Get Mystery Box with random crypto!

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

የቴሌግራም ቻናል አርማ ortodoxmezmur — ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit
የቴሌግራም ቻናል አርማ ortodoxmezmur — ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit
የሰርጥ አድራሻ: @ortodoxmezmur
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 135.77K
የሰርጥ መግለጫ

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ አሜን።
. ዝማሬ ዳዊት
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች, መዝሙራት እና ወረባትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ።
ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት
@zmaredawit_messengerbot ላይ
ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 12

2023-11-27 00:12:51 ​​እንኳን ለዓለም ሁሉ መምሕር ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ እና ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ማን ነው?

ነገዱ ከሶርያ: የተወለደው በ347 ዓ/ም በእስክንድርያ ሲሆን አባቱ አስፋኒዶስ እናቱ ደግሞ አትናስያ ይባላሉ:: እነርሱ ደግ ቢሆኑ ይህንን እንቁ ልጅ እግዚአብሔር ሰጣቸው:: ዮሐንስ ለክርስቲያን እንደሚገባ በትምሕርትና በጥበብ አደገ:: ገና በሕጻንነቱ ወደ ግሪክ ሔዶ የዘመኑን ሳይንስ (ፍልስፍና) ከአፉ እስከ ገደፉ ተምሮ ተመልሷል::

ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅን ለየት ከሚያደርጉት ነገሮችም አንዱ ይሔው ነው:: በዘመናዊም ሆነ በመንፈሳዊ ትምሕርት ይህ ቀረህ የማይሉት ሊቅ የሆነው ገና በ15 ዓመቱ ነበር:: በ2 ወገን የተሳለ ሰይፍ በመሆኑ ስንኩዋን በሕይወተ ሥጋ እያለ ዛሬም ለንፉቃን ትልቅ የራስ ምታት ነው::

ቅዱሱ ገና በ16 ዓመቱ ሃብት: ንብረት: ውበት: ክብርና እውቀት የሞላለት ቢሆንም ያለውን ሁሉ ለነዳያን ሰጥቶ መጻሕፍትን ብቻ ሰብስቦ ከባልንጀራው ቅዱስ ባስልዮስ ጋር በርሃ ገባ:: ሰውነቱን በጾምና በጸሎት እየቀጣ በበርሃ ሲኖር ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስና ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ዼጥሮስ ወደ እርሱ መጡ:: ሊቀ ሐዋርያት የመንግስተ ሰማያትን መክፈቻ ስልጣን ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌሉን ሰጥተው ተሰወሩት::

ከዚህች እለት በሁዋላ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ባሕረ ምስጢራት ሆነ:: ብሉይ ከሐዲስ: ከኦሪት ዘፍጥረት እስከ ራዕየ ዮሐንስ ድረስ በአንድምታ ትርጉዋሜ ተነተናቸው:: በተለይ ሐዲስ ኪዳንን እየመላለሰ አመሰጠረው:: ቅዱስ ሕሊናው ሳይታክት: ንጹሕ እጆቹ ሳይዝሉ የጻፋቸው ድርሳናት: መልዕክታትና ትርጉዋሜያት ቢቆጠሩ አሥር ሺህ ሞሉ:: በእውነት ለዚህ አንክሮ ይገባል የሚገርመው ይህን ሁሉ ሲሰራ እድሜው ገና ለጋ: ማዕርጉም ዲቁና ነበር::

ከዚህ በሁዋላ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ቅስና ተሹሞ በስብከተ ወንጌል ብዙ ቦታዎችን አዳረሰ:: በቅድስናው ወደውታልና የቁስጥንጥንያ ፓትርያርክ አድርገው ሾሙት:: አፈ ወርቅ ሲናገርም ሆነ ሲያስተምር እንኩዋን የሚያወራ ኮሽ የሚል የለም:: ከጣዕመ ትምሕርቱ የተነሳ ሕዝቡ በተደሞ ይሰሙት ነበር:: ሲያስተምር ምድራዊው ሰው ይቅርና ልዑላኑ መላእክት ተሰብስበው ያደንቁት ነበር:: አንዴም እመቤታችን በሕዝብ መካከል አፈ ወርቅ ብላ ጠርታዋለች:: ለዛም ነው አፈ ወርቅ የሚባለው:: ቅዱሱ በሥልጣነ ቃሉ መልዐከ ሞትን ገስፆ 10 ዓመት አቁሞታል::

ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ለሰው ፊት አያደላም:: በርሱ ዘንድ ንጉሥና ደሃ ነዳይ እኩል ነው:: ለሞት ያበቃውም ይሔው ነበር:: ምክንያቱም የወቅቱ ንግስት አውዶክስያ ያንዲት ድሃ መበለትን መሬት ቀምታ አልመልስም በማለቷ መክሮ አወገዛት:: እርሷ ግን ከኃጥአንና መናፍቃን ጋር መክራ 2 ጊዜ አጋዘችው:: በተሰደደበት ሃገር ፍሬ አፍርቶ: አስተምሮና አሳምኖ በ407 ዓ/ም አርፏል:: ቤተ ክርስቲያንና ምእመናን ሳይጠግቡት እንደናፈቁት በ60 ዓመቱ አጡት:: በወቅቱ ታላቅ ሐዘንና ለቅሶ ተደረገ::

አንድ ቀን የዘመኑ ደግ ንጉሥ አርቃድዮስ ግብር አገባ:: (ግብዣ አዘጋጀ) በዚያች ሌሊት ደግሞ ቅዱሱ ሊቅ ታጥቆ ሲጸልይ ሳለ: አባ ማርዳሪ የሚባል ጻድቅ ደግሞ 12ቱ ሊቃነ መላእክት (እነ ቅዱስ ሚካኤል) ከሰማይ በግርማ ሲወርዱ ተመለከተ::

ደንግጦ "ወዴት ናችሁ ጌቶቼ" ቢላቸው "ቁስጥንጥንያ: ወደ ዮሐንስ አፈ ወርቅ እንሔዳለን:: እርሱ እመቤታችንን እንደሚያመሰግናት ጌታ ነግሮናልና" አሉት:: "እባካችሁ እኔም የአፈ ወርቅ ምስጋናው እንዲገለጥልኝ መርቁኝ" አላቸው:: ሊቃነ መላእክቱም መርቀውት ጐዳናቸውን ቀጠሉ::

በማግስቱ በቤተ መንግስት ውስጥ ሊቃውንቱ: መሳፍንቱ: ዻዻሳቱ: ሕዝቡ ሁሉ ተሰብስበው ከድግሱ በሉ:: ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ግን በመንበሩ ተቀምጦ ነበር እንጂ አልበላም:: ድግሱ ሲጠናቀቅ ንጉሡ አርቃድዮስ ሊቁን "ጥያቄ አለኝ" ብሎ በጉባኤ መካከል ጠየቀው::

"ምነው ወንጌላዊ ማቴዎስ 'ኢያዕመራ ዮሴፍ እስከ አመ ወለደት ወለደ ዘበኩራ - የበኩር ልጇን እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም' ማለቱ (ማቴ. 1:25) ስለ ምን ነው?" ቢለው ቅዱሱ ተነስቶ: በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ ይተረጉምለት ጀመር::

"ድንግል ማርያም ንጹሕ ብርሌን ትመስላለች:: ብርሌ የተለያየ ቀለም ያለው ፈሳሽ ቢያስገቡበት ቀለሙ አብሮ ይቀያየራል:: እመቤታችንም ጌታን ጸንሳለችና ሕብረ መለኮቱ ሲለዋወጥ መልኩዋ አብሮ ሲለዋወጥ እያየ ዮሴፍ ይደነግጥ ነበር::

'እርሷ ማን ናት? በማሕጸኗ ያለውስ ማን ነው?' እያለ ይጨነቅ ነበር:: ጌታን ከወለደች በሁዋላ ግን አንድ ሕብረ መልክ ሆናለችና:: አስቀድሞ ማን እንደ ነበረች አላወቀም::

አሁን ግን እርሷም ወላዲተ አምላክ: ልጇም አምላክ ዘበአማን መሆኗን አወቀ ማለት ነው" እያለ ሲተረጉም ሰምተው ሁሉም ሲያደንቁ: በዚያ የነበረች ስዕለ አድኅኖ "አፈ ወርቅ! ልሳነ ወርቅ! አፈ በረከት!" ስትል ተናገረች::

ያን ጊዜ አርቃድዮስ የወርቅ ልሳን በሊቁና በስዕሏ ላይ አደረገ:: አፈ ወርቅ ግን ባጭር ታጥቆ "እሰግድ ለኪ! እሰግድ ለኪ! ወእዌድሰኪ . . ." ብሎ ዛሬ በተአምረ ማርያም የምናውቀውን ምስጋና ሰተት አድርጐ አደረሰላት:: ይህንን ምስጋናም ሊቃነ መላእክቱ ሰምተው እያደነቁ ወደ ሰማይ ወጥተዋል::

ሊቁ ባረፈ በ35 ዓመቱ በትንሹ ቴዎዶስዮስ ዘመን: በዚህ ቀን ሥጋው ፈልሷል:: ወደ ቁስጥንጥንያ ሲደርስም ከናፍቆት የተነሳ ታላቅ ዝማሬና እንባ ተደርጉዋል:: አፈ ወርቅም ቀና ብሎ ሕዝቡን ባርኩዋል::

ቅዱሱ ሲጠራ እንዲሕ ነው:-
- ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
- አፈ በረከት
- አፈ መዐር (ማር)
- አፈ ሶከር (ስኩዋር)
- አፈ አፈው (ሽቱ)
- ልሳነ ወርቅ
- የዓለም ሁሉ መምሕር
- ርዕሰ ሊቃውንት
- ዓምደ ብርሃን (የብርሃን ምሰሶ)
- ሐዲስ ዳንኤል
- ሊቀ ዻዻሳት ዘበርትዕ (እውነተኛው)
- መምሕር ወመገስጽ ዘኢያደሉ ለገጽ
- ጥዑመ ቃል

አምላከ ቅዱሳን ከቅዱሱ ረድኤት በረከት አይለየን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር።

ለሁሉም ኦርቶዶክሳዊ ሼር አድርጉ
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
15.6K views21:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-26 22:37:43
በኦርቶዶክሳዊ ዲዛይነሮች ተውበው የተሰሩ የጥምቀት ቲሸርቶችን ለማየት እና ለማዘዝ የስር ያለውን የቴሌግራም ሊንክ ይጠቀሙ።
https://t.me/KABAPrint
https://t.me/KABAPrint

ማሳሰቢያ - በምታዙበት ወቅት ለምትከፍሉት የቀብድ ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ሀላፊነቱን እኛ እንወስዳለን። አንዳንድ ጥያቄዎች እየደረሱን ስለሆነ ነው።

ለበለጠ መረጃ
0965875219
0922501999
0913655116
13.9K views19:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-26 22:22:36 ስርዐተ ቅዳሴ

፨ በአማርኛ ፣ በግእዝ እና በ እንግሊዝኛ
፨ አዘጋጅ @Ortodoxmezmur
፨ መጠን 1.7 MB

አቅራቢ @Ortodoxmezmur
12.7K viewsJoseph , edited  19:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-26 21:43:18 ሰላም ውድ ኦርቶዶክሳዊያን የዝማሬ ዳዊት ተከታታዮች? እንኳን ለእናታችን ቅድስት ኪዳነምህረት ወርሀዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

ባለፈው ባልናችሁ መሰረት ብዙዎቻችሁ ፈቃዳችሁን እና ፍላጎታችሁን በማየት ቻሌንጁን ከነገ ማለትም ከሰኞ እንጀምራለን። ምናልባት በአጋጣሚ ይህንን መልዕክት ዛሬ ያላያችሁ ካላችሁ ደግሞ ከማክሰኞ ትጀምራላችሁ።

እንደ እግዚአብሔር ቸርነት እና ፈቃድ በዚህ በጾመ ነቢያት መንፈሳዊ ሕይወታችንን ሊለውጡ የሚችሉ 3 መሰረታዊ ቻሌንጆችን እንከውናለን። ሁላችንም የዚህ ተሳታፊ መሆን ይጠበቅብናል። የዚህ ቻሌንጅ ዓላማ መንፈሳዊ ሕይታችንን መለወጥ እንደመሆኑ ሁላችንም በፍጹም ትህትና ለራሳችን ቃል በመግባት ሳናቋርጥ ልንፈጽመው ይገባል።

ቻሌንጅ አንድ
በቅዱስ ሲኖዶስ እንደታዘዝነው አባቶቻችንም እንዳሉን እስከ ሕዳር 21 ድረስ የቻልን ጠዋት ካልሆነ ደግሞ በሰርክ ጉባኤ ላይ ተገኝተን ጸሎተ ምህላ ማድረስ።

ቻሌንጅ ሁለት
የክርስቲያኖች ሕይወት ከሚለወጥበት አንዱ መንገድ መካከል ገድለ ቅዱሳን ነው። በዚህም መሰረት ዝማሬ ዳዊት ከነገ ሰኞ ጀምሮ እስከ አርብ ጾሙ እስኪፈጸም ድረስ በዕለቱ ከሚከበሩ አንድ ቅዱስ በመምረጥ ጠዋት ለእናንተ አጠር ባለ መልኩ ያቀርባል።

ተማሪ የሆንን ከትምህርታችን በፊት ሰራተኛም የሆንን ከስራችን አስቀድመን የምንለቅላችሁን የቅዱሳን ሕይወት በጠዋት ማንበብ ይጠበቅብናል። ይህም ቀናችን ብሩክ እንዲሆን መልካም ሀሳብ በአይምሮአችን እንዲመላ ያደርጋል።

በዚህም መሰረት ዘወትር ቅዳሜ ምሽት ጥያቄዎች እናዘጋጃለን። ጥያቄዎቹም የሚወጡት ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ በምንለቅላችሁ የቅዱሳን ታሪክ ላይ ተመርኩዞ ይሆናል።

ቻሌንጅ ሦስት
በዚህ በጾመ ነቢያት ሁላችንም የቅዳሴ ተሳታፊ እንሆናለን። በዚህም መሰረት የቻልን ቅዳሜ እና እሁድ በለሊት ቅጽረ ቤተ ክርስቲያን በመገኘት እናስቀድሳለን። ይህንን የማንችል ደግሞ ሰንበተ ክርስያን በሆነችው እሁድ እናስቀድሳለን። ታድያ ቅዳሴ ከመጀመሩ በፊት በመገኘት ሙሉ ስርዐተ ቅዳሴ ተካፋይ መሆን ይጠበቅብናል። እሁድንም ማስቀደስ የማንችል ግን ቢያንስ ስርዓተ ቅዳሴ ከመጀመሩ በፊት ተገኝተን ኪዳን ማድረስ ይኖርብናል።

እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ከነገ ጀምሮ ከላይ የዘረዘርናቸውን ሦስት ቻሌንጆች እንጀምራለን። እግዚአብሔር አምላክ ሀሳባችንን ከፍጻሜ ይድረስልን። ሀገራችን ኢትዮጵያን ዳሯን እሳት መኃሏን ገነት አድርጎ ይጠብቅልን። አሜን!!!

ቻሌንጃችንን ለመፈጸም የምንለቅላችሁን ነገሮች በሙሉ ይደርሳችሁ ዘንድ ቻናላችንን PIN እንድታደርጉት በትህትና እንጠይቃለን።

@Ortodoxmezmur
ለሁሉም ኦርቶዶክሳዊ በሙሉ ሼር አድርጉ የቻሌንጁ ተሳታፊ ይሆኑ ዘንድ።
14.6K viewsJoseph , edited  18:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-26 14:32:01 #የልቤን_በልቤ_ይዤ

የልቤን በልቤ ይዤ ከፊትሽ ቆሜአለው
የሆዴን በሆዴ ይዤ ከፊትሽ ቆሜአለው
ካለኝ ነገር ሁሉ አንቺን መርጫለሁ
እናቴ ሆይ ስሚኝ አማልጅኝ እላለሁ

ግራኝ ቀኝ ህይወቴ በሾህ ታጥሮብኛል
በፊት በኋላዬ መሰናክል በዝቷል
እኔስ ያለ ምርኩዝ ጉዞዬ ከብዶኛል
እመ አምላክ ደግፊኝ እጄ ተዘርግቷል(2)
#አዝ
ቆሜ ስራመድ ጤነኛ እመስላለሁ
የውስጤን ጎዶሎ እኔ አውቃለሁ
ድንግል ሆይ ቅረቢኝ አይዞህ ልጄ በይኝ
የጭንቀቴን ካባ አውልቀሽ ጣይልኝ(2)
#አዝ
እናት ያለው ሰው ፍጹም አይተክዝም
አንድ ቀን ይስቃል አልቅሶም አይቀርም
ሀዘኔን በደስታ ለውጪው እናቴ
በደስታ ልዘምር በቀረው ሕይወቴ(2)
#አዝ
አሁን ጎዶሎ በውስጤ አለና
ድንግል ሆይ ቅረቢኝ ዛሬም እንደገና
ለዚች ለትንሿ ለጥቂቷ እድሜ
እንደከፋኝ አልኑር ቀና አርጊኝ እናቴ(2)

@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
12.9K viewsJoseph , 11:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-24 22:34:56 ውድ የዝማሬ ዳዊት ቤተሰቦች እንኳን ለጾመ ነቢያት በሰላም አደረሳችሁ? ጾሙን በማስመልከት ኦርቶዶክሳዊ እና የመንፈሳዊ ሕይወታችንን የሚያጠነክር አንድ ቻሌንጅ የዝማሬ ዳዊት አዘጋጆች ለእናንተ አዘጋጅተን የእናንተን ፈቃደኝነት እየጠበቅን ነው! ፈቃዳችሁን አሳዩን እሱን ተመልክተን ዝርዝር ሀሳቡን ነገ ወደ እናንተ ይዘን እንቀርባለን።

እግዚአብሔር አምላክ ጾማችንን ይቀበልልን! ጾሙ ሰይጣንን ድል መንሻ መንግስቱን መውረሻ ያድርግልን። አሜን
15.0K viewsJoseph , edited  19:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-24 17:29:59 ​​ጾመ ነቢያት (የገና ጾም)
ኅዳር ፲፭ ቀን

ጾመ ነቢያት በየዓመቱ ከኅዳር ፲፭ ቀን ጀምሮ እስከ በዓለ ልደት ዋዜማ ድረስ የሚጾም፤ ከሰባቱ አጽዋማት መካከል አንደኛው ጾም ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ዓለምን ለማዳን ሲል የሰውን ሥጋ ስለ መልበሱ፤ ወደ ግብጽ ስለ መሰደዱ፤ በባሕረ ዮርዳኖስ ስለ መጠመቁ፤ በትምህርቱ ብርሃንነት ጨለማውን ዓለም ስለ ማብራቱ፤ ለሰው ልጆች ድኅነት ልዩ ልዩ መከራን ስለ መቀበሉ፤ ስለ መሰቀሉ፣ ስለ ሞቱ፣ ትንሣኤው፣ ዕርገቱና ዳግም ምጽአቱ በየዘመናቱ የተነሡ ቅዱሳን ነቢያት በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው ትንቢት ተናግረዋል፤ ትንቢቱ ደርሶ፣ ተፈጽሞ ለመመልከትም ‹‹አንሥእ ኃይለከ ፈኑ እዴከ፤ ኃይልህን አንሣ፤ እጅህን ላክ›› እያሉ በጾም በጸሎት ተወስነው አምላክ ሰው የሚኾንበትን ጊዜ በቀናት፣ በሳምንታት፣ በወራትና በዓመታት እያሰሉ ሲጠባበቁ ቆይተዋል፡፡

ይህ ጾም የእግዚአብሔርን ሰው መኾን ሲጠባበቁ የኖሩት የነቢያት ትንቢትና ጸሎት በጌታችን መወለድ ፍጻሜ ያገኘበት ወቅት በመኾኑ ‹‹ጾመ ነቢያት (የነቢያት ጾም)›› እየተባለ ይጠራል፡፡ ለአዳም የተነገረው የድኅት ተስፋ ስለ ተፈጸመበትም ‹‹ጾመ አዳም (የአዳም ጾም)›› ይባላል፡፡

ስለ እግዚአብሔር ሰው መኾን በስፋት ትምህርተ ወንጌል የሚሰጥበት ወቅት በመኾኑም ‹‹ጾመ ስብከት (የስብከት ጾም)››፤ የጾሙ መጨረሻ (መፍቻ) በዓለ ልደት በመኾኑ ደግሞ ‹‹ጾመ ልደት (የልደት ጾም)›› በመባል ይታወቃል፡፡

እንደዚሁም ‹‹ጾመ ሐዋርያት›› ይባላል። ቅዱሳን ሐዋርያት ‹‹በዓለ ትንሣኤን ዐቢይ ጾምን ጾመን እናከብረዋለን፤ በዓለ ልደትንስ ምን አድርገን እናከብረዋለን? ›› በማለት ነቢያት የጾሙትን ከልደተ ክርሰቶስ በፊት ያለውን ጾም ጾመዋልና፡፡

በተመሳሳይ መልኩ ይህ ጾም ‹‹ጾመ ፊልጶስ (የፊልጶስ ጾም)›› ተብሎ ይጠራል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ፊልጶስ በአፍራቅያና አውራጃዋ ዅሉ እየተዘዋወረ በጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ወንጌልን በማስተማር፣ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን በማድረግ ብዙዎችን ወደ አሚነ እግዚአብሔር ሲመልስ ቆይቶ ትምህርቱን በማይቀበሉ የአፍራቅያ ሰዎች አማካይነት በሰማዕትነት ዐርፏል፡፡

ደቀ መዛሙርቱ ሥጋውን ሊቀብሩ ሲሉም ስለ ተሰወረባቸው የሐዋርያውን ሥጋ ይመልስላቸው ዘንድ ሱባዔ ይዘው፣ በጾም በጸሎት ተወስነው በለመኑት ጊዜ እግዚአብሔር ልመናቸውን ተቀብሎ በ፫ኛው ቀን መልሶላቸው ሥጋውን (አስከሬኑን) በክብር አሳርፈውታል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ የሐዋርያውን ሥጋ ካገኙ በኋላ እስከ ጌታችን ልደት ድረስ ጾመዋል፡፡ ስለዚህም ጾመ ነቢያት ‹‹ጾመ ፊልጶስ›› እየተባለ ይጠራል፡፡

ከዚሁ ዅሉ ጋርም ወልደ አምላክ ክርስቶስን በግብረ መንፈስ ቅዱስ እንደምትፀንሰው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ካበሠራት በኋላ እመቤታችን ‹‹ሰማይና ምድር የማይወስኑትን አምላክ ፀንሼ ምን ሠርቼ እወልደዋለሁ?›› በማለት ጌታችንን ከመውለዷ አስቀድማ ጾማዋለችና ይህ ጾም ‹‹ጾመ ማርያም›› በመባልም: ይታወቃል፡፡

በአጠቃላይ በዚህ በገና ጾም ነቢያትም ሐዋርያትም ጾመው በረከት አግኝተውበታል፡፡ እኛ ምእመናንም እንደ እነርሱ በረከትን እናገኝ ዘንድ ይህንን ጾም መጾም እንደሚገባን የቤተ ክርስቲያን አባቶች ሥርዐት ሠርተውልናል፡፡

በዚህም መሠረት የነቢያት፣ የሐዋርያት፣ የጻድቃንና የሰማዕታት አምላክ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ከቅዱሳን ነቢያትና ሐዋርያት በረከት እንዲያሳትፈን፤ መንግሥቱንም እንዲያወርሰን ዅላችንም በዚህ በጾመ ነቢያት ወቅት በጾም በጸሎት ተወስነን እግዚአብሔርን ልንማጸነው ይገባል፡፡

ምንጭ፡- ፍትሐ ነገሥት ንባቡና ትርጓሜው፣ አንቀጽ ፲፭፡፡
ጾምና ምጽዋት፣ ዲያቆን ቃኘው ወልዴ፤ ገጽ ፵፯ -፶፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
18.9K viewsJoseph , 14:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-24 07:18:26 ጾመ ነቢያት /የገና ጾም/ የሚጀምረው ቅዳሜ ነው።
16.3K views04:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-23 21:08:22
ይህ ከላይ የላክንላችሁን ለሁሉም እህት ወንድሞቻችን እንድትልኩላቸው በፍጹሕ ትህትና በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።
13.0K views18:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-23 21:04:08 የተወደድከው ወንድሜ
የተወደድሽው እህቴ
ዛሬ የእግዚአብሔርን ቃል የምታገኝበትን ኦርቶዶክሳዊ ቻናል እንድትከታተል ልጋብዝህ ነው
የመጣሁት።

በእዚህ ቻናል
ዝማሬዎች
ቃለ እግዚአብሔር
የቅዳሴ ትምህርት በቀላሉ ለመማር
የተለያዩ መንፈሳዊ መጽሐፍት ማግኘት ከፈለጋችሁ እና
የተለያዩ ጽሑፍ እና ፎቶዎች ከፈለጋችሁ እዚህ ታገኛላችሁ።

ይሄንን ቻናል ከተቀላቀልኩ ጀምሮ መንፈሳዊ ሕይወቴን እንዲያድግ ረድቶኛል አንተም/ቺም አሁን በመቀላቀል ትጠቀሙበት ዘንድ እለምናለሁ።

https://t.me/+pTxbeTxPagA3OGNk
13.3K views18:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