ወድቋል
ትንሽ ግዜ ጠብቀን በጥሩ ዋጋ
እንሸጠዋለን፡፡" ብሎ ይመልስለትና የተወሰነ ገንዘብ ከሰጠው በኋላ ለልጁም
እስከዛው በየጊዜው እየመጣ እዛው ሱቅ ስራ እንዲሰራ ያደርጋል ።
ልጁ በየግዜው እየሄደ የጌጣጌጥ አሰራር ጥበብ ተካነ ፡፡ የገበያም እውቀት
አካበተ በስራውም ታዋቂም ለመሆን ቻለ ፡፡
ይሄኔ ባለሱቁ "የሆነ ግዜ ልትሸጠው አምጠተኸው የነበረውን ጌጥ አሁን
አምጣው አሁን ገበያው ጣራ ነክቷል እና ታተርፋላችሁ ፡፡ ብሎ ይልከዋል ፡፡ ልጁ
እንደተባለው እቤት ሄዶ ጌጣጌጡን በአይኑ በማየት ብቻ አርቴፊሻል ሆኖ
ያገኘዋል፡፡
ወደ ሱቅ ይመለሳል ፡፡ባለቤቱ ይጠይቃል "ዳይመንዱስ ?" ልጁም "አርቴፊሻል
ነው ግን እያወክ ያን ጊዜ ለምን አልገርከኝም ?አሁንስ ለምን ላከኝ?ሲል
ጠየቀው፡፡ ዘመዱም "ያን ጊዜ ለረጅም ዘመን ዳይመንድ ነው ብላችሁ
ያመናችሁትን ነበር ይዘህ የመጣኸው ፡፡ያለምንም እውቀት፤ ባዶህን እና በሙሉ
እምነት ብቻ ! በሰዓቱ ባለህበት ሁኔታ ልክ ያልሆነ ነገር ለማስረዳት ይከብዳል፡፡
ምናልባት ላታምኑኝ ትችሉ ነበር ፡፡ምናልባትም ባለመግባባት የሚፈጠሩ የቃላት
ልውውጥ አሁን ላይ መጥፎ ስሜት ሊያሳድርብን በቻለ ነበር ።" ብሎ በትህትና
መለሰለት፡፡
ሜሎሪና የሳይኮሎጂ ልብወለድ መጽሐፍ ላይም መሰል ምክሮችና ስነልቦናዊ
ሀሳቦችና በታሪክ ተዋዝቶ ታገኛላችሁ ፡፡ ሜሎሪና ስውር ጥበብ

@yehasab_menged
@yehasab_menged
512 viewsBabi, 18:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-01 14:50:19 "ህይወት ውስጥ እውነት ብቻውን አይገኝም።ህይወት እንደ ቡና በወተት
ነው።ወተቱ እውነት ቡናው ደግሞ ውሸት ይሁን።ግን ይሄ ልዩነት ባንጎላችን
ውስጥ ይኑር እንጂ ሲኒው ውስጥ ባንድ በኩል ቡና ባንድ በኩል ወተት
የለም።ሲኒው ውስጥ ያለው ቡና በወተት ነው።ህይወትም ውስጥ በቀኝ በኩል
እውነት በግራ በኩል ውሸት አይገኝም።ህይወት ውስጥ የምታገኘው የእውነት
ና የውሸት ቅልቅል ነው።
ጋሽ ስብሀት ገ/እግዛቤር
ሌቱም አይነጋልኝ

@yehasab_menged
@yehasab_menged
532 viewsBabi, 11:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-29 11:28:15 ግብረገብነት (Morality)

ግብረገብነት ትክክለኛውን ስህተት ከሆነው ተገቢውን ተገቢ ካልሆነው ዓላማ፣ ውሳኔና ድርጊት መለየት የመቻልና በፍትሀዊነት ላይ የተመሰረተ ህሊናዊ ባህሪ ነው፡፡ ግብረገብነት ከፍልስፍና፣ ከሀይማኖት ወይም ከባህል የመነጩ መልካም እሴቶች መገለጫ ሊሆን ይችላል፡፡ በአጠቃላይ ግብረገብነት መልካምነት ወይም ትክክለኛነት የሚለውን ትርጉም ሊወስድ ይችላል፡፡

ከግብረገብነት መገለጫዎች የሚከተሉትን እንደማሳያ እንመልከት፦

#ትዕግስት- ትዕግስት ማለት ሁኔታዎች አስቸጋሪ በሚሆኑበት ጊዜ የሚኖረን የመፅናት ችሎታ ነው፡፡ ግጭቶች እንዲወገዱ ያደርጋል፣ ከፀፀት ያድናል፣ ለይቅርታ በር ይከፍታል፡፡

#አብሮነት- መልካም ተግባራትን በማከናወን ሌሎችን መርዳት እና ደስታን ማግኘትን ያካትታል፡፡ በጋራ መኖር፣ በጋራ መስራት፣ በጋራ መብላት እንዲሁም በዋናነት በጋራ ማሰብ ነው።

#አክብሮት- አክብሮትን የሚያስቀድሙ ሰዎች ተግባቢ እና ዲፕሎማሲያዊ ሆነው ይታያሉ፡፡ በዕድሜም ሆነ በሥራ ኃላፊነት አክብሮት መስጠትን ወይም መቀበልን ባህል ወይም ወግ ማድረግ ጠቀሜታው የጎላ ነው፡፡

#መቻቻል- በሃገራችን ባህል ውስጥ ሁል ጊዜ እንደ አዎንታዊ እና ተፈላጊ ነገር ተደርጎ የሚወሰድ የባህርይ መገለጫ ነው፡፡ ቀለል ያለ የአኗኗር ዘይቤ (simplicity) መምረጥ ነው። የሚፈፀሙ ተግባራትን በምክንያታዊነት የማደራጀት ችሎታን ያሳያል።

#ትህትና- ከእንሰሳት የሚለየን የሰው ልጅ ባህሪ ነው። ትህትና ራስን ዝቅ ማድረግ ደግሞም ራስን ከፍ ማድረግ ነው። ትህትና ያለው ሰው የራሱን በትክከል ሰለሚመለከት የሌሎችን ጉድለት አይመለከትም። ወደ ንጹህ ልቦና ሰገነት የሚወጣበት መሰላል ነው።

#ፍቅር- ፍቅር በሰው ልጆች እድገት ውስጥ አንዱ የማይታይ እጅ መሆኑን መገንዘብ ጠቃሚ ነው። ፍቅር በሌላው ያምናል፣ ብሰጥ አይጎልብኝም ይላል፣ ሌሎችን ለማገልገል እንደተፈጠረ ዕድለኛ ያስባል፣ ክብሩን ያውቃል።

ለማጠቃለል የሞራል ህጎች ለሰው ልጆች ሁለንተናዊ እድገት አስተዋጾ ያላቸው የአዕምሮ እሴቶች ናቸው። ለህይወት የተሳካ መሰረት የሚጣለው ለእነዚህ ጉዳዮች በምንሰጠው ዋጋ ልክ ነው። ሰው ብቻውን ተወልዶ፣ ብቻውን ኖሮ፣ ብቻውን አስቦ፣ ሁሉንም ፍላጎቶች ብቻውን አሳክቶ ብቻውን ይሞት ዘንድ አይቻለውም። ራሱን የሚያገኘው በሌሎች መካከል እንደመሆኑ የህይወቱ ትርጉም የሚበየነው በእነዚህ በማህበራዊ የሞራል ህጎች አማካኝነት ነው።

ግብረገብነት የአንድ የሰለጠነ ማህበረሳብ እሴት መገለጫ ነው!!!

@yehasab_menged
@yehasab_menged
563 viewsTeddy, 08:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-28 21:39:46 ወጣትነት ወይስ ስሜታዊነት
ወጣትነት ግን ምንድነው? አሁንስ ያለነው ወጣቶች ምን ላይ ነው
ያለነው? .........ለኔ እንደሚመስለኝ ያሁን ጊዜ ወጣቶችስንገለፅ(እኛን ማለት
ነው)...... ሁሌም በተራ ነገራቶች የሚደመም ÷ በብራንድ የሚያምን ÷ ለገንዘብ
ሟች ÷ ማንነት ስብዕና መልካም ባህሪ የሚባሉት ነገራቶች የተረሱበት ÷ አንዱ
ካንዱ የሚፎካከረው በልብሱ በስታይሉ በብራንዱ እንጂ በአስተሳሰቡ በማንነቱ
ያልሆነበት ÷ `ለምን' ብሎ መጠየቅ የማያውቅ ትውልድ ለሱሱ ምክንያት
የሚደረድር ለባህሪው ግን ተፈጥሮዬ ነው ብሎ የሚያልፍ ÷ እኔ በራሴ ሙድ
ነው ምንቀሳቀሰው እያለ የሰዎችን ሙድ የሚቦክም ÷ እኔ ግልፅ ነኝ ምንም
አልደብቅም እየተባለ የራሱን ደብቆ ያንተን ልክልክህን የሚነግርህ ÷ ሞራሊቲ
የላሸቀበት ÷ ግራ በመጋባት ዉስጥ ግራ ላለመጋባት ብሎ ግራ የገባው ÷
ለሚያደርገው ነገር ምክንያት ማይፈልግ ÷ ከእኩዮቹ የተለየ ስለለበሰ ብቻ ራሱን
የተለየ የሚያደርግ ÷ በጩኸት የሚያምን ÷ እኔ አልጎርርም እያለ ባለመጎረሩ
የሚጎርር÷ሲበዛ ነቃፊ የሆነ ትውልድ ÷ ትዕግስት የለሽ ÷ እያንዳንዱ ነገር
ያገባኛል ይመለከተኛል የሚል ÷ ሁሉም አይቅርብኝ ÷ ባዶውን ተቀምጦ
ያለፈውን ወቃሽ ÷ አለቅጥ አስመሳይ ÷ እሱ ሲሰራው ምንም የማይመስለው
ሌላው ሲሰራ ግን ተቆጪ ተናጋሪ ÷ ተደብቆ ያንንም ያንንም ያግበሰብስና
ፊትለፊት ሲወጣ ባህላችን ሀይማኖታች የሚል ÷ሁሉም የሚያምረው ÷
አማኞችን ሲያይ ልክ እንደ አማኝ የሚያረገው ደሞ ከሚያተራምሰው ጋር
የሚያተራምስ ÷[ልክ እንደ እኔ ሁሉንም አንድ ላይ የሚነቅፍ] ÷ ማሰብ
የተነጠቀ ትውልድ ÷ ወገንተኛ ÷ በጅምላ የሚያስብ ÷ ሲበዛ አድናቂ የእንትና
አድናቂ ነኝ ማለት ብቻ ...........ብቻ ብዙ ማለት ይቻላል ወጣትነታችንን
ለምንድነው በስሜታዊነታችን ውስጥ የምንወሽቀው? ልቅ የሆነ ማንነት ስሜትን
ብቻ የሚከተል ማንነት ከዚህ አዙሪት ወጥተን በአስተሳሰባችን የምንልቅበት
በተመስጦ የምንፈካበት በማስተንተን የምንበለፅግበት ጊዜ ይመጣ ይሆን? ያ
ጊዜ እንዲመጣስ ምን ማድረግ ነው ያለብን?

@yehasab_menged
@yehasab_menged
525 viewsBabi, 18:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-18 11:18:46 ነፃና ብልህ መሆን

ነፃነትን በማግኘት በኩል ስላለው ችግር ልነግራችሁ እወዳለሁ። ችግሩ ጥልቅ ጥናትና ግንዛቤ የሚፈልግ በጣም ውስብስብ ነዉ። ስለነፃነት፣ ስለሃይማኖት ነፃነት እና ያሹትና ማድረግ ስለሚቻልበት ነፃነት ብዙ እንሰማለን። ምሁራን ይህን ርዕሰ ጉዳይ ይዘው ብዙ መፃህፍትን ፅፈዋል፡፡ ይሁን እንጂ ወደ እውነተኛው መፍትሄ በሚወስደን መልኩ በቀላሉና በቀጥታ ልንደርስበት እንደምንችል አስባለሁ፡፡

በምዕራብ አቅጣጫ ፀሃይዋ ልትጠልቅ ስትቃረብና ዓይናፋሯ ጨረቃ ከዛፎቹ በላይ ብቅ ስትል አስተውላችሁ ታውቃላችሁ? አብዛኛውን ጊዜ በዚያ ሰዓት ወንዞች በጣሙን ይረጋሉ፤ ሁሉም ነገር በላያቸው ላይ ይንፀባረቃል - ድልድዩ፣ በላዩ ላይ የሚያልፈው ባቡር፣ አስደናቂዋ ጨረቃ፣ በኋላ ላይ ብቅ የሚሉት ከዋክብት:: ኩነቱ እጅግ ውብ ነው። እንዲህ አይነቱን ውበት ለማስተዋል፣ ለመመልከት፣ በሙሉ ትኩረት ለማጤን አዕምሮ ነፃ መሆን አለበት፡፡ በችግሮች፣ በስጋቶች፣ በግምቶች መሞላት የለበትም። እንዲያ ሲሆን ብቻ ነው አዕምሮ ተረጋግቶ ማስተዋልና እጅግ ልዩ የሆነውን ውበት ማድነቅ የሚችለው።
ምናልባትም የነፃነት ችግራችን የሚፈታው በዚህ መልኩ ሳይሆን አይቀርም።

ነፃ መሆን ማለት ምን ማለት ነው? ነፃነት ማለት የሚፈልጉት ማድረግ፣ ወደፈለጉበት መሄድ፣ የፈቀዱትን ማሰብ ይሆን? ከጥገኝነት መላቀቅ ማለት ነፃነት ነውን? በዓለም ላይ ከጥገኝነት የተላቀቁ ብዙ ሰዎች አሉ፤ ነፃ የሆኑት ግን እጅግ ጥቂቶች ናቸው፡፡ ነፃነት ትልቅ ብልህነትን ይፈልጋል ፤ ነፃ መሆን ማለት ብልህ መሆን ማለት ነው። ነገር ግን ነፃ መሆንን በመሻት ብቻ ብልህነት አይመጣም፡፡ ብልህነት የሚመጣው ጠቅላላ አካባቢያችሁን፣ ማህበራዊ፣ ሃይማኖታዊ፣ ቤተሰባዊና ባህላዊ ተፅዕኖዎቻችሁን መገንዘብ ስትጀምሩ ነው። የተለያዩ ተፅዕኖዎችን ምንነት ለመረዳት - የወላጆችን፣ የመንግስትን፣ የማህበረሰብን፣ የባህልን፣ የእምነትን፣ የአምልኮን፣ ሳያስቡ የገቡበትን ባህል ተፅዕኖዎች- እነዚህን ሁሉ ተገንዝቦ ከእነዚህ ነፃ ለመሆን ጥልቅ ምልከታ ያስፈልጋል፡፡ሆኖም በውስጣችሁ ፍርሃት ስላለ በቀላሉ አትላቀቋቸውም። በህይወታችሁ ትልቅ ስፍራ አናገኝ ይሆናል ብላችሁ ትፈራላችሁ፤ ካህኑ አንድ የሆነ ነገር ይሉናል ብላችሁ ትፈራላችሁ፤ ባህሉን አልተከተልን፣ ትክክለኛውን ነገር አልፈፀምን ይሆን ብላችሁ ትፈራላችሁ። ነፃነት ፍርሃት ወይም አስገዳጅ ነገር የሌለበት፣ የደህንነትና የዋስትና ጥያቄ የማይነሳበት አዕምሯዊ ሁኔታ ነው፡፡

አብዛኞቻችን ደህንነታችን እንዲጠበቅ አንፈልግምን? ሰዎች ስለ ውበታችን፣ ስለመልካችን ወይም ስለእውቀታችን - እንዲነግሩን አንፈልግምን? እንዲህ አይነት ነገሮች የእርግጠኝነት ስሜት፣ የተፈላጊነት ስሜት ይፈጥሩብናል። ሁላችንም ዝነኞች መሆን እንፈልጋለን፡፡ ይሁንና አንድ ነገር በሆንን ቅፅበት ነፃ መሆናችን ያቆማል።

