Get Mystery Box with random crypto!

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

የቴሌግራም ቻናል አርማ ortodoxmezmur — ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit
የቴሌግራም ቻናል አርማ ortodoxmezmur — ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit
የሰርጥ አድራሻ: @ortodoxmezmur
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 135.77K
የሰርጥ መግለጫ

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ አሜን።
. ዝማሬ ዳዊት
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች, መዝሙራት እና ወረባትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ።
ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት
@zmaredawit_messengerbot ላይ
ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 15

2023-11-11 10:13:29 ሰላም የተወደዳችሁ ኦርቶዶክሳዊያን

እኔ ዲያቆን ዳግማዊ ሰለሞን እባላለሁ ከዝማሬ ዳዊት ቻናል አስተባባሪዎች መካከል አንዱ ስሆን እኔ እና አገልጋይ ወንድሞቼ ይሄንን ቻናል ለብዙዎች
ኦርቶዶክሳዊያን የሚጠቅም እና መንፈሳዊ ትምህርት የሚገኝበት እንዲሆን ከቀን ከሌሊት
እየሰራን እንገኛለን። ነገር ግን ባለፉት 4 ወራት
ከ140,000 ወደ 135,800 የቻናላችን ተከታዮች ቀንሰዋል ።

በተለያዩ አጋጣሚዎች እንደ ቻናል ማስተካከል ያለብን ነገር ካለ እንድትጠቁሙን ስንጠይቅ ነበር።
ነገር ግን ይሄ ቻናል እስከ አሁንም ድረስ የቆመው
በእናንተ ድጋፍ እና ብርታት ነውና። አሁንም ይሄንን
ቻናል ወደ ቀደመ ቦታው መመለስ የእናንተም ድርሻ ይሆናል።


ስለዚህ ኦርቶዶክሳዊያን የዝማሬ ዳዊት አባላት
የቅዳሴው ትምህርት፣ሌሎችም ዝማሬዎች እና መንፈሳዊ ሕይወትን ያተኮሩ ትምህርቶች እንዲቀጥሉ ከእዚህ በኋላ ከእናንተ የሚጠበቀው።

ለምታውቋቸው ስልካችሁ ላይ፣ቴሌግራማችሁ ላይ ላሉ 100 ኦርቶዶክሳዊያን ይሄንን ከታች የምንልክላችሁ የቻናሉን ሊንክ እና መልእክት ትልኩላቸው ዘንድ በታላቅ ፍቅር እና አክብሮት እንጠይቃለን።

እስከ አሁን እኛ በእግዚአብሔር ቸርነት ደከምን
እናንተ ኦርቶዶክሳዊያን እህት ወንድሞቻችን ደግሞ
የእኛን ድካም የምታግዙን ከሆነ አሁን እኛን ደግፋችሁ የሳምራዊቷን ሴት አገልግሎት በሚመስል መልኩ ለብዙዎች የሚደርሰውን ይህንን የወንጌል ቃል በመላክ ከምናዘጋጀው መንፈሳዊ ማዕድ እንዲካፈሉ ታደርጉ ዘንድ እንጠይቃለን
13.0K views07:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-10 14:01:38 ​​አዘነች ድንግል አለቀሰች

