Get Mystery Box with random crypto!

#የልቤን_በልቤ_ይዤ የልቤን በልቤ ይዤ ከፊትሽ ቆሜአለው የሆዴን በሆዴ ይዤ ከፊትሽ ቆሜአለው ካለ | ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

#የልቤን_በልቤ_ይዤ

የልቤን በልቤ ይዤ ከፊትሽ ቆሜአለው
የሆዴን በሆዴ ይዤ ከፊትሽ ቆሜአለው
ካለኝ ነገር ሁሉ አንቺን መርጫለሁ
እናቴ ሆይ ስሚኝ አማልጅኝ እላለሁ

ግራኝ ቀኝ ህይወቴ በሾህ ታጥሮብኛል
በፊት በኋላዬ መሰናክል በዝቷል
እኔስ ያለ ምርኩዝ ጉዞዬ ከብዶኛል
እመ አምላክ ደግፊኝ እጄ ተዘርግቷል(2)
#አዝ
ቆሜ ስራመድ ጤነኛ እመስላለሁ
የውስጤን ጎዶሎ እኔ አውቃለሁ
ድንግል ሆይ ቅረቢኝ አይዞህ ልጄ በይኝ
የጭንቀቴን ካባ አውልቀሽ ጣይልኝ(2)
#አዝ
እናት ያለው ሰው ፍጹም አይተክዝም
አንድ ቀን ይስቃል አልቅሶም አይቀርም
ሀዘኔን በደስታ ለውጪው እናቴ
በደስታ ልዘምር በቀረው ሕይወቴ(2)
#አዝ
አሁን ጎዶሎ በውስጤ አለና
ድንግል ሆይ ቅረቢኝ ዛሬም እንደገና
ለዚች ለትንሿ ለጥቂቷ እድሜ
እንደከፋኝ አልኑር ቀና አርጊኝ እናቴ(2)

@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur