Get Mystery Box with random crypto!

በእራስ መተማመን ከተነበበ በኀላ # share ይደረግ ለአንድ ግለሰብ ከሚያስፈልጉት መሠረታዊ የስነ | የሀሳብ መንገድ

በእራስ መተማመን
ከተነበበ በኀላ # share ይደረግ
ለአንድ ግለሰብ ከሚያስፈልጉት መሠረታዊ የስነ-ልቦና እሴቶች መካከል አንዱና
ዋነኛው በራስ መተማመን (self confidence) ነው፡፡ ብዙዎቻችን በራስ
መተማመናችን አነስተኛ ወይም ከነጭራሹ ባለመኖሩ ምክንያት ያጣናቸው ብዙ
ነገሮች አሉ፡፡
በራስ መተማመን ማለት ይለናል በራስ መተማመን ማለት ስለ ራሳችን ችሎታ
በቂ የሆነ እውቀት እና እምነት ኖሮን ከዚህ በመነሳት ደግሞ በግፊት እና በጫና
ውስጥ ስንሆን ጥሩ ውሳኔዎችን መስጠት ነው፡፡ በራስ መተማመን የራስ
እውቀት እና ክብር (self esteem) እና የራስን ችሎታን የማወቅና ውጤታማ
በሆነ መልኩ ነገርን እፈጽማለሁ ብሎ በራስ ላይ እመነት መጣል (self
efficacy) ድምር ውጤት ሲሆን፤ በራስ የሚተማመን ሰው መገለጫዎቹም……..
ስለ ነገ ሲያስብ መልካም መልካሙ ነው የሚታየው፣ በራሱ የሚተማመን ሰው
ምክንያታዊ በመሆን ምን ይመጣልን ከግምት ውጥ በማስገባት እና አደጋን
በመጋፈጥ (risk taker) ኢላማውን ለመምታት የሚታትር ነው ፣ በእራሱ
የሚተማመን ሰው እራሱን በትክክለኛ ደረጃ የሚወድ ነው….. ወዘተ በአንጻሩ
ደግሞ በራሱ የማይተማመን ሰው ደግሞ የሚሞክራቸው ነገሮች የሚሳኩለት
የማይመስሉት፣ ነገን ሲያስብ መጥፎው ብቻ እና ውድቀቱ ፈጥኖ የሚታየው፣
አቅሙን አሟጦ ለመጠቀም የሚፈራ ወዘተ… መገለጫዎች ያሉት ነው፡፡
ዛሬ በራስ መተማመናችን አነስተኛ ስለሆነ ስላጣናቸው ነገሮች ለማውራት
ሳይሆን የተነሳሁት እንዴት በራስ መተማመንን መገንባት እንችላለን ወይም ያለንን
አጠንክረን እንሄዳለን የሚለውን ለማየት ነው፡፡
ስለዚህ በራስ መተማመንን እንዴት መገንባት እንችላለን??
★የሚከተሉትን ነጥቦች እንያቸው
1.በራስ መተማመንህን የሚሸረሽሩ ሃሳቦችን ነቅሰህ አውጣ፡- በአዕምሮህ
ውስጥ ያሉትን አልችልም፣ አይሳካልኝም፣ እወድቃለሁ እና አይሆንልኝም የሚሉ
አሉታዊ ሃሳቦችን ለያቸው፡፡ እነዚህ ሃሳቦች የጨለምተኛነትን ዘር በውስጥህ
በመዝራት የራስ ዕውቀትህን በማሳነስ በእራስ መተማመንህን ይሸረሽሩታል፡፡
2.አሉታዊውን ሃሳቦች ወደ አዎንታዊ ቀይራቸው፡- ከላይ የተጠቀሱትን
አሉታዊውን ሃሳቦች ወደ ምክንያታዊ ወደ ሆኑ አዎንታዊ ሀሳቦች ቀይራቸው
ለምሳሌ እችላለሁ፣ እሞክረዋለሁ ፣ አሳካዋለሁ ወደ ሚሉ ሃሳቦች ቀይራቸው
እነዚህን እራስን የማበረታቻ እና ለራስ ዕውቅና መስጫ ሃሰቦች ቀስ በቀስ
አዳብራቸው፡፡
3.አዎንታዊ ሃሳቦችህን ትኩረት ስጣቸው፡- አዕምሮህ አሉታዊውን ሃሳቦች ብዙ
ትኩረት እንዳይሰጠቸው ለአዎንታዊው ሃሳቦች ሰፊ ቦታና ጊዜ ስጣቸው፡፡
ለማሳካት የምታልመው ን ጉዳይ ትኩረት በመስጠት ይህን ጉዳይ ወደ ትናኝሽ
ሃሳቦች በመቀየር ወደ ተግባር ግባ፡፡
4.ዙሪያህን በጥንቃቄ ቃኘው፡- በዙሪያህ ላሉ አዎንታዊ ሀሳቦችን እንድታስብና
መልካም ድርጊቶችን እንድታከናውን ለሚያደርጉህ እና ለሚያግዙህ ወዳጆችህ
ሰፊ ጊዜ ስጥ፣ በአንጻሩ ስለ ራስህ መጥፎ እንድታስብና ምቾት የማጣት ስሜት
እንዲሰማህ ከሚያደርጉ ሰዎች እና ድርጊቶች በተቻለህ መጠን እራቅ፡፡
5.ችሎታህን ለይተህ አውጣ፡- እያንዳንዱ ሰው ቢያንስ በአንድ ነገር ላይ ጎበዝ
ነው፡፡ ስለዚሀም አንተም ጎበዝ የሆንክበትን ወይም ብሰራው አሳካዋለሁ
የምትለውን ነገር ነቅሰህ በማውጣት ትኩረትህን ወደእዚህ አድርገው፡፡
6.በራስህ ኩራ፡- ባሉህ አዎንታዊ እና በጎ ጎኖች ምክንያት ተገቢ እና መጠነኛ
የሆነ ኩራትን ኩራ፡፡
7.ሁሌም ራስህን ሁን፡- አዳዲስ ሰዎችን ስትተዋወቅ ስለ እራስህ ውሸት
በመናገር ዕውቅናን ለማግኘት አትሞክር፡፡
በራስ መተማመን ሁሌም ሚዛናዊ ሊሆን የሚገባው እሴት ነው፡፡ ዝቅተኛ በራስ
መተማመን ያለው ሰው የሚመጣውን አስቀድሞ በመፍራት ነገሮችን ከመስራት
ወይም ከመሞከር ይቆጠባል አልያም ደግሞ ከመጠን ያለፈ እና ጥግ የያዘ
በራስ መተማመን ያለው ሰው የሚመጣውን ነገር ሁሉ እየሞከረ ራሱን አደጋ
ውስጥ ይከታል፡፡ ስለዚህ በራስ መተማመን ሁለቱን በአመክንዮአዊ ልኬት
ሚዛናዊ አድርጎ መጓዝን አብዝቶ ይጠይቃል፡፡
ሰላማችሁ ይብዛ……….
መልካም ቀን !

@yehasab_menged
@yehasab_menged