Get Mystery Box with random crypto!

ወጣትነት ወይስ ስሜታዊነት ወጣትነት ግን ምንድነው? አሁንስ ያለነው ወጣቶች ምን ላይ ነው ያለነው? | የሀሳብ መንገድ

ወጣትነት ወይስ ስሜታዊነት
ወጣትነት ግን ምንድነው? አሁንስ ያለነው ወጣቶች ምን ላይ ነው
ያለነው? .........ለኔ እንደሚመስለኝ ያሁን ጊዜ ወጣቶችስንገለፅ(እኛን ማለት
ነው)...... ሁሌም በተራ ነገራቶች የሚደመም ÷ በብራንድ የሚያምን ÷ ለገንዘብ
ሟች ÷ ማንነት ስብዕና መልካም ባህሪ የሚባሉት ነገራቶች የተረሱበት ÷ አንዱ
ካንዱ የሚፎካከረው በልብሱ በስታይሉ በብራንዱ እንጂ በአስተሳሰቡ በማንነቱ
ያልሆነበት ÷ `ለምን' ብሎ መጠየቅ የማያውቅ ትውልድ ለሱሱ ምክንያት
የሚደረድር ለባህሪው ግን ተፈጥሮዬ ነው ብሎ የሚያልፍ ÷ እኔ በራሴ ሙድ
ነው ምንቀሳቀሰው እያለ የሰዎችን ሙድ የሚቦክም ÷ እኔ ግልፅ ነኝ ምንም
አልደብቅም እየተባለ የራሱን ደብቆ ያንተን ልክልክህን የሚነግርህ ÷ ሞራሊቲ
የላሸቀበት ÷ ግራ በመጋባት ዉስጥ ግራ ላለመጋባት ብሎ ግራ የገባው ÷
ለሚያደርገው ነገር ምክንያት ማይፈልግ ÷ ከእኩዮቹ የተለየ ስለለበሰ ብቻ ራሱን
የተለየ የሚያደርግ ÷ በጩኸት የሚያምን ÷ እኔ አልጎርርም እያለ ባለመጎረሩ
የሚጎርር÷ሲበዛ ነቃፊ የሆነ ትውልድ ÷ ትዕግስት የለሽ ÷ እያንዳንዱ ነገር
ያገባኛል ይመለከተኛል የሚል ÷ ሁሉም አይቅርብኝ ÷ ባዶውን ተቀምጦ
ያለፈውን ወቃሽ ÷ አለቅጥ አስመሳይ ÷ እሱ ሲሰራው ምንም የማይመስለው
ሌላው ሲሰራ ግን ተቆጪ ተናጋሪ ÷ ተደብቆ ያንንም ያንንም ያግበሰብስና
ፊትለፊት ሲወጣ ባህላችን ሀይማኖታች የሚል ÷ሁሉም የሚያምረው ÷
አማኞችን ሲያይ ልክ እንደ አማኝ የሚያረገው ደሞ ከሚያተራምሰው ጋር
የሚያተራምስ ÷[ልክ እንደ እኔ ሁሉንም አንድ ላይ የሚነቅፍ] ÷ ማሰብ
የተነጠቀ ትውልድ ÷ ወገንተኛ ÷ በጅምላ የሚያስብ ÷ ሲበዛ አድናቂ የእንትና
አድናቂ ነኝ ማለት ብቻ ...........ብቻ ብዙ ማለት ይቻላል ወጣትነታችንን
ለምንድነው በስሜታዊነታችን ውስጥ የምንወሽቀው? ልቅ የሆነ ማንነት ስሜትን
ብቻ የሚከተል ማንነት ከዚህ አዙሪት ወጥተን በአስተሳሰባችን የምንልቅበት
በተመስጦ የምንፈካበት በማስተንተን የምንበለፅግበት ጊዜ ይመጣ ይሆን? ያ
ጊዜ እንዲመጣስ ምን ማድረግ ነው ያለብን?

@yehasab_menged
@yehasab_menged