የነፃነትን ችግር ለመገንዘብ እውነተኛው ፍንጭ ይህ ነውና ይህንን በአፅንኦት ተመልከቱት፡፡ በዚህ የፖለቲከኞች፣ የስልጣን፣ የማዕረግና የደረጃ ዓለምም ሆነ ደግ፣ ሩህሩህ፣ ቅዱስ ለመሆን በምትመኙበት መንፈሳዊ ዓለም አንድ የሆነ ሰው ለመሆን ባሰባችሁ ቅፅበት ነፃ መሆናችሁ ይቀራል፡፡ የእነዚህን ነገሮች አይረቤነት የተገነዘበ፣ ልቡ ንፁህ የሆነና አንድ ሰው ለመሆን ምኞት የሌለው ሰው ነፃ ነው፡፡ የነገሩን ቀላልነት ከተገነዘባችሁ እጅግ የተለየ ውበቱንና ጥልቀቱን ታያላችሁ::

በትምህርት ውስጥ የሚገኙ ፈተናዎች አላማም ይኸው ነው - አንድ ደረጃ መስጠት፣ አንድ የሆነ ሰው ማድረግ፡፡ ማዕረጎች፣ ደረጃዎችና ዕውቀት አንድ የሆነ ሰው እንድትሆኑ ያበረታቷችኋል። ወላጆቻችሁና መምህራኖቻችሁ በህይወታችሁ አንድ ቦታ ላይ እንድትደርሱ፣ እንደ አጎታችሁ ወይም እንደ አያታችሁ ስኬታማ እንድትሆኑ ነግረዋችሁ አያውቁም? ታድያ አንድን ጀግና ወይም አንድን መምህር ለማስመስል ስትሞክሩ ነፃ አይደላችሁም:: የአንድን መምህር ወይም ወዳጅ ምሳሌ ከተከተላችሁ ወይም አንድ የሆነ ባህልን የምትከተሉ ከሆነ በውስጣችሁ አንድ የሆነ ነገር እንድትሆኑ ያስገድዳችኋል፡፡ ይህን ሃቅ ከተገነዘባችሁ ብቻ ነፃ ትሆናላችሁ፡፡

የትምህርት ዓላማ ከልጅነታችሁ ጀምሮ ሌሎችን እንዳታስመስሉ፣ ሁልጊዜም ራሳችሁን እንድትሆኑ ማስተማር መሆን አለበት- ምክንያቱም አስቀያሚም ሆናችሁ ቆንጆ፣ የዋህም ሆናችሁ ቀናተኛ ራስን መሆን በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡ ራስን መሆን አስቸጋሪ የሆነበት ምክንያት አሁን ባላችሁበት ሁኔታ የማይረቡ እንደሆናችሁ ስለምታስቡ ነው፤ ራሳችሁን ስትለውጡ ብቻ የተሻላችሁ እንደምትሆኑ ታስባላችሁ፤ ነገር ግን ይህ አይከሰትም:: ይሁን እንጂ እውነተኛ ማንነታችሁን ከተመለከታችሁትና ከተገነዘባችሁት አንድ ለውጥ እንዳለ ማየት ትችላላችሁ። ስለዚህም ነፃነት የሚገኘው አንድ የተለየ ሰው ለመሆን በመጣር ወይም የሻቱትን ነገር በማድረግ ወይም የባህልን፣ የወላጆችን፣ የመምህርን ትዕዛዝ በመከተል ሳይሆን ከአንዱ ቅፅበት እስከ ቀጣዩ ቅፅበት ማንነትን በመረዳት ነው::

እርግጥ ያ ይህን እንድታደርጉ አልተማራችሁም፤ የእናንተ ትምህርት አንድ ነገር እንድትሆኑ ነው የሚያበረታታችሁ፡፡ ይህ ግን ራስን መገንዘብ አይደለም፡፡ የእናንተ «ማንነት» በጣም ውስብስብ የሆን ነገር ነው፡፡ ወደትምህርት ቤት የሚሄደው፣ የሚጣላው፣ ጨዋታ የሚጫወተው፣ የሚፈራው ይህ አካል አይደለም ፤ አንድ ሌላ የተደበቀ ግልፅ ያልሆነ ነገር አለ፡፡ የምታስቡት ነገር ብቻ ሳይሆን በአዕምሯችሁ ውስጥ የተቀመጠው ነገር በሙሉ በሌሎች ሰዎች፣ በመፃህፍት፣ በጋዜጦች፣ በመሪዎቻችሁ የገባ ነው፡፡ ይህንን የምትገነዘቡት አንድ የሆነን ሰው ለመሆን ሳትፈልጉ ስትቀሩ፣ ማስመሰላችሁን ስታቆሙ፣ መከተላችሁን ስትተው ማለትም አንድ የሆነ ነገር እንድትሆኑ የሚገፋፋችሁን ባህል በሙሉ ስትቃወሙ ብቻ ነው:: እጅግ ልዩ ወደሆነው ነፃነት የሚመራው አብዮት ብቻ እውነተኛ ነው፡፡ የትምህርት ዓላማም ይህን ነፃነት መኮትኮት መሆን አለበት፡፡

ወላጆቻችሁ፣ መምህሮቻችሁ እና የራሳችሁ ፍላጐቶች አንድ ልዩ ሰው እንድትሆኑ ወይም ደስተኛና አስተማማኝ እንድትሆኑ ይፈልጋሉ። ታድያ ብልህ ለመሆን እስረኞች እንድትሆኑና እንድትጠፉ ምክንያት የሚሆኑት ተፅዕኖዎች በሙሉ መጥፋት ያለባቸው አይመስላችሁምን?

የአዲሱ ዓለም የመምጣት ተስፋ ሃሰተኛውን ነገር ለይተው በቃላት ሳይሆን በተግባር መቃወም በሚጀምሩ ሰዎች እጅ ውስጥ ነው። ለዛም ነው ትክክለኛው ትምህርት የሚያስፈልጋችሁ፡፡ በነፃነት ስትበለፅጉ ብቻ በባህል ላይ ያልተመሰረተ ወይም በአንድ ፈላስፋ ወይም ሃሳባዊ አስተሳሰብ ያልተቀረፀ አዲስ ዓለም መፍጠር ትችላላችሁ፡፡ አንድን ሰው ለመሆን ስትፈልጉ ወይም አንድን ሰው እንደ አብነት ወስዳችሁ እሱን ለማስመሰል ስትሞክሩ ነፃነት አይኖርም፡፡

ምንጭ ፦ ውስጣዊን ማንነት ማወቅ
ደራሲ :- ክሪሽና ሙርቲ
ተርጓሚ ፦ ተስፋሁን ምትኩ

@yehasab_menged
@yehasab_menged
752 viewsTeddy, 08:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-13 22:42:11 ችግሮችን ከመፍታት ይልቅ ችግሮችን ማስወገድ ተማር!!

ጥበብ ሕይወትን የምንቀዝፍባቸው ክህሎቶች መለኪያ ነው። ችግሮችን አስቀድሞ መከላከል ከተፈጠሩ በኋላ ከመፍታት የተሻለ ጥበብን ይጠይቃል፡፡እውነታው ሕይወት ከባድ መሆኗ ነው፡፡ ችግሮች በሁሉም አቅጣጫ በየጊዜው ይተኮሱብሃል፡፡ እጣ ፈንታ መርገጫህ ስር ጉድጓዶችን ልትቆፍርብህ ወይም መሿለኪያዎችህን ልትዘጋብህ ትችላለች። ይህንን መቀየር አትችልም፡፡ አስቀድሞ አደጋ ያለው የት ጋር እንደሆነ ከተረዳህ ግን ወዳንተ እንዳይመጣ ለማጠር እድል ይኖርሃል፡፡ በዚህ መንገድ መሰናክሎችን ሁሉ ማስወገድ ትችላለህ፡፡ ይህንን ሀሳብ አልበር አንስታይን እንዲህ ያስቀምጠዋል፡፡ “ጎበዝ ሰው ችግሮችን ይፈታል፤ ጥበበኛ ሰው ግን ችግሮችን ያስወግዳል፡፡”

ችግሩ ችግሮችን ማስወገድም የሚወደስ ነገር አለመሆኑ ነው፡፡ ሁለት ፊልሞችን አስብ፡፡
1.በመጀመሪያው ፊልም ውስጥ አንድ መርከብ ከበረዶ ክምር ጋር መጠነኛ ግጭት ይገጥመዋል፡፡ መርከቡም ይሰምጣል። በዚህ ጊዜ የመርከቧ ካፒቴን ራስ ወዳድነት በሌለበት መልኩ ራሱን አበርትቶ ተሳፋሪዎቹን ሁሉ ከመስመጥ ይታደጋቸዋል፡፡ - መርከቧ ለዘለዓለሙ ከመሰወሯ ከደቂቃዎች በፊት ሁሉንም ተጓዦች በመዳን ከጀልባው ላይ ዘሎ ወደ ሕይወት አድኑ ቦቴ ውስጥ በመግባት የመጨረሻው ሰው ነበር።

2.በሁለተኛው ፊልም ውስጥ ደግሞ እንዲህ ሆነ፡፡ መርከበኛው መርከቧ ከበረዶ ክምሩ ጋር ከመጋጨቷ በፊት አስተውሎ በቂ ርቀት ላይ እንድትቆም አደረጋት፡፡

የትኛውን ፊልም ለማየት የበለጠ ትከፍላለህ?በእርግጠኝነት የመጀመሪያውን ፊልም፡፡ ሌላ ጥያቄ ደግሞ ላንሳልህ፡፡ አንተ በመርከቧ ውስጥ ተጓዥ ብትሆን ኖሮ በየትኛው ፊልም ሁኔታ ውስጥ መሆንን ትመርጣለህ? ያለ ምንም ጥርጥር ሁለተኛው ፊልምን።

እነዚህ ምሳሌዎች እውነተኛ ገጠመኞች ናቸው ብለን እናስብ፡፡ ቀጥሎ ምን ይፈጠራል? የመጀመሪያው ፊልም ውስጥ ያለው ካፒቴን የቴሌቭዥን ፕሮግራም ላይ ይጋበዛል። ምናልባት መርከበኛነቱን ትቶ አነቃቂ ንግግሮችን እያደረገ ሕይወቱን መምራት ሊጀምር ይችላል። መንገድም በስሙ ሊሰየምለት ይችላል፡፡ ልጆቹም (ምናልባት ለመጀመሪያ ጊዜ) በአባታቸው ይኮራሉ፡፡ የሁለተኛው ፊልም ውስጥ የሳልነው ካፒቴንስ? ከስራው በጡረታ እስኪገለል ድረስ ችግሮች እንዳይከሰቱ በቅድመ ጥንቃቄ የመርከበኝነት ስራውን ይሰራል። መርሁም “ከ20 ጫማ እርቀት ላይ ልታልፈው የምትፈራውን ነገር በ500 ጫማ እርቀህ እለፈው” የሚለው የቻርሊ ሙገር የሕይወት መርህ ይሆናል፡፡

እንግዲህ ተመልከት፡- የሁለተኛው ፊልም ካፒቴን ከመጀመሪያው ፊልም ካፒቴን በሚታይ መልኩ የሚሻል ቢሆንም እኛ የምናከብረውና የምናደንቀው ግን የመጀመሪያውን ፊልም ካፒቴን ነው፡፡ ለምን? በቅድመ ጥንቃቄ የሚመጣ ስኬት ለውጪው ዓለም እይታ የሚጋለጥ አይሆንም፡፡

ጋዜጠኞች አስቸጋሪ ሁኔታዎች እንዳይመጡ ካረጉ በሳል ሰዎች ይልቅ ችገሮችን የቀለበሱ የሥራ መሪዎችን ነው የሚያሞካሹት ።የቅድመ ጥንቃቄ ስኬቶች ለውጪው ዓለም የማይታዩ ባለመሆናቸው ምክንያት ሳይታዩና ሳይወደሱ ይኖራሉ፡፡ የእንደዚህ አይነት ስኬቶት ባለቤቶችን ጥበብ የሚያውቁት በእሱ ዙሪያ ያሉ የቡድኑ አባላት ብቻ ናቸው። እነሱም ቢሆን በተወሰኑ መልኩ ቢያውቁት ነው፡፡

የአንተስ ሕይወት? አመንክም አላመንክም ከስኬቶችህ ሁሉ 50% የሚሆኑት የቅድመ መከላከል ጥንቃቄህ ውጤቶች ናቸው፡፡ ሁላችንም እንደምናደርገው ሁሉ አንተም አንዳንድ ነገሮችን በንዝህላልነት ልታደርግ ትችላለህ፡፡ ይህ እንዳለ ሆኖም ግን ስህተቶችን ላለመስራት ሁልጊዜም ትጠነቀቃለህ፡፡ በአርቆ · አሳቢነት ያስወገድካቸውን በስራህ፣ በትዳርህ፣ በትምህርትህ ወይም በሌላ የሕይወትህ ዘርፍ ሊገጥሙህ የነበሩ ችግሮችን አስብ፡፡

ጥንቃቄ (prevention) ቀላል ነገር አይደለም፡፡ ቅድመ ጥንቃቄ በባህሪው ቀድሞ ማየት (imagination) ይጠይቃል ቀድሞ መረዳትና የሚመጣውን መገመት ደግሞ ብዙውን ጊዜ አዛብተን የምንረዳቸው ነገሮች ናቸው፡፡ ይህ አዲስ ሀሳብ አያመጣልንም፡፡ በዓይነ ህሊና ማየት (imagination) ማለት የመጨረሻው ፍትሃዊ ነገር ሆኖ እስክናይ ድረስ ሊሆኑ የሚችሉት ነገሮች ውጤቶችና የመፈጠር እድላቸውን ሁሉ እንዲያስብ አዕምሯችንን ማሰራት ማለት ነው፡፡ ስለሆነም አስቀድሞ ማየትና መገመት ከባድ ስራ ነው።

በተለይ ጉዳዩ ስለአደገኛ ችግሮች ሲሆን ደግሞ ቀድሞ የመገመት ሥራ የበለጠ ፈታኝ ይሆናል፡፡ ሊመጡ እድል ባላቸው ችግሮች ላይ ሁሉ እየተጠነቀቅክ መኖር ይጠበቅብሃል? ይህስ ሁልጊዜ የተጨናነቀ ሰው ሆነህ እንድትኖር አያደርግህም? ተሞክሮዎች የሚያሳዩት እንደዚያ እንዳልሆነ ነው፡፡ ቻርሊ ሙገር እንዲህ ይላል “በሕይወት ዘመኔ ሁሉ የሚመጠብኝን አደጋዎች ስገምት ኖሬያለሁ፡፡ ሁልጊዜ ይሄንን እያሰብኩ፣ አደጋዎች ከመጡም እንዴት መመከት እንዳለብኝ እያሰላሰልኩ መኖሬ ደስተኛ እንዳልሆን አላደረገኝም፡፡”

ሮልፍ ዶልቢ
The art of good life


ሀገራችን እንደዚህ ውጥንቁጡ የወጣ ችግር ውስጥ የሆነችው አደጋዎችን ቀድሞ መከላከል የሚችሉ በሳል ሰዎች ስለሌሏት ይመሰለኛል።ጎበዝ ጦረኞች ያስፈልጉናል ግን ከዛ የበለጠ ጦርነት እንዳይከሰት ቀድመው በሳል እርምጃ የሚወስዱ መሪዎች ያስፈልጉናል። እርዳታ የሚሰበስቡ አክቲቪስቶች ቢያስፈልጉንም ከዛ የበለጠ ኢኮኖሚያችንን በዘላቂነት የሚያሻሽሉ ፖሊሲዎችን የሚቀርፁ ሙሁራን ያስፈልጉናል።

@yehasab_menged
@yehasab_menged
600 viewsTeddy, 19:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-06 14:48:23 ጦርነት የምናባዊ ተረክ ውጤት ነው!!
#repost

በአለም ታሪክ ውስጥ የሰው ልጅ ለተሳሳተ ምናባዊ ተረክ ብዙ የህይወት መስዋአትነትን ከፍሏል።ለምናባዊ ተረኮቻችን ብለን ትልቅ ዋጋ በከፈልን ቁጥር ደግሞ ተረኩ ይበልጥ እየጠነከረ መሄዱ ነው፤ ምክንያቱም ለከፈልናቸው ዋጋዎችና ላደረስነው ጉዳት ትርጉም መስጠትን አብዝተን እንሻለን።

