Get Mystery Box with random crypto!

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

የቴሌግራም ቻናል አርማ ortodoxmezmur — ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit
የቴሌግራም ቻናል አርማ ortodoxmezmur — ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit
የሰርጥ አድራሻ: @ortodoxmezmur
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 135.77K
የሰርጥ መግለጫ

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ አሜን።
. ዝማሬ ዳዊት
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች, መዝሙራት እና ወረባትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ።
ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት
@zmaredawit_messengerbot ላይ
ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 11

2023-12-03 20:11:42
እነዚህን ውብ ቲሸርቶች ተመልከቱ!

በ2016 ዓ.ም በጥምቀት ቀን መላው ሃገሪቱን ያጥለቀልቁታል ከተባሉት እና በብዙዎች ከተወደዱት ቲሸርቶች መካከል እነዚህ ጥቂቶቹ ናቸው።

ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በእነዚህ ክፍለ ሃገር ላላችሁ
ጅማ ሊሙ
አዳማ ዝዋይ (ባቱ)
ቦንጋ ወሊሶ
አሰላ ሃዋሳ
ሻሸመኔ ሆለታ
አንቦ ሆሳዕና
ወላይታ ሶዶ ድሬድዋ
ሀረር ጂግጂጋ
ወልቂጤ ደብረ ብርሃን
ወሊሶ

ከኛ ተረክባችሁ ማከፋፈልበማህበርም ሆነ በግል ማዘዝ ከፈለጋችሁ ከላይ በተጠቀሱት ቦታዎች በሙሉ ያሉበት ድረስ የምናደርስ ይሆናል።

ሌሎቹንም በኦርቶዶክሳዊ ዲዛይነሮች ተውበው የተሰሩ የጥምቀት ቲሸርቶችን ለማየት እና ለማዘዝ የስር ያለውን የቴሌግራም ሊንክ ይጠቀሙ።
https://t.me/KABAPrint
https://t.me/KABAPrint

ማሳሰቢያ - በምታዙበት ወቅት ለምትከፍሉት የቀብድ ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ሀላፊነቱን እኛ እንወስዳለን። አንዳንድ ጥያቄዎች እየደረሱን ስለሆነ ነው።

   ለበለጠ መረጃ
0965875219
0922501999
0913655116
13.7K views17:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-01 21:57:23 እንደምታውቁት መንፈሳዊ ቻሌንጅ ከጀመርን ዛሬ አምስተኛ ቀናችን ነው። ከቻሌንጃችን መካከል 3ኛው ቻሌንጅ ምን ነበር? እስቲ ሁላችሁም መልሱ! ቻሌንጁን ለራሳችሁ ቃል በገባችሁት መሰረት ተግባራዊስ እያደረጋችሁ ነው?
12.6K views18:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-01 19:44:55 ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን

ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን 
ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን
ውስተ አፍላገ ባቢሎን
ህየ ነበርነ ወበከይነ
እንዚራቲነ ሰቀልነ ውስተ ኲሓቲሃ

ባሰብናት ጊዜ ጽዮንን
ባሰብናት ጊዜ ጽዮንን
በባቢሎን ወንዞች አጠገብ
ተቀምጠን አለቀስን
መሰንቆአችንን ሰቀልን በዛፎቿ ላይ
አዝ
ፅኑ መከራን ተቀበልን ተጨነቅን በፈተና
የደዌ ሞት በላያችን እንደዝናብ ወርዷልና
አሕዛብም ዘበቱብን እንዲህ ብለው በየተራ
ዘምሩለት ለአምላካችሁ ቢያድናችሁ ከመከራ

እግዚአብሔር ጽዮንን በመንግስቱ መርጧታል እና
ማደሪያው ትሆነው ዘንድ ወዷታል እና
ጽዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
ጽዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
አንቺን ብንረሳ ቀኛችን ትርሳን
አዝ
የማረኩን በጦራቸው በኃይላቸው የተመኩ
በጽዮን ደጅ ያለፍርሃት የጽዮንን ክብሯን ነኩ
ይህን ያየ ከላይ ሆኖ በደመና ተሸፍኖ
ባቢሎንን አሻገረ የማረኩንን በትኖ

እግዚአብሔር ጽዮንን በመንግስቱ መርጧታል እና
ማደሪያው ትሆነው ዘንድ ወዷታል እና
ጽዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
ጽዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
አንቺን ብንረሳ ቀኛችን ትርሳን
አዝ
ስጋችንን ሊገንዘን የሞት ጥላ ቢያጠላም
እናልፋለን ሁሉን ባንቺ
የአምላክ እናት ድንግል ማርያም
ቅድስት ሆይ ከባረክሽን
እንድናለን ከደዌያችን
ለስጋና ለነብሳችን መድኃኒት ነሽ እናታችን

እግዚአብሔር ጽዮንን በመንግስቱ መርጧታልና
ማደሪያው ትሆነው ዘንድ ወዷታልና
ጽዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
ጽዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
አንቺን ብንረሳ ቀኛችን ትርሳን

@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
13.3K views16:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-30 22:24:04 ሕዳር 21/03/2016 ዓ.ም
የሕዳር ጽዮን ማርያም

በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ።

ዲያቆን፦ 2ቆሮ 7÷12-ፍ.ም
ንፍቅ ዲያቆን፦ 1ጴጥ 2÷5-11
ንፍቅ ካህን፦ ግብረ ሐዋርያት፦ 7÷44-59

ምስባክ ፦ መዝ 131÷13-15
እስመ ሐረያ እግዚአብሔር ለጽዮን
ወአብደራ ከመትኩኖ ማህደሮ
ዛቲ ይእቲ ምዕራፍየ ለዓለም

ትርጉም
እግዚአብሔር ጽዮንን መርጧታልና
ማደርያውም ትሆነው ዘንድ
ወዷታልና እንዲህም ብሎ
ይህች የዘለዓለም ማረፊያዬ ናት

ወንጌል ፦ ማቴ 21÷42-ፍ.ም
ቅዳሴ ፦ ዘእግዝእትነ

@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
15.4K viewsedited  19:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-30 20:44:57 ​​እንኳን ለጽዮን "ማርያም ማሕደረ አምላክ" እና ለቅዱሳኑ "ጐርጐርዮስ ወዮሐንስ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ

"ጽዮን ማርያም"

"ጽዮን" ማለት "ጸወን - አምባ - መጠጊያ" ማለት ነው:: አንድም በምሥጢሩ "ማሕደረ አምላክ" ማለት ነው:: ጽዮን የሚለው ስም በቁሙ ለቅዱስ ዳዊት ተራራና ለኪዳኑ ጽላት ሲያገለግል በትንቢታዊ ምሥጢሩ ግን ለድንግል ማርያም: ለቤተ ክርስቲያንና ለዘለዓለማዊት ርስት ያገለግላል::

እግዚአብሔር ከዘመነ አበው በሁዋላ በጊዜው ለእሥራኤላውያን ክብር: ሞገስ: አምባ የምትሆናቸውን ታቦተ ጽዮንን በቅዱስ ሙሴ አማካኝነት ሰጥቷቸዋል:: (ዘጸ. 31:18) ከዚያም ለ500 ዓመታት ከእነሱ ጋር በመሆኗ በፈጣሪና በእነሱ መካከል ድልድይ ሆና ኖራለች::

ከዚያም ባለቤቱ ሲፈቅድ በዘመነ ሳባ: በቀዳማዊ ምኒልክ (እብነ መለክ-እብነ ሐኪም) አማካኝነት ወደ ኢትዮዽያ መጥታለች:: እነሆ በሃገራችን የ3ሺ ዓመት ቆይታዋን ልትደፍን የቀራት ጥቂት ዓመታት ብቻ ናቸው:: ጌታ እንደ ፈቀደ ቅዱስ መስቀሉንና ታቦተ ጽዮንን ይዘን ይሔው በቸርነቱ እንኖራለን::

ያም ሆኖ ታቦተ ጽዮንን መስረቅ የሚፈልጉ ብዙ ቀሳጢዎች እንዳሉ እናውቃለን:: ግን አንጨነቅም:: ምክንያቱም የመጣችውም: የምትጠበቀውም በፈቃደ እግዚአብሔር ነውና እንጸልያለን እንጂ አንጨነቅም:: በተለያየ ወሬም ራሳችንን አናማጥንም:: ባለቤቱ እንድትሔድ ከፈቀደ ደግሞ ማንም ጉልበተኛ አያስቀራትም::

ታቦተ ጽዮን ብዙ ጊዜ "ጽላተ ኪዳን: ታቦተ ሕጉ" እየተባለች ትጠራለች:: "ጽሌ" ማለት "ሰሌዳ" እንደ ማለት ሲሆን "ጽላት" ደግሞ በብዙ ቁጥር ነው:: "ኪዳን" ደግሞ በፈጣሪና በሰው ልጆች መካከል ያለ "ውል - ስምምነት" ነው::

"ታቦት" ማለት "ማሕደር-ማደሪያ" እንደ ማለት ነው:: ሕጉ የተጻፈባቸውን ሰላድው "ጽላት" ስንላቸው የጽላቱ ማደሪያ ደግሞ "ታቦት" ይባላል:: ጽላት (ታቦትን) ያመጣ ፈጣሪ ነው:: በሐዲስ ኪዳንም ምሥጢርና ሐተታ ቢኖረውም 2 ቦታ ላይ ስለ ታቦት ተጠቅሶ እናገኛለን:: (2ቆሮ. 6:16, ራዕይ. 11:19)

#በመጨረሻም_ኅዳር_21 ቀን ጽዮን ማርያምን የምናከብርባቸውን ምክንያቶች እንመለከታለን:: በዚህች ቀን:-

1. ታቦተ ጽዮን (ጽላተ ኪዳን) ለሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ መሰጠቷን እናስባለን:: ይሕ ሲሆንም ቅዱስ ሙሴ 40 መዓልት: 40 ሌሊት ጾሞ እንደ ተቀበለ ሳንዘነጋ ማለት ነው:: (ዘጸ. 31:18, ዘዳ. 9:19)

2. በዘመነ ኤሊ ሊቀ ካህናት ታቦተ ጽዮን በታሪኩዋ ለመጀመሪያ ጊዜ በአሕዛብ (ኢሎፍላውያን) እጅ ተማርካለች:: ግን ደግሞ ዳጐንን ቀጥቅጣዋለች:: (1ሳሙ. 5:1)

3. በዘመነ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በአሚናዳብ ሠረገላ ሁና: ከአቢዳራ ቤት ስትመጣ ቅዱሱ ንጉሥ በታላቅ ሐሴት በፊቷ ዘመረ: አገለገለ:: ምድራዊ ክብሩን እስኪረሳ ድረስ ለታቦተ አምላክ ተቀኘላት:: በዚህም ሜልኮል ንቃው ማሕጸኗ ተዘግቷል:: (1ዜና. 15:25) ሊቃውንትም "ድንግል እመቤታችን ማርያም በትንቢት መነጽር ተመልክቷል" ብለውናል::

"ሰላም ለኪ ማርያም እምነ::
ዘሰመይናኪ ጸወነ::
ሶበ እምርሑቅ ርእየ ዘጽላሎትኪ ስነ::
ለቢሶ ዳዊት ልብሰ ክብር ዘየኀይድ ዓይነ::
ቅድመ ታቦተ ሕግ ኀለየ ወዓዲ ዘፈነ::" እንዲል:: (አርኬ ዘኅዳር 21)

4. በዘመነ ንጉሥ ሰሎሞን (መፍቀሬ ጥበብ) ግሩም የሆነ ቤተ መቅደስ ተሰርቶላት ስትገባ ታላቅ ሐሴት ተደርጉዋል:: እግዚአብሔርም በደመና ወርዶ ንጉሡን አነጋግሯል:: (2ዜና. 5:1, 1ነገ. 8:1)

5. በዚያው ዘመንም በፈጣሪ ፈቃድ ንጉሥ ምኒልክ ቀዳማዊ (ዕብነ ሐኪም) ታቦተ ጽዮንን ይዞ ወደ ኢትዮዽያ ገብቷል::

6. በዘመነ አፄ ባዜን (በ4 ዓ/ም አካባቢ) አማናዊት ጽዮን ድንግል ማርያም ወደ አክሱም ጽዮን በስደት መጥታ ገብታለች:: በዚህ ጊዜም 2ቱ ጽዮኖች ሲገናኙ ታላቅ ብርሃን አክሱምን ውጧታል::

7. በ4ኛው መቶ ክ/ዘመንም ነገሥት ጻድቃን አብርሐ ወአጽብሐ 12 መቅደሶች ያሏትን ግሩም ቤተ ክርስቲያን ለእመ ብርሃን ሠርተው በዚሁ ቀን በጌታችን ተቀድሷል::

8. በተጨማሪም በየጊዜው: ማለትም በዮዲት ጉዲትና በግራኝ አማካኝነት ስትፈርስ ወደ ዝዋይ ትሰደድ ነበር:: ተመልሳ ስትታነጽም ቅዳሴ ቤቷ የሚከበረው ኅዳር 21 ቀን ነው:: በእነዚህና በሌሎች ምክንያቶች ይህ በዓል ልዩ ነው::

" አማናዊት ጽዮን እመ ብርሃን ድንግል ማርያምን እንዲህ እንላታለን "

"ቅድስት" የሚለው ቃል ለሁሉም ቅዱሳት እናቶች ቢሰጥም ቅሉ ለድንግል ማርያም ሲሰጥ ግን ትርጉሙ ይለያል:: እርሷ "ቅድስተ ቅዱሳን: ንጽሕተ ንጹሐን: ቡርክት እምቡሩካን: ኅሪት እምኅሩያን" ናትና::

ከሰው ልጆችም ሁሉ ትበልጣለች:: ይቅርና የሰው ልጅን ንጹሐን መላእክትንም በንጽሕናና በቅድስና ትበልጣቸዋለች:: እርሷ እመ ብርሃን: የአምላክ እናቱ: የሰውነታችን መመኪያ ናትና::

#እመቤታችንን "ቅድስት" ስንል "ጽንዕት: ንጽሕት: ክብርት: ልዩ" ማለታችን ነው::

1. "ንጽሕት" ትባላለች:: ሌሎች ቅዱሳን ቢነጹ ከገቢር: ከነቢብ ኃጢአት ነው እንጂ ከኃልዮ ኃጢአት አይደለም:: እርሷ ግን ከነቢብ: ከገቢር: ከኃልዮ ንጽሕት ናት::

"ለመኑ ተውኅቦ ተደንግሎ ኅሊና: ለመላእክትሂ ኢተክህሎሙ-ኃጢአትን ከማሰብ መጠበቅ ከሰው ልጆች ለማን ተሰጠው: ይህስ ለመላእክትም አልተቻላቸውም" እንዲል:: (ተአምረ ማርያም)

2. "ጽንዕት" እንላታለን:: ሴቶች ቢጸኑ ለጊዜው ነው እንጂ በሁዋላ በጊዜው ተፈትሆ አለባቸው:: እመቤታችን ግን ቅድመ ጸኒስ: ጊዜ ጸኒስ: ድኅረ ጸኒስ: ቅድመ ወሊድ: ጊዜ ወሊድ: ድኅረ ወሊድ ድንግል ናትና::

¤ "ጽንዕት በድንግልና አልባቲ ሙስና" እንዳላት:: (ቅዱስ ያሬድ)
¤ ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስም "ወትረ ድንግል ማርያም-ማርያም ዘለዓለማዊት ድንግል ናት" እንዳለ:: (መጽሐፈ ቅዳሴ)

3. ድንግልን "ክብርት" እንላታለን:: ሌሎች ሴቶች ቢከብሩ ጻድቃን ሰማዕታትን: ነቢያት ሐዋርያትን ወልደው ነው:: እመቤታችንን ግን የምናከብራት "ወላዲተ አምላክ-የአምላክ እናቱ" ብለን ነውና::

4. እመቤታችንን "ልዩ" እንላታለን:: ከእርሷ በቀር እናት ሁና ድንግል: እመቤት ሁና አገልጋይ የሆነች: በድንግልና ወልዳ ወተትን (ሐሊበ ድንግልናዌን) ያስገኘች ሌላ ሴት የለችምና::

#ሼር
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
21.5K viewsedited  17:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-29 23:28:57 ​​ኅዳር 20
ቅዱስ አባት አንያኖስ

በዚህች ቀን ቅዱስ አባት አንያኖስ አረፈ። እርሱም ለወንጌላዊ ማርቆስ ሁለተኛ የሆነ የእስክንድርያ አገር ሊቀ ጳጳሳት ነው።

የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ አረማውያን ናቸው እርሱም ጫማ ሰፊ ነበር ቅዱስ ወንጌላዊ ማርቆስም ወደ እስክንድርያ አገር መጀመሪያ በገባ ጊዜ እግሩን ተደናቅፎ ጫማው ተቆረጠ እንዲሰፋለትም ወደ ጫማ ሰፊ አንያኖስ ዘንድ ሔደና ጫማውን ሰጠው መስፋትም በጀመረ ጊዜ መስፊያው ጣቱን ወጋው በዮናኒም ቋንቋ አታኦስ አለ ትርጓሜውም አንድ እግዚአብሔር ማለት ነው። ቅዱስ ማርቆስም የእግዚአብሔርን ስም ሲጠራ በሰማ ጊዜ ደስ ብሎት የክብር ባለቤት ክርስቶስን አመሰገነው።

ከዚህም በኋላ አፈር አንሥቶ በምራቁ ጭቃ አድርጎ በአንያኖስ ጣት ላይ አደረገውና በዚያን ጊዜ አዳነው አንያኖስም ከዚህ ድንቅ ምልክት የተነሣ አደነቀ ቅዱስ ማርቆስንም ወደ ቤቱ ወሰደው ስለ ሥራው ስለ አምልኮቱም የመጣውም ከወዴት ቦታ እንደሆነ ጠየቀው።

ቅዱስ ማርቆስም ከብሉያትና ከሐዲሳት መጻሕፍት የአንድ እግዚአብሔርን ህልውና ስለ ዓለሙ ሁሉ ድኅነት የወልደ እግዚአብሔርን ሰው መሆን፣ መከራ መስቀልንም ተቀብሎ ስለመሞቱ፣ ስለ ትንሣኤውና፣ ስለዕርገቱ፣ ዳግመኛም ለፍርድ ስለ መምጣቱ ይነግረው ጀመረ።

የአንያኖስም ልቡ ብሩህ ሆኖለት በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ ከቤተሰቡ ሁሉ ጋር ተጠመቀ። የመንፈስ ቅዱስም ጸጋ በላያቸው ወረደ አዘውትሮ በመጠመድ የሐዋርያ ቅዱስ ማርቆስን ትምህርት የሚሰማ ሆነ የቤተ ክርስቲያንንም ትምህርት ሕጓንና ሥርዓቷንም ተማረ።

ቅዱስ ማርቆስም ወደ ሌሎች አገሮች ሒዶ ለማስተማር በፈለገ ጊዜ እጆቹን በአንያኖስ ላይ ጭኖ በግብጽ አገር ለወገኖቹ ወንጌልን ይሰብክ ዘንድ ሊቀ ጵጵስና ሾመው እርሱም ብዙዎችን አስተምሮ አጠመቃቸው በቀናች ሃይማኖትም አጸናቸው ቤቱንም ቤተ ክርስቲያን አደረጋት እርሷም በስተምዕራብ ከእስክንድርያ ከተማ ውጭ ያለች ዛሬ የሰማዕት ቅዱስ ሰርጊስ ቤተ ክርስቲያን ሁና የታወቀች ናት።

ይህ የተመሰገነ አባት አንያኖስም በወንጌላዊ ማርቆስ ወንበር ዐሥራ ሁለት ዓመት ኖረ እግዚአብሔርንም አገልግሎ በሰላም አረፈ።

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን ።

ለሁሉም ኦርቶዶክሳዊ ሼር አድርጉ
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
17.5K views20:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-29 08:55:17
ሰላም፡ለኵልክሙ። እነሆ ግእዝን በአንድ ወር ኮርሳችን በአዲስ መልኩ ለመጀመር በ10ኛው ዙር ትምህርት መርሐ-ግብር ተመልሷል።

በመሆኑም ለጀማሪዎች የግእዝ ቋንቋን ቀለል ባለና ዘመኑን በዋጀ መልኩ ለመስጠት ቅድመ ዝግጅታችንን አጠናቀናል ከታች በተቀመጠው ሊንክ በመመዝገብ ጥንታዊና ውዱ ቋንቋችንን እናጥና ፥ ዕንወቅ።

ትምህርቱን ከ14 ዓመት ዕድሜ በላይ የሆነ ማንኛውም ሰው፤ ስልክ ወይም ላፕቶፕ ወዴስክቶፕ በመጠቀም መማር ይቻላል።

 ለመመዝገብ በዚህ ሙሉ ስም እና ስልክ ቁጥር በመላክ ግሩፖችን መቀላቀል ነው
@Geez202
@Geez202
@Geez202
                

ለበለጠ መረጃ በ @Geez202 ውስጥ ይደርስዎታል ወይም ከታች በተቀመጠው ደውለው ያግኙን። ሠናይ፡ጊዜ።

ለሌሎችም ሼር በማድረግ እንድናዳርስ በአክብሮት እንጠይቃለን
መሠረተ፡ግእዝ
@MesereteGeez - 0977682046
12.7K views05:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-28 00:50:59 ​​✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን፡፡ ✞✞✞

ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ

እንደ አባቶቻችን ትርጉም 'ፊልዾስ' ማለት መፍቀሬ አኃው ወንድሞችን የሚወድ' ማለት ሲሆን ከ12ቱ ቅዱሳን ሐዋርያት አንዱ ነው:: (ማቴ. 10:3) በዚህ ስም የሚጠራ ሐዋርያ ከ72ቱ አርድእት ውስጥ ነበር:: እርሱም ጃንደረባውን ባኮስን ያጠመቀው ነው።

አንዳንዴ የ2ቱ ታሪክ ሲቀላቀል እንሰማለን:: ለሁሉም ይህኛው ቅዱስ ፊልዾስ ቁጥሩ ከ12ቱ ሐዋርያት ሆኖ ምሑራነ ኦሪት ከሚባሉትም አንዱ ነበር:: በወቅቱ ገማልያል የሚሉት ክቡርና ምሑረ ኦሪት በርካታ ምሑራነ ኦሪትን አፍርቶ ነበር::

እንደ ምሳሌም ቅዱሳኑን "ዻውሎስን: ኒቆዲሞስን: ናትናኤልን: እስጢፋኖስንና የዛሬውን ሐዋርያ ቅዱስ ፊልዾስን" መጥቀስ እንችላለን:: ቅዱስ ፊልዾስ ነገዱ ከእሥራኤል ሲሆን ተወልዶ ያደገው በቤተ ሳይዳ ነው:: ኦሪትን ተምሮ በመንገድ ዳር ቁጭ ብሎ 'መሲሕ ቀረ' እያለ ሲተክዝ ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እርሱ ደረሰ::

ትክ ብሎ አይቶት "ተከተለኝ" አለው:: (ዮሐ. 1:44) ቅዱስ ፊልዾስም ያለ ማመንታት: ሁሉን ትቶ በመንኖ ጥሪት ተከተለው:: በዚህ ዓይነት ጥሪ መድኃኒታችን ቅዱስ ማቴዎስንም ጠርቶታል:: (ማቴ. 9:9) ቅዱስ ፊልዾስ ጌታን ከተከተለ በሁዋላ ሥራ አልፈታም። ወዲያውኑ ሒዶ ለናትናኤል (ቀናተኛው ስምዖን) ሰበከለት እንጂ።

"ሙሴ በኦሪት: ነቢያትም የተነበዩለትን መሲሕን አግኝቸዋለሁ" አለው:: ይሕ አነጋገሩም ምሑረ ኦሪት እንደ ነበር በእርግጥ ያሳያል:: (ዮሐ. 1:46) ቅዱስ ናትናኤልም ምሑር ነውና "ከናዝሬት ደግ እንዴት ይወጣል?" ቢለው ቅዱስ ፊልዾስም መልሶ "ነዐ ትርአይ-ታይ ዘንድ ና" አለው::

ናትናኤልም ሒዶ በጌታ አመነ:: ቅዱስ ፊልዾስ አገልጋይ እንደ መሆኑ መጠን በዮሐንስ ወንጌል ተደጋግሞ ስሙ ተጠቅሷል:: በተለይ ደግሞ ጌታ የ5 ገበያ ሕዝብን አበርክቶ ሲመግብ አስቀድሞ ጥያቄ ቀርቦለት ነበር:: እርሱ ግን "ጌታ ሆይ! የ200 ዲናር እንጀራ ብንገዛም አንዘልቀውም" ብሎ ነበር::

በሁዋላ ግን የጌታን ድንቅ ተአምር ተመለከተ:: (ዮሐ. 6:5) በተለይ ደግሞ በሐዋርያት አበው መካከል ለጌታ እንደ እንደራሴ ሆኖ ያገለግል እንደ ነበርም ተጠቅሷል:: ሰዎች ጌታን ማግኘት ሲፈልጉ እሱና እንድርያስን ያናግሩ ነበር:: (ዮሐ. 12:20) አንድ ጊዜ ግን እስካሁን ሊቃውንትን የምታስደምም ጥያቄ ጠይቆ ነበር::

