Get Mystery Box with random crypto!

ኹሉድ ✍️

የቴሌግራም ቻናል አርማ khuludnuri — ኹሉድ ✍️
የቴሌግራም ቻናል አርማ khuludnuri — ኹሉድ ✍️
የሰርጥ አድራሻ: @khuludnuri
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 218
የሰርጥ መግለጫ

"የዕውነተኛው ዓለም ነፀብራቅ" 😊
ስሜቶቻችን በብዕር ሲሰፍር✍️
ማንኛውንም አስተያየታቹ በ @Khulud_bot

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2021-10-29 20:00:20 እናቴ"ተበዳይ ዝም ሲል ተከሳሽ ይሆናል"ትለኝ ነበር..እህምምም ሁሉም አባባሎች በቦታቸው ልክ ይሆናሉ..እና እንዳልኩህ ውዴ የበደልክ ዱላ የክህደትክ ውርጅብኝ መላ እኔነቴን ካሳመመኝ በላይ ያንተ መልስ እጅጉኑ ያቆስላል..ረጅም መንገደኛ ስንቁን ሳይቋጥር መንገድ አይጀምርም እኮ...ሊያውም መድረሻውን አውቆ..እንደኔ ተገፊ መነሻ ዬን እንጂ መድረሻዬን የማላውቅ..ያንተዋ ከርታታ ታዲያ በምን አፏ ምክንያትክን ትጠይቅ..ለኔ የመኖሬ..ካንተ ውጭ ያሉትን ሰዎች አይን ላፈር ብዬ ሙሉ እኔነቴን የሰጠውበት ምክንያቴ እኮ አንተው ነክ ታዲያ አንተ እኔን ለመተው አጥጋቢ ምክንያት እንዴት አለክ ብዬ እንዴት ለምን ልበልክ..ደግሞስ አንተ የልቤ ንጉስ እኔ ያንተ ታዛዥ ሂጂ ስትለኝ ወዴት ከማለት ውጪ ለምን ብል ነውርም አይደል...ይልቁኑም"ካንጀት ካለቀሱ እንባ አይገድብም"አይደል የሚለው የአበው ተረቱ ይሁንን ግድ የለም..መግፋትን እንጂ መገፋትን አልጠላውም...ፍቅሬ አንሶብክ ውበቴ ቀንሶ አንተን አንተን ስል ሌላው ሁሉን ነገር መዘንጋቴም አደል የሰለቸክ እኔን ለማስቀመጥ ምክንያት የጠፋክ ከራስክ አልፈክ የኔን ፍላጎትና ስሜት ባንተው እይታ ወስነክልኝ እንዲው እንደዘበት እንዲው እንደ ቀላል " ሂጂ በመኖሬ ከምትጠቀሚው የምትጎጅው ስለሚበልጥ ሂጂ ጠልቼሽ አይደለም ሂጂ ምልሽ ራስወዳድ ስላልሆንኩ እንጂ አዎ ለእኔ ብለሽ ከተጋጨሽው አለም ጋር ዳግም ታረቂ ሂጂ ማለቴን የምታመሠግኝበት ቀን ቅርብ ነው ሂጂ"ያልከኝም..መሄዱን ልሄድ ነው ንጉስ ሆይ ካዘዙ ምን አደርጋለሁ.. ስንቄም ክህደትክ ነው ብርታቴም መገፋቴ ነው..ግን ውዴ ስሞትልክ ሁለት ነገሮችን ልጠይቅክ...አንደኛው ጥያቄ ያው እንደምታውቀው የኔ ዓለም ያንተ ግዛት ነበር ይህች አንተ የሌለክባትን ዓለም እኔ አላውቃትምና  ወስደክ ከሷ አገናኝተክ አስማማኝ..ሁለተኛው ጥያቄ መድረሻዬን ንገረኝ ማረፍያዬን ጠቁመኝ..
ኹሉድ...
ለ Nedir ፅሁፍ የተሰጠ መልስ
384 views17:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-28 12:14:21 አለመረዳትሽ ሲገርመኝ ለሰዎች የቡና ማድመቂያ የነገር ዳንቴል መተብተቢያ አድርገሽኝ ከዛም ብሶ አማረርሽ አይግረምሽ ለእኔ ብለሽ ከሚሳሱልሽ እናትሽ ተጋጭተሽ...... ከአባትሽ ለአንቺ ከማሠብ ብዛት ቁጡ የሆኑትን ክብራቸውን ረግጠሽ .......ከእህትሽ በእኔ ምክነያት አይንሽን ለአፈር ተባብለሽ. .... ወንድምሽም ቢሆን የእገለዋለው ፉከራውን አፈር አብልተሽ. ...... አደግክ አደግኩ አለች ብለው ያወሩብሽን ጎረቤቶች አዎ በደንብ አድጊያለው ምን አገባችሁ ብለሽ. .... ከአብሮ አደጎችሽ ከጓደኞችሽ በተቃራኒዉ ቆመሽ ወይ ዝም በሉ አለበለዛ ከእን ጓደኝነታቸሁ ገደል መግባት ትችላለችሁ በለሽ ወደኔ እንደመጣሽ አውቀዋለሁ ከእነዚያ መጋፈጦች ጋር የኔን የልብ ትርታ አልቀሽ ከጎኔ ቆመሽ አለሁል ስትይኝ በደንብ አውቀዋለሁ እሱን ብረሳው ቀኔ ይርሳኝ