በፖለቲካ ቋንቋ ይህ 'ልጆቻችን በከንቱ አልሞቱም' የሚባል አባዜ ነው። በ1915 ዓ.ም. ጣሊያን የወዳጅነት ሀገራቱን በመቀላቀል ወደ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ገባች። ጣሊያን ዓላማዬ ብላ የተነሣችው በኦስትሪያ-ሀንጋሪ ግዛት ኢ-ፍትሐዊ በሆነ መልኩ የተነጠቁትን ትሬንቶና ትሪስቴ የተባሉ ሁለት የጣሊያን ግዛቶችን ነፃ ለማውጣት ነበር። የጣሊያን ፖለቲከኞች ፓርላማ ውስጥ ታሪክን ለማስተካከልና ታላቋን ሮም ዳግም ለመመለስ ቃል በመግባት ሳቢ የሆኑ ንግግሮችንአደረጉ።በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩጣልያናዊያን“ለትሬንቶና ለትሪስቴ!” እያሉ በመፎከር ወደ ግንባር ነጎዱ። በቀላሉ ድል እንደሚያደርጉ አስበው ነበር።

የሆነው ግን ከዚህ በተቃራኒው ነበር። የኦስትሪያ-ሀንጋሪ ጦር በኢሶንዞ ወንዝ ዙሪያ ጠንካራ የመከላከያ መሥመር አቁመው ጠበቋቸው። ጣሊያኖቹ ራሳቸውን ደም አፋሳሽ በሆኑ ዐሥራ አንድ ውጊያዎች በመክተት ከጥቂት ኪሎሜትሮች ያልበለጠ ስፍራ መቆጣጠር ቢችሉም ድል ሊያደርጉ አልቻሉም። በመጀመሪያው ውጊያ የ5 ሺህ፤ በሁለተኛው ደግሞ የ40 ሺህ ወታደሮችን ነፍስ ገበሩ። በሦስተኛው ውጊያ 60 ሺህ ወታደሮችን አጡ። ለሁለት አሰቃቂ ዓመታት እንዲህ ከቀጠለ በኋላ በዐሥራ አንደኛው ዙር ኦስትሪያዊያን በመጨረሻ የመልሶ ማጥቃት ጀምረው በካፖሬቶ ጦርነት ጣሊያኖችን በማሸነፍ እስከ ቬኒስ መግቢያ ድረስ መልሰው አባረሯቸው፡፡ ታላቁ ዘመቻ የደም ገንዳ ሆኖ አረፈው። ጦርነቱ ሲጠናቀቅ 700,000 የጣሊያን ወታደሮች ሲገደሉ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ደግሞ ቆሰሉ።


የጣሊያን ፖለቲከኞች ከኢሶንዞ ጦርነት ሽንፈት በኋላ ሁለት አማራጭ ነበራቸው። መሳሳታቸውን አምነው ከኦስትሪያ-ሀንጋሪ ጋር የሰላም ስምምነት ይፈርማሉ። ኦስትሪያ ሀንጋሪ ጣሊያን ላይ የይገባኛል ጥያቄ ስለሌላቸው የሰላም ስምምነቱን ለመፈረም ደስተኛ ይሆኑ ነበር። ምክንያቱም በወቅቱ ይበልጥ ጠንካራ ከሆኑት ከሩሲያዊያን የሞት ሽረት እያደረጉ ነበር። ሆኖም ፖለቲከኞቹ ወደ 15 ሺህ የሟች ወታደር ወላጆች “ሚስቶችና ልጆች ጋር በመሄድ “ይቅርታ ስሕተት ሰርተናል። ብዙም አትዘኑ፤ ግን የእናንት ጂኦቫኒና ማርኮ የሞቱት በከንቱ ነበር” አሊያም “ጂኦቫኒና ማርኮ ጀግኖት ነበሩ! የሞቱት ትሪስቴ የጣሊያን ግዛት እንድትሆን ብለው ስለሆነ ደማቸው በከንቱ ፈሶ እንዳይቀር እናደርጋለን፤ ድል የኛ እስክትሆንም እንፋለማለን!” ሊሏቸው ይችላሉ። እንደሚገመተው ፖለቲከኞቹ ሁለተኛውን አማራጭ በመምረጣቸው ሌላ ጦርነት ውስጥ ገብተው 40,000 ተጨማሪ ወታደሮች ሞቱ። ፖለቲከኞቹ አሁንም ቢሆን ውጊያውን መቀጠል መረጡ፤ ምክንያቱም "ልጆቻችን በከንቱ አልሞቱምና።"

ሆኖም ፖለቲከኞቹን ብቻ ልንወቅስ አንችልም። ብዙ ሕዝብም ጦርነቱን እየደገፈው ነበር። ጦርነቱ ካበቃ በኋላ ጣሊያን ድንበሮቹን መልሳ ማግኘት አልቻለችም። የጣሊያን ዴሞክራሲም “ሀገሪቱ ለከፈለችው መሥዋዕትነት በሙሉ ካሳ እንድታገኝ እናደርጋለን” ያለውን ቤኒቶ ሙሶሊኒና ፋሺስት ጭፍሮቹን የበላይ አድርጎ አስቀመጠ። ለወላጆች ልጃቸው ያለ በቂ ምክንያት ሕይወቱን እንዳጣ መንገር ፖለቲከኞቹ ቢከብዳቸውም ወላጆች ይህንን ለራሳቸው መንገር ይበልጡኑ ይከብዳቸዋል፤ ለተጎጂው ደግሞ ከዚያም የባሰ ነው። በጦርነት እግሩ ተቆርጦ አካል ጉዳተኛ የሆነ አንድ ወታደር ለራሱ “የገዛ አካሌን መሥዋዕት
ያደረግኩት ለዘለዓለማዊቷ ሀገሬ ጣልያን ክብር ነው” ሲል ይመርጣል እንጂ “በሞኝነት ራስ ወዳድ የሆኑ ፖለቲከኞችን በማመኔ የገዛ እግሬን አጣሁ” ሊል አይችልም። ምናባዊ ታሪክን ተቀብሎ መኖር እጅግ ቀላል ነው፤ ምክንያቱም ለስቃያችን ትርጉም ይሰጣልና።

ካህናት ይህንን ሕግ የተረዱት ከሺህ ዓመታት በፊት ነው። ይህ በርካታ ሃይማኖታዊ ስርዓቶችንና ትእዛዛትን የሚያድበሰብስ ነው። ሰዎች እንደ ሀገርና አማልክት ባሉ ምናባዊ አካላት ላይ እምነት እንዲያሳድሩ ከፈለጋችሁ ዋጋ የሚሰጡትን አንድ ነገር መሥዋዕት እንዲያደርጉ ልታደርጓቸው ይገባል። መስዋዕቱ ከባድ በሆነ ቁጥር ሰዎች በመሥዋዕት ተቀባዩ ህልውና ላይ ያላቸው እምነት ይበልጥ ይጠነክራል። ለጁፒተር ውድ ንብረቱ የሆነ በሬውን የሚሰዋ አንድ ምስኪን ገበሬ፤ ጁፒተር ስለሚባል አምላክ ህልውና ያምናል። እንደዚያ ካልሆነ ድድብናውን በሌላ በምን ያሳብባል? ገበሬው ከዚህ ቀደም የሰዋቸው በሬዎች ባክገው እንዳልቀሩ ራሱን ለማሳመን ሌላ በሬ፣ እንደገና ሌላ በሬ፣ አሁንም ሌላ በሬ ለመሥዋዕት ያቀርባል። በተመሳሳይ ምክንያትም ለጣሊያን ክብር ስል ልጄን መሥዋዕት ካደረኩኝ ወይንም ለኮሚኒስታዊ አብዮት ስል እግሬ ከተቆረጠ፤ ይህ እኔን ወደ አክራሪ የጣሊያን ብሔረተኛ ወይም ወደ ኮሚኒስትነት ለመለወጥ በቂ ምክንያት ነው። የጣሊያን ብሔረተኝነት ትርክቶች ወይም የኮሚኒስት የፕሮፓጋንዳ ውሸት ሆነው ከተገኙ ልጄ በሞት የተነጠቀብኝ ወይም አካል ጉዳተኛ የሆንኩት ትርጉም ለሌለው ነገር እንደሆነ ለማመን እገደዳለሁ። ይህንን ለመቀበል ድፍረቱ ያላቸው ጥቂቶች ብቻ ናቸው።


በዚህ ወጥመድ ውስጥ የሚወድቁት መንግሥታት ብቻ አይደሉም። የንግድ ኩባንያዎች አክሳሪ የሆኑ ሥራዎች ላይ ሚሊዮኖችን ያፈሳሉ፣ ግለሰቦች ደግሞ ጤናማ ያልሆነ ትዳራቸው ላይ የሙጢኝ ብለው ይቀራሉ ወይም እድገት በማያገኙበት ሥራ ላይ እድሜ ልክ ይቆያሉ። ተራኪው እኔነት(ኢጎ) ያለፈ ስቃያችን ምንም ትርጉም እንዳልነበረው ላለመቀበል ሲል ብቻ ወደፊትም እየተሰቃየን እንድንቀጥል ይፈልጋል። ካለፉ ስሕተቶቻችን ራሳችንን ለማውጣት ከፈለግን ተራኪ እኔነታችን እነኚህ ስሕተቶች ውስጥ ትርጉም የሚሸጉጥ አንድ ማምለጫ ታሪክን ይፈጥራል።

ሆሞ ዲየስ(ገፅ 81-83)
ኖኀ ሀራሪ

ይሄን ሀሳብ አሁን ወዳለው የሀገራችን ቀውስ እናመጣው። ህውሀት የትግራይ ህዝብ ላይ በቀላሉ የማይፋቅ የተዛባ 'ምናባዊ ተረክ' ፈጥሯል።እናም ይህም ተረክ" ትግራይ ነፃ እና ታላቅ ሀገር ትሆናለች ነገር ግን ጠላቶች ከበውሀል ከጠላቶችህም ነፃ የማወጣህ እኔ ነኝ።ለነፃነትህም ልጆችህን ሰውተሀል የልጆጅህም ደም በከንቱ ፈሶ አይቀርም እና ድል የኛ እስክትሆንም እንፋለማለን!”
የሚል ይመስላል።

ለተሳሳተ ምናባዊ ተረክ ብዙ የህይወት መስዋአትነትን ባስከፈላቸው ቁጥር ተረኩ ይበልጥ እየጠነከረ ይሄዳል። ምክንያቱም ለከፈሉት ዋጋና ለደረሰው ጉዳት ትርጉም መስጠትን ይፈልጋሉ።ህዝቡም በጦርነቱ አሸናፊ እንደማይሆን እያወቀው። ጦርነቱን ቢያሸንፍም አትራፊ እንደማይሆን እየተረዳው ልጆቻችን በከንቱ አልሞቱም በሚል አባዜ ትርጉም ለሌለው ጦርነት ራሱን ይማግዳል።ይህም የማያባራ እልቂትን በመፍጠር ትልቅ የታሪክ ጠባሳ ያኖራል።

@yehasab_menged
@yehasab_menged
556 viewsTeddy, 11:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