አጠያየቁ ደግሞ ፍጹም የዋሕ እንደ ሆነ ያሳያል:: ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ባሕርይ አባቱ አብ እየነገራቸው ሳለ ቅዱስ ፊልዾስ ከመካከል ተነስቶ "እግዚኦ አርእነሁ ለአብ ወየአክለነ": ልክ ወልድን በዐይኑ እንዳየ ሁሉ አብን ሊያይ ቸኩሎ "አቤቱ ስለ አብ የሰማነው ይበቃልና አሳየን" ብሎታል:: (ዮሐ. 14:8)

ጌታችን ግን "ዘርእየ ኪያየ ርዕዮ ለአብ-እኔን ያየ አብን አይቷል" (ዮሐ.14:9) ብሎ ምሥጢረ ባሕርዩን: አንድነቱን ሦስትነቱን አስረድቶታል:: ቅዱስ ፊልዾስም ጌታን እስከ ሕማሙ አገልግሎ: ቅድስት ትንሳኤውን አይቶ: ለ40 ቀናት መጽሐፈ ኪዳንን: ትምሕርተ ኅቡዓትን ተምሮ: ቅዱስ መንፈሱን ከ72 ልሳን ጋር ነስቶ ለስብከተ ወንጌል ወጥቷል::

ቅዱሳን ሐዋርያት ዓለምን በእጣ ሲካፈሉ ለእርሱ አፍራቅያ (አፍሪካ) ደርሳዋለች:: ስለዚህም በምድረ አፍሪካ ወንጌልን ከሰበኩ ሐዋርያት አንዱ ነው:: በአፍራቅያና በቀድሞው የኃምስቱ አሕጉር ግዛት ድንቅ ድንቅ ተአምራትን አድርጐ ብዙዎችን ወደ መንጋው (ወደ ክርስትና በረት) ቀላቀለ::

ለበርካታ ዓመታትም በተለያዩ የዓለም ክፍሎች እየተዘዋወረ ወንጌልን ሲሰብክ: ብርሃነ ክርስቶስን ሲያበራ: ነፍሳትንም ሲማርክ ቆየ:: ገድለ ሐዋርያት እንደሚለው የቅዱስ ፊልዾስ ፍጻሜው በሰማዕትነት እንደ ሆነ ቢታወቅም የትኛው ሃገር ውስጥ እንደ ሆነ መለየት አልተቻለም::

ዜናው ግን እንዲህ ነው:- በአንዲት ሃገር ውስጥ ገብቶ ሰበከ:: ብዙዎችንም አሳመነ:: ያላመኑት ግን ይዘው አሰቃዩት: ገረፉት:: "በክርስቶስ እመኑ እባካችሁ!" እያለ እየለመናቸው ዘቅዝቀው ሰቅለው ገደሉት::

ከዚያም በእሳት እናቃጥላለን ሲሉ ቅዱስ መልአክ ከእጃቸው ነጥቆ ወደ ኢየሩሳሌም ወሰደው:: በዚህ የደነገጡት ገዳዮቹ ለ3 ቀናት ጾሙ: ተማለሉ:: በዚህ ምክንያት የቅዱሱ ሥጋ ተመልሶላቸው: ገንዘው ቀብረውት በክርስቶስ አምነዋል::

አምላከ ቅዱሳን ስለ ወዳጆቹ ሲል ቸርነቱን: ምሕረቱን ይላክልን። ከበረከታቸውም ይክፈለን።

ለሁሉም ኦርቶዶክሳዊ ሼር አድርጉ
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
13.9K views21:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-27 20:32:48 ​​እንኳን ለዓለም ሁሉ መምሕር ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ እና ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ማን ነው? ነገዱ ከሶርያ: የተወለደው በ347 ዓ/ም በእስክንድርያ ሲሆን አባቱ አስፋኒዶስ እናቱ ደግሞ አትናስያ ይባላሉ:: እነርሱ ደግ ቢሆኑ ይህንን እንቁ ልጅ እግዚአብሔር ሰጣቸው:: ዮሐንስ ለክርስቲያን እንደሚገባ…
13.0K views17:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-27 07:48:36
15.2K views04:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