አዘነች ድንግል አለቀሰች ፍጹም አምርራ
በአንድ ልጇ ምክንያት ደርሶባት መከራ
በአንድ ልጇ ምክንያት ደርሶባት መከራ/፪/
#አዝ
በመንጻቱ ወር በዓርባኛው ቀን
ሥምዖን አረጋዊ ታቀፈ እና ጌታን
ትንቢት ተናገረ ተገልጾለት ሞቱ
በነፍስሽ ሠይፍ ያልፋል አንቺም እናቲቱ
ይኽንን መከራ ሲሠማ ጆሮዋ
አምርራ አለቀሰች አልቆም አለ ዕንባዋ
#አዝ
በአሥራ ሁለት ዓመቱ ለማክበር በዓል
በኢየሩሳሌም ቢገኝ አማኑኤል
ሲጠይቅ ሲሠማ በቤተ መቅደሱ
የኦሪት ካኅናት ሲደነቁ በእርሱ
እስከ ሦስት ቀን ድረስ ብትልጣው ፈልጋ
ልቧ ተሠበረ በሐዘን አለንጋ
#አዝ
ጠዋት በማለዳ በጲላጦስ ደጅ
ሲጸናበት አይታ የጨካኞች እጅ
ርቃኑን አድርገው ያለ አንዳች ጥፋት
ከግንድ ጋር አስረው ጀርባውን ሲገርፉት
እንዴትስ አታለቅስ እንዴት አታነባ
ሲገርፉት ሲያዳፉት ልጇን እንደ ሌባ
#አዝ
የዓለሙን ፈጣሪ የዓለሙን ዳኛ
ንጹሑን ጌታ መሥሏቸው ቀማኛ
እጁን እና እግሮቹን በችንካር ወጥረው
በወንበዴ መሐል ሠቅለውን ብታየው
ድንግል አለቀሰች አልቻለች መጽናናት
ዕንባዋ ወረደ እንደ ክረምት ጅረት
#አዝ
ዮሴፍ ኒቆዲሞስ በአንድ ሲማከሩ
ቅዱሥ ሐያል ብለድ ገንዘው ሊቀብሩ
በአዲስ መቃብር በአሥራ አንደኛው ሠዓት
ሥጋውን አኑረው በድንጋይ ቢዘጉት
እያለች ዐነባች አንድ ልጄ እኮ ነው
ከእርሱ የሚቀድም ተከታይ የሌለው።

@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
15.3K views11:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-10 08:23:15 #ሰላም_አርጊው_ማርያም

ሰላም አርጊው ማርያም ስጭን የእጅሽን(፪)
አንድ መንጋ ሆነን በዛ ቋንቋችን
ናፍቀናል ልጆችሽ ፍቅር አንድነትን

በስንዴው መሃል እንክርዳዱን
ጠላት ዘራና ክፍፍሉን
የፍቅር ቋንቋ ቀዘቀዘ
አንድነታችን ደበዘዘ
እንወድሻለን ማርያም

#አዝ

ያስጎነበሰን ሸክም ይቅለል
በልጅሽ ምህረት ቀና እንበል
ሰላም እንዲሰንፍ በምሕረቱ
ንጉሡን ማልጅው ንግስቲቱ
እንወድሻለን ማርያም

#አዝ

የሽንገላ ቃል ከኛ ይውጣ
ያ ክፉ ዘመን እንዳይመጣ
በመለያየት ተመስርቶ
የፀና መንግስት የለም ከቶ
እንወድሻለን ማርያም

#አዝ

በረከት አዟል አምላካችን
ህብረት ባለበት መኖሪያችን
ክፍፍል ይቅር አሳስቢልን
በቃል ኪዳንሽ አስጠልይን
እንወድሻለን ማርያም

#አዝ

ክፋትን ተክለን በልባችን
መልክ ብቻ ነው አምልኳችን
ወድቀን እንዳንቀር እንዳንጠፋ
ፍቅርን ሳይብን የአዳም ተስፋ
እንወድሻለን ማርያም

ሊቀ_መዘምራን
ዲያቆን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
14.9K views05:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-09 22:02:12 ​​✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡፡ አሜን✞✞✞

#ቅዱስ_ማርቆስ_ዘአንበሳ

✞✞✞ በዚሕች ዕለት ከ72ቱ አርድእት አንዱ የሆነ: ወንጌላዊ: ሐዋርያ: ሰማዕት: ዘአንበሳና ርዕሰ ሊቃነ ዻዻሳት የተባለ ቅዱስ ማርቆስ ተወልዷል ::

ቅዱስ ማርቆስ እናቱ ማርያም: አባቱ አርስጥቦሎስ ይባላሉ:: በልጅነቱ ኦሪትንና የዘመኑን ጥበብ ሥጋዊ በሚገባ ተምሮ ክርስቶስን ከቤተሰቦቹ ጋር ተከትሏል:: የመጀመሪያ ስሙ ዮሐንስ ሲሆን ከ120ው ቤተሰብ በእድሜ በጣም ትንሹ /20 ዓመት/ እርሱ ነበር::

ለ3 ዓመታት ከጌታ እግር ሥር ተምሮ: በበዓለ ሃምሳ ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ ለሐዋርያዊ አገልግሎት ብዙ ደክሟል:: በተለይ የግብፅና የኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያን አባት ነው:: ክህነትን ያገኘን ከርሱ ነውና::

ቅዱስ ማርቆስ 16 ምዕራፍ ያለውን ወንጌሉን ሲጽፍ ኪሩብ ገጸ አንበሳ በቀኙ: ሊቀ ሐዋርያት በግራው ሆነው ይራዱት ነበር:: ቅዱሱ ክቅዱስ ዻውሎስ: ከበርናባስና ዼጥሮስ ጋር ተጉዟል:: ከብዙ ስቃይና መከራ በኋላ ሰሜን አፍሪካ አካባቢ አረማውያን ገድለውታል:: ይህቺ ዕለት የልደቱ መታሠቢያ ናት::

ዳግመኛ በዚህ ቀን የቅዱስ ማርቆስን ወላጆችን እናስባቸው ዘንድ ይገባል:: ቅዱስ አርስጥቦሎስ (አባቱ) የጌታ ቅን አገልጋይ የነበረ: ቅድስት ማርያም (እናቱ) ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት አንዷ: ጌታችንን ያገለገለች ቤቷን ለሐዋርያትና ለጌታ በስጦታ ያበረከተች ቅድስት ናት::

ቤቷም (ጽርሐ ጽዮን) የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን ስትሆን ይህች ቤት መንፈስ ቅዱስ ወርዶባታል:: የእመቤታችን ግንዘትም ተከናውኖባታል::

እግዚአብሔር ከሐዋርያዊው ቅዱስ ቤተሰብ በረከትን ያድለን::

#ቅዱስ_ዮሐንስ_መጥምቅ

ቅዱስ ወንጌል ላይ ከእመቤታችን ቀጥሎ የነዘካርያስን ቤተሰብ ያህል ክብሩ የተገለጠለት ፍጡር ይኖራል ብሎ መናገሩ ይከብዳል:: ቅዱስ ሉቃስ ወንጌሉን የጀመረው በዚህ ቅዱስ ቤተሰብ ነውና መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ሲል አጽፎታል:: "ዘካርያስ ካህኑና ቅድስት ኤልሳቤጥ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ የሚኖሩ ጻድቃን ነበሩ" ይላቸዋል:: (ሉቃ. 1:6)

የሰውን እንተወውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ መኖር ምን ይረቅ? ለዚህ አንክሮ (አድናቆት) ይገባል!
እሊህ ቅዱሳን ባልና ሚስት ግን መካኖች በመሆናቸው ልጅ ሳይወልዱ ዘመናቸው አልፎ ነበር:: እንደ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት ዕድሜአቸው የኤልሳቤጥ 90 የዘካርያስ 100 ደግሞ ደርሶ ነበር::

ፍጹም መታገሳቸውን የተመለከተ ጌታ ግን በስተ እርጅናቸው ከሰው ሁሉ በላይ የሆነ: ትንቢት ለብቻው የተነገረለት (ኢሳ. 40:3, ሚል. 3:1) ታላቅ ነቢይን ይሰጣቸው ዘንድ መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤልን ላከላቸው::

ቅዱስ ዘካርያስ ሰው ነውና ከደስታ ብዛት በመከራከሩ ድዳ ሆነ:: ቅድስቲቷ ግን መስከረም 26 ቀን ታላቁን ሰው ጸንሳ ለ6 ወራት ራሷን ሠወረች:: በ6ኛው ወር የፍጥረት ሁሉ ጌታ በተጸነሰ ጊዜ የአርያም ንግሥት ድንግል እመቤታችን ደጋ ደጋውን ወደ ኤልሳቤጥ መጣች:: ሁለቱ ቅዱሳት የእህትማማች ልጆች ናቸው::

የአምላክ እናቱ ስትደርስና "ሰላም" ስትላቸው መንፈስ ቅዱስ በእናትና ልጅ ወርዶ ኤልሳቤጥ በምስጋና: ዮሐንስ ደግሞ ገና በማሕጸን ሳለ በደስታ ዘለለ (ሰገደ):: ከዚህ በኋላ በዚህች ቀን (ሰኔ 30) ተወልዶ: አባቱ ዘካርያስ "ዮሐንስ" ሲለው አንደበቱ ተፈትቶለታል::

ቅዱስ ዮሐንስ ከተወለደ 2 ዓመት ከ6 ወር በሆነው ጊዜ ሰብአ ሰገል በመምጣታቸው በእሥራኤል ምድር የሚገኙ ሕጻናትን ሔሮድስ ቁዝ አስፈጀ:: ትንሽ ቆይቶም አይሁድ ለሔሮድስ ስለ ቅዱሱ ሕጻን ነገሩት:: "ሲጸነስ የአባቱን አንደበት የዘጋ: ሲወለድ ደግሞ የከፈተ 'ዮሐንስ' የሚባል ሕጻን አለና እሱንም ግደል" አሉ::

እናቱ ቅድስት ኤልሳቤጥ ይዛው ስትሸሽ ካህኑን ዘካርያስን ግን በቤተ መቅደስ መካከል ገድለውታል:: አረጋይት ኤልሳቤጥም ሕጻኑን እያሳደገች በገዳመ ዚፋታ ለ3 (5) ዓመታት ቆይታለች:: ቅዱስ ዮሐንስ 5 (7) ዓመት ሲሞላው ግን እዚያው በበርሃ እናቱ ዐረፈች:: ከሰማይ ዘካርያስና ስምዖን ወርደው ቀበሯት::

ሕጻኑ ዮሐንስ ሲያለቅስ ድንግል ማርያም ስንት አገር አልፋ ሰማችው:: እርሷም ስደት ላይ ነበረችና:: ከጌታ ጋር በደመና ሒደው ድንግል አቅፋ አጽናናችው:: ጌታንም "እንውሰደው ይሆን?" አለችው:: ጌታችን ግን "ለአገልግሎት እስክጠራው እዚህ ይቆይ" አላት:: ባርካው: አጽናንታውም ተለያዩ::

ቅዱስ ዮሐንስ ከዚህ በኋላ በዚያ ቆላ የግመል ጠጉር ለብሶ: ጠፍር ታጥቆ ተባሕትዎውን ቀጠለ:: ለ25 (23) ዓመታትም በንጽሕና ሲኖር ከምድር አራዊትና ከሰማይ መላእክት በቀር ማንንም አላየም:: ይሕችን ዐመጸኛ ዓለምም አልቀመሳትም::

ከዚህ በኋላ 30 ዘመን ሲሞላው እግዚአብሔር ከሰማይ ተናገረው:: "ሒድ! የልጀን ጐዳና ጥረግ" አለው:: ነቢያት ስለዚህ ነገር ተናግረው ነበርና:: (ኢሳ. 40:3, ሚል. 3:1) አባቱ ዘካርያስም "ወአንተኒ ሕጻን ነቢየ ልዑል ትሰመይ: እስመ ተሐውር ቅድመ እግዚአብሔር ከመ ትጺሕ ፍኖቶ" (ሉቃ. 1:76) ብሎ መንገድ ጠራጊነቱን ተናግሮ ነበርና::

ቅዱስ ዮሐንስ በዚያ ጊዜ በኃይለ መንፈስ ቅዱስ እየገሰገሰ ከበርሃ ወደ ይሁዳ መጣ:: ያዩት ሁሉ ፈሩት: አከበሩት:: ቁመቱ ቀጥ ያለ: ጽሕሙ እንደ ተፈተለ ሐር የወረደ: ጸጉሩ የቁራ ያህል የጠቆረ: መልኩ የተሟላ: ግርማው የሚያስፈራ ገዳማዊ ነውና::

ፈጥኖም ሕዝቡን ለንስሃ ሰበከ: ለንስሃም በርካቶችን አጠመቃቸው:: በዚህ አገልግሎት ለ6 ወራት ቆይቶ ጌታችን ወደ እርሱ ዘንድ መጣ:: ዮሐንስ ሰማይን ከነግሱ: ምድርን ከነልብሱ የያዘ ፈጣሪ 'አጥምቀኝ' ብሎ ሲመጣ ደነገጠ:: የሚገባበትም ጠፋው::

"እንቢ ጌታየ! አንተ አጥምቀኝ" አለው:: ጌታ ግን "ፈቅጄልሃለሁ" አለው: አጠመቀው:: በዚህ ምክንያት ይሔው እስከ ዛሬም "መጥምቀ መለኮት" ሲባል ይኖራል:: ቅዱስ ዮሐንስ በመጨረሻ ሔሮድስን ገሰጸው:: ንጉሡም ተቀይሞ ለ7 ቀናት አሠረው::

በዚህች ቀንም ልደቱን ባከበረ ጊዜ ወለተ ሔሮድያዳ በዘፈን አጥምዳ አስማለችው:: እርሱም የታላቁን ነቢይ ራስ አስቆርጦ በወጪት አድርጐ ሰጣት:: አበው "እምሔሶ ለሔሮድስ ይብላዕ መሐላሁ - ሔሮድስ መሐላውን በበላ በተሻለው ነበር" ይላሉ:: የቅዱስ ዮሐንስ ራሱ በርራ ስትሔድ አካሉን ግን ደቀ መዛሙርቱ ቀብረውታል:: (ማቴ. 3:1, ማር. 6:14, ሉቃ. 3:1, ዮሐ. 1:6)

ርጉም ሔሮድስ አንገቱን ካስቆረጠው በኋላ የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ራሱ የጸጋ ክንፍ ተሰጥቷት ጌታችን ወዳለበት ደብረ ዘይት ሔዳ በፊቱ ሰገደች:: ቅዱሳን ሐዋርያት በአዩት ነገር ተገርመው ራሱን እጅ ነሷት::

ከዚሕ በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱስ ዮሐንስ ራስ የማስተማር ስልጣን ሰጥቶ አሰናበታት:: በመላው ዓለም ለ15 ዓመታት ስትሰብክ ኑራ ዓረቢያ ውስጥ ዓርፋለች::

ይህች ዕለት ለቅዱሱ 'አስተርዕዮተ ርዕሱ' ወይም ቅድስት ራሱ ከተወረችበት የተገለጠችበት ነው::

ጥቅምት 30 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

1. ቅዱስ ማርቆስ ሐዋርያ
2. ቅዱስ አርስጥቦሎስ (አባቱ)
3. ቅድስት ማርያም (እናቱ)
4. ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
5. አባ አብርሃም ገዳማዊ
6. ቅዱስ ይስሐቅ ንጉሥ

ዝክረ ቅዱሳን
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
15.9K views19:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-09 13:48:30 በይስሐቅ ፈንታ
የበገና መዝሙር

