Get Mystery Box with random crypto!

ሰላም ውድ ኦርቶዶክሳዊያን የዝማሬ ዳዊት ተከታታዮች? እንኳን ለእናታችን ቅድስት ኪዳነምህረት ወርሀ | ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

ሰላም ውድ ኦርቶዶክሳዊያን የዝማሬ ዳዊት ተከታታዮች? እንኳን ለእናታችን ቅድስት ኪዳነምህረት ወርሀዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

ባለፈው ባልናችሁ መሰረት ብዙዎቻችሁ ፈቃዳችሁን እና ፍላጎታችሁን በማየት ቻሌንጁን ከነገ ማለትም ከሰኞ እንጀምራለን። ምናልባት በአጋጣሚ ይህንን መልዕክት ዛሬ ያላያችሁ ካላችሁ ደግሞ ከማክሰኞ ትጀምራላችሁ።

እንደ እግዚአብሔር ቸርነት እና ፈቃድ በዚህ በጾመ ነቢያት መንፈሳዊ ሕይወታችንን ሊለውጡ የሚችሉ 3 መሰረታዊ ቻሌንጆችን እንከውናለን። ሁላችንም የዚህ ተሳታፊ መሆን ይጠበቅብናል። የዚህ ቻሌንጅ ዓላማ መንፈሳዊ ሕይታችንን መለወጥ እንደመሆኑ ሁላችንም በፍጹም ትህትና ለራሳችን ቃል በመግባት ሳናቋርጥ ልንፈጽመው ይገባል።

ቻሌንጅ አንድ
በቅዱስ ሲኖዶስ እንደታዘዝነው አባቶቻችንም እንዳሉን እስከ ሕዳር 21 ድረስ የቻልን ጠዋት ካልሆነ ደግሞ በሰርክ ጉባኤ ላይ ተገኝተን ጸሎተ ምህላ ማድረስ።

ቻሌንጅ ሁለት
የክርስቲያኖች ሕይወት ከሚለወጥበት አንዱ መንገድ መካከል ገድለ ቅዱሳን ነው። በዚህም መሰረት ዝማሬ ዳዊት ከነገ ሰኞ ጀምሮ እስከ አርብ ጾሙ እስኪፈጸም ድረስ በዕለቱ ከሚከበሩ አንድ ቅዱስ በመምረጥ ጠዋት ለእናንተ አጠር ባለ መልኩ ያቀርባል።

ተማሪ የሆንን ከትምህርታችን በፊት ሰራተኛም የሆንን ከስራችን አስቀድመን የምንለቅላችሁን የቅዱሳን ሕይወት በጠዋት ማንበብ ይጠበቅብናል። ይህም ቀናችን ብሩክ እንዲሆን መልካም ሀሳብ በአይምሮአችን እንዲመላ ያደርጋል።

በዚህም መሰረት ዘወትር ቅዳሜ ምሽት ጥያቄዎች እናዘጋጃለን። ጥያቄዎቹም የሚወጡት ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ በምንለቅላችሁ የቅዱሳን ታሪክ ላይ ተመርኩዞ ይሆናል።

ቻሌንጅ ሦስት
በዚህ በጾመ ነቢያት ሁላችንም የቅዳሴ ተሳታፊ እንሆናለን። በዚህም መሰረት የቻልን ቅዳሜ እና እሁድ በለሊት ቅጽረ ቤተ ክርስቲያን በመገኘት እናስቀድሳለን። ይህንን የማንችል ደግሞ ሰንበተ ክርስያን በሆነችው እሁድ እናስቀድሳለን። ታድያ ቅዳሴ ከመጀመሩ በፊት በመገኘት ሙሉ ስርዐተ ቅዳሴ ተካፋይ መሆን ይጠበቅብናል። እሁድንም ማስቀደስ የማንችል ግን ቢያንስ ስርዓተ ቅዳሴ ከመጀመሩ በፊት ተገኝተን ኪዳን ማድረስ ይኖርብናል።

እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ከነገ ጀምሮ ከላይ የዘረዘርናቸውን ሦስት ቻሌንጆች እንጀምራለን። እግዚአብሔር አምላክ ሀሳባችንን ከፍጻሜ ይድረስልን። ሀገራችን ኢትዮጵያን ዳሯን እሳት መኃሏን ገነት አድርጎ ይጠብቅልን። አሜን!!!

ቻሌንጃችንን ለመፈጸም የምንለቅላችሁን ነገሮች በሙሉ ይደርሳችሁ ዘንድ ቻናላችንን PIN እንድታደርጉት በትህትና እንጠይቃለን።

@Ortodoxmezmur
ለሁሉም ኦርቶዶክሳዊ በሙሉ ሼር አድርጉ የቻሌንጁ ተሳታፊ ይሆኑ ዘንድ።