የሰርጥ አድራሻ:
ምድቦች:
ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች:
196.37K
የሰርጥ መግለጫ
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን 251913134524
Ratings & Reviews
Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.
5 stars
0
4 stars
1
3 stars
1
2 stars
0
1 stars
1
የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 269
2022-05-12 10:29:41
#EthiopianCoffee
የኢትዮጵያ ቡና በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ 1 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር የውጭ ምንዛሪ ማስገኘቱን የግብርና ሚኒስትር ኡመር ሁሴን ገልጸዋል።
@tikvahethmagazine
23.3K viewsedited 07:29
2022-05-12 10:09:20
#PowerOutage
በአዲስ አበባ ከተማ ለመካከለኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ተሸካሚ መስመሮች የማሻሻያ ስራ ለመስራት ለጥንቃቄ ሲባል አርብ ግንቦት 5 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 10፡00 ድረስ በለቡ ፣ በጆሞ አንድ በከፊል እና አካባቢዎቻቸው የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት እንደሚቋረጥ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል።
@tikvahethmagazine
23.3K viewsedited 07:09
2022-05-12 09:56:30
የአፋን ኦሮሞ እና የትግረኛ ቋንቋዎች በGoogle Translate ሥርዓት ውስጥ ተካተቱ።
የተለያዩ ቋንቋዎችን የሚተረጉመው Google Translate ተጨማሪ 24 ቋንቋዎችን ወደ ሥርዓቱ ማስገባቱን አስታውቋል። ከዚህ ውስጥም የአፋን ኦሮሞ እና የትግረኛ ቋንቋዎች መካተታቸው ተገልጿል።
አዲስ ከተካተቱት ቋንቋዎች ጋር ተደምሮ አገልግሎቱ 133 የዓለም ቋንቋዎችን መተርጎም ያስችለዋል ተብሏል። ከዚህ ቀደም የአማርኛ ቋንቋ በስርዓቱ ውስጥ ተካቶ አገልግሎት ላይ መዋሉ ይታወሳል።
ይህ የትርጉም አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ ትክክልኛ ትርጉም ባይሰጥም በተወሰነ ደረጃ የጹሑፎችን ሀሳብ ለመረዳትና ለመጠቀም ይሆናል።
ድርጅቱ ይህንን አገልግሎት ይፋ ያደረገው በትላንትናው ዕለት ሲሆን እስከ ሳምንቱ መጨረሻ ድረስ ለሁሉም ተጠቃሚዎች ተደራሽ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።
@tikvahethmagazine
21.7K viewsedited 06:56