በይስሐቅ ፈንታ ኢየሱስ ታረደ/2/
ደሙን ከፈለና አዳምን ታደገ/2/

ተጨነቀ ጌታ ተሰቃየ ጌታ
የኔ መድኃኔዓለም የአዳም ልጅ አለኝታ
እንደሚታረድ በግ ተነዳ ወደ ሞት
ንፁህ ኢየሱስ በደል የሌለበት

በማመን ሲሸከም የአዳምን መከራ
ስቃይ ተቀበለ ደሙ እየተዘራ
ለሚገርፋት ሁሉ ምህረትን ሲቸር
እርሱ ግን ሲገረፍ ብዙ ተቸገረ

የሰማነውን ድምፅ ማን ሰው እኮ አምኗል
የእግዚአብሔርስ ክንድ ለነማን ተገልጿል
ባየነው ጊዜ ህመም ተሸክሞ
ስለበደላችን ተገርፎና ታሞ

እጁ የታሰረው ይስሀቅ ተፈቶ
ኢየሱስ ቀረበ በሰው ልጆች ፈንታ
ንፁህ በግ ቀረበ በደል የሌለበት በደለኛ ሆኖ
ሊሰቀል ሊገደል መስቀሉን ተጭኖ

በእውነት ደዌያችንን እርሱ ተሰቀለ
በሰው ልጆች ፈንታ በእንጨት ተሰቀለ
እኛ ግን ከሰስነው እንደ ወንጀለኛ
ስለ እኛ ቢሰቀል ሰማያዊው ዳኛ

ለሰው ልጆች ህይወት የታሰበውን ሰይፍ
አይተናል ሰምተናል በኢየሱስ አንገት ሲያልፍ
የመስቀሉ ስዕል ኧረ እንዴት ይገርማል
እዩት ንፁህ በግ በአርምሞይነዳል

@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
15.1K views10:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-09 10:18:31
የሉቃስ ወንጌል የመጨረሻው ክፍል
14.6K views07:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-07 15:30:19 ​​ጥቅምት ፳፯ በዚህች ዕለት የታላቁ ኢትዮጵያዊ ጻድቅ አባ መባዓጽዮን መታሰቢያ ነው።

አቡነ መብዓጽዮን ለቸሩ አምላካችን ለመድኃኔ ዓለም ባላቸው ጽኑዕ ፍቅር የሚታወቁ ግሩም አባት ናቸው። ገና ልጅ እያሉ ሥዕለ አድኅኖ ተለይቷቸው አያውቅም። የመድኃኒታችንን ጽኑዕ መከራ በማሰብ በራሳቸው ላይ ያላደረጉት ምን አለ? ችንጋሮችን ራሳቸው ላይ ይቸነክሩ ነበር፣ ድንጋይ ተሸክመው ብዙ ይሰግዱና ከልቅሶ ጋር ይጸልዩ ነበር፣ ሥጋቸውንም በጽኑዕ ቅጣት ይቀጡት ነበር።

ጌታችንን ይወዱትም ስለነበር በቅዱስ ስሙ ዝክር ይዘክሩ ነበር። ዝክራቸውም በንጽሕና የኾነ ነበርና ከዚያ ዝክራቸው የቀመሰ ኹሉ ካለበት ደዌ ይፈወሳል።
ጌታችንም የሚያስደንቁ ቃልኪዳናትን የገባላቸውና በዚህች እለት ብዙ ነፍሳትን ከሲዖል ያወጡበትም እለት ነው።

ዕረፍታቸውም ከጌታችን ዕረፍት ጋራ አንድ እምደሚኾንላቸው ተነግሯቸው ነበር። ከጽኑዕ ገድልም በኋላ በዚህች ቡርክት ቀን ዐርፈዋል።

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፣ እኛንም በአባታችን በአባ መባዓ ጽዮን ጸሎት ይማረን !

@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
16.6K views12:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-06 19:55:59 ​​በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን፡፡ ✞✞✞

ጥቅምት ፳፯ (27)

✞✞✞ እንኳን ለፈጣሪያችን "መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ" እና ለቅዱሳኑ "አባ መቃርስ": "አቡነ መብዓ ጽዮን" "ወአባ ጽጌ ድንግል" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞

መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ

ጌታችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ለእኛ ሲል በፈጸመው የማዳን ሥራ ክፉዎች አይሁድ ከምሽቱ 3:00 ጌቴሴማኒ ውስጥ ያዙት:: ሙሉውን ሌሊት ከቀያፋ ወደ ሐና: ከሐና ወደ ቀያፋ ሲያመላልሱት: አስረው ሲደበድቡት አድረዋል::

ዝም ቢላቸው ዓይኑን ሸፍነው በጥፊ መቱት:: ምራቃቸውን ተፉበት:: ዘበቱበት:: ራሱንም በዘንግ መቱት:: እርሱ ግን ሁሉን ታገሰ:: በጧት ከገዢው ዘንድ ሞት እንዲፈረድበት አቀረቡት::

በሠለስት (3:00 ላይ) አካሉ እስኪያልቅ እየተዘባበቱ 6,666 ገረፉት:: ሊቶስጥሮስ አደባባይ ላይ እርጥብ መስቀል አሸክመው ወደ ቀራንዮ ወሰዱት:: 6:00 ላይ በረዣዥም ብረቶች 5 ቦታ ላይ ቸንክረው ሰቀሉት::

7 ታላላቅ ተአምራት በምድርና በሰማይ ታዩ:: ዓለም በጨለማ ሳለች ጌታ በመስቀል ላይ 7 ቃላትን ተናገረ:: ከቀኑ 9:00 አካባቢ በባሕርይ ስልጣኑ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው ለየ::

+በዚያች ሰዓትም ወደ ሲዖል ወርዶ የታሠሩትን ሁሉ ፈታ:: 11:00 ላይ ደጋጉ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብርና ሐዘን ጋር በአዲስ መቃብር ቀበሩት:: በዚአች ቀን ድንግል ማርያም ልቧ በሐዘን ተቃጠለ:: ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስም ፍፁም ለቅሶን አለቀሰ:: ቅዱሳት አንስት በዋይታ ዋሉ::

ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለው መጋቢት 27 ቀን ቢሆንም በዓሉ ወደ ጥቅምት እንዲመጣ ያደረጉት አበው ሊቃውንት ናቸው:: ምክንያቱም ብዙ ጊዜ መጋቢት 27 የሚውለው ዓቢይ ጾም ውስጥ በመሆኑና የንግሥ በዓላት በዓቢይ ጾም ስለማይፈቀዱ ነው::

ምንም እንኩዋ በቅርብ ጊዜ በዓቢይ ጾም የሚያነግሡ አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት ቢኖሩም አባቶቻችን ግን እንዲህ ያለውን ሥርዓት አላቆዩልንም:: ከበሮና የቸብቸቦ ዝማሬም በወቅቱ የተፈቀደ አይደለም::

በዚህም ምክንያት የበዓለ ስቅለት ንግሡ ወደ ጥቅምት 27 ሲመጣ: የመጋቢት 5 ገብረ መንፈስ ቅዱስ ንግሥ ወደ ጥቅምት 5: የመጋቢት 10 መስቀል ወደ መስከረም 17 መጥቶ እንዲከበር ሆኗል::

ዝክረ ቅዱሳን
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
14.6K views16:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-03 21:39:13 ምሥጢረ ጥምቀት የመጨረሻው ክፍል

አፕሊኬሽኑ ላይ ከታች የተጠቀሱትን ተጨማሪ ጥቅሶች አይታችሁ። ጥያቄ ካላችሁ መጠየቅ ትችላላችሁ
17.7K views18:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-03 21:39:13 ምሥጢረ ጥምቀት ክፍል ፬
የጥምቀት ምሳሌ በብሉይ ኪዳን
16.4K views18:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