Get Mystery Box with random crypto!

​​አዘነች ድንግል አለቀሰች አዘነች ድንግል አለቀሰች ፍጹም አምርራ በአንድ ልጇ ምክንያት ደርሶባ | ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

​​አዘነች ድንግል አለቀሰች

አዘነች ድንግል አለቀሰች ፍጹም አምርራ
በአንድ ልጇ ምክንያት ደርሶባት መከራ
በአንድ ልጇ ምክንያት ደርሶባት መከራ/፪/
#አዝ
በመንጻቱ ወር በዓርባኛው ቀን
ሥምዖን አረጋዊ ታቀፈ እና ጌታን
ትንቢት ተናገረ ተገልጾለት ሞቱ
በነፍስሽ ሠይፍ ያልፋል አንቺም እናቲቱ
ይኽንን መከራ ሲሠማ ጆሮዋ
አምርራ አለቀሰች አልቆም አለ ዕንባዋ
#አዝ
በአሥራ ሁለት ዓመቱ ለማክበር በዓል
በኢየሩሳሌም ቢገኝ አማኑኤል
ሲጠይቅ ሲሠማ በቤተ መቅደሱ
የኦሪት ካኅናት ሲደነቁ በእርሱ
እስከ ሦስት ቀን ድረስ ብትልጣው ፈልጋ
ልቧ ተሠበረ በሐዘን አለንጋ
#አዝ
ጠዋት በማለዳ በጲላጦስ ደጅ
ሲጸናበት አይታ የጨካኞች እጅ
ርቃኑን አድርገው ያለ አንዳች ጥፋት
ከግንድ ጋር አስረው ጀርባውን ሲገርፉት
እንዴትስ አታለቅስ እንዴት አታነባ
ሲገርፉት ሲያዳፉት ልጇን እንደ ሌባ
#አዝ
የዓለሙን ፈጣሪ የዓለሙን ዳኛ
ንጹሑን ጌታ መሥሏቸው ቀማኛ
እጁን እና እግሮቹን በችንካር ወጥረው
በወንበዴ መሐል ሠቅለውን ብታየው
ድንግል አለቀሰች አልቻለች መጽናናት
ዕንባዋ ወረደ እንደ ክረምት ጅረት
#አዝ
ዮሴፍ ኒቆዲሞስ በአንድ ሲማከሩ
ቅዱሥ ሐያል ብለድ ገንዘው ሊቀብሩ
በአዲስ መቃብር በአሥራ አንደኛው ሠዓት
ሥጋውን አኑረው በድንጋይ ቢዘጉት
እያለች ዐነባች አንድ ልጄ እኮ ነው
ከእርሱ የሚቀድም ተከታይ የሌለው።

@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur