Get Mystery Box with random crypto!

ግብረገብነት (Morality) ግብረገብነት ትክክለኛውን ስህተት ከሆነው ተገቢውን ተገቢ ካልሆነው | የሀሳብ መንገድ

ግብረገብነት (Morality)

ግብረገብነት ትክክለኛውን ስህተት ከሆነው ተገቢውን ተገቢ ካልሆነው ዓላማ፣ ውሳኔና ድርጊት መለየት የመቻልና በፍትሀዊነት ላይ የተመሰረተ ህሊናዊ ባህሪ ነው፡፡ ግብረገብነት ከፍልስፍና፣ ከሀይማኖት ወይም ከባህል የመነጩ መልካም እሴቶች መገለጫ ሊሆን ይችላል፡፡ በአጠቃላይ ግብረገብነት መልካምነት ወይም ትክክለኛነት የሚለውን ትርጉም ሊወስድ ይችላል፡፡

ከግብረገብነት መገለጫዎች የሚከተሉትን እንደማሳያ እንመልከት፦

#ትዕግስት- ትዕግስት ማለት ሁኔታዎች አስቸጋሪ በሚሆኑበት ጊዜ የሚኖረን የመፅናት ችሎታ ነው፡፡ ግጭቶች እንዲወገዱ ያደርጋል፣ ከፀፀት ያድናል፣ ለይቅርታ በር ይከፍታል፡፡

#አብሮነት- መልካም ተግባራትን በማከናወን ሌሎችን መርዳት እና ደስታን ማግኘትን ያካትታል፡፡ በጋራ መኖር፣ በጋራ መስራት፣ በጋራ መብላት እንዲሁም በዋናነት በጋራ ማሰብ ነው።

#አክብሮት- አክብሮትን የሚያስቀድሙ ሰዎች ተግባቢ እና ዲፕሎማሲያዊ ሆነው ይታያሉ፡፡ በዕድሜም ሆነ በሥራ ኃላፊነት አክብሮት መስጠትን ወይም መቀበልን ባህል ወይም ወግ ማድረግ ጠቀሜታው የጎላ ነው፡፡

#መቻቻል- በሃገራችን ባህል ውስጥ ሁል ጊዜ እንደ አዎንታዊ እና ተፈላጊ ነገር ተደርጎ የሚወሰድ የባህርይ መገለጫ ነው፡፡ ቀለል ያለ የአኗኗር ዘይቤ (simplicity) መምረጥ ነው። የሚፈፀሙ ተግባራትን በምክንያታዊነት የማደራጀት ችሎታን ያሳያል።

#ትህትና- ከእንሰሳት የሚለየን የሰው ልጅ ባህሪ ነው። ትህትና ራስን ዝቅ ማድረግ ደግሞም ራስን ከፍ ማድረግ ነው። ትህትና ያለው ሰው የራሱን በትክከል ሰለሚመለከት የሌሎችን ጉድለት አይመለከትም። ወደ ንጹህ ልቦና ሰገነት የሚወጣበት መሰላል ነው።

#ፍቅር- ፍቅር በሰው ልጆች እድገት ውስጥ አንዱ የማይታይ እጅ መሆኑን መገንዘብ ጠቃሚ ነው። ፍቅር በሌላው ያምናል፣ ብሰጥ አይጎልብኝም ይላል፣ ሌሎችን ለማገልገል እንደተፈጠረ ዕድለኛ ያስባል፣ ክብሩን ያውቃል።

ለማጠቃለል የሞራል ህጎች ለሰው ልጆች ሁለንተናዊ እድገት አስተዋጾ ያላቸው የአዕምሮ እሴቶች ናቸው። ለህይወት የተሳካ መሰረት የሚጣለው ለእነዚህ ጉዳዮች በምንሰጠው ዋጋ ልክ ነው። ሰው ብቻውን ተወልዶ፣ ብቻውን ኖሮ፣ ብቻውን አስቦ፣ ሁሉንም ፍላጎቶች ብቻውን አሳክቶ ብቻውን ይሞት ዘንድ አይቻለውም። ራሱን የሚያገኘው በሌሎች መካከል እንደመሆኑ የህይወቱ ትርጉም የሚበየነው በእነዚህ በማህበራዊ የሞራል ህጎች አማካኝነት ነው።

ግብረገብነት የአንድ የሰለጠነ ማህበረሳብ እሴት መገለጫ ነው!!!

@yehasab_menged
@yehasab_menged