ግን ዛሬ ሂጂ ስልሽ ለምን ሂጂ አለኝ ከማለት ይልቅ ፍቅሬ እንዳለቀ እንዳስጠላሽኝ አድርገሽ ለምን አሰብሽው ለምን ሂጂ ባልኩበት ምላሴ የዛኔ ነይ እንዳልኩ የረሳሁት አስመሰልሽው
አዎ ሂጂ ብያለው አሁንም ቢሆን ሂጂ በመኖሬ ከምትጠቀሚው የምትጎጅው ስለሚበልጥ ሂጂ ጠልቼሽ አይደለም ሂጂ ምልሽ ራስወዳድ ስላልሆንኩ እንጂ አዎ ለእኔ ብለሽ ከተጋጨሽው አለም ጋር ዳግም ታረቂ ሂጂ ማለቴን የምታመሠግኝበት ቀን ቅርብ ነው ሂጂ. ....

ግልባጭ ለ Megfira
Nedirs
325 views09:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-28 12:12:40 በመገፋት ውስጥ ለካ ፍቅር አለ........ ሰው እንዴት እየተገፋ ያፈቅራል? ተው ሲባል አይተውም እንዴ.............
እውነት እኔ ለሱ የምገባ ሰው አይደለሁምና ነው? "እኔን ተይኝ" ያለኝ ቀለል አድርጎ "እኔን እርሺኝና የራስሽን ኑሮ ኑሪ" ያለኝ?
ሰርክ አዲስ ነኝ! ንግግሩ ጆሮዬ ላይ ያቃጭላል፤ ሳስበው ልቤ ይቆስላል..........
"ወድሻለው! የኔ ሁኚ!" ባለበት አንደበቱ "ሂጂ" ሲለኝ እንዴት አልቁሰል?............
"ሂጂ!" ወዴት ልሂድ?......... ላንተ ብዬ ወደተውኳቸው እልፍ አእላፍ ሰዎች?............ ወይስ አንተን ለማግኘት "ከቤት አትውጪ" እያለችኝ የሷን ትዕዛዝ ጥሼ ወጥቼ ወደተበሳጨችብኝ እናቴ?.......... ወይንስ "ዛሬ ከዚ በር ታልፊና ወይ እኔ ወይ አንቺ!" ብሎ ዝቶብኝ እሱንም እኔንም ትቼ ወደአንተ ከንፌ ወዳኮረፈኝ አባቴ?.......... እኮ ወዴት ልሂድ? "ምንሄድበት ቦታ አለ የትም አትሂጂ" ብላ ቀጥራኝ ልክ አንተ ነይ ስትለኝ እሷን ትቼ ወደአንተ በርሬ መጥቼ ከኔጋ ቀጠሮ መያዝ ያታከታት እህቴጋ ነው?.......... ወይስ "መንገድ ላይ ከወንድ ጋር ባይሽ!" ብሎ አስፈራርቶኝ ፍራቻውን ትቼ መንገድ ለመንገድ ካንተጋ በነፃነት ስበር አይቶኝ እስከአሁን የማያናግረኝ ወንድሜ ጋ?......... የት ነው "ሂጂ" ያልከኝ? የት?.......... ካንተጋ አይተውኝ "የትም ስትንዘላዘል" ብለው ያሙኝ ጎረቤቶቼጋ? .......... ወይንስ "ተይ አይሆንሽም" እያሉ ሲመክሩኝ እንደውም "እናንተ አትሆኑኝም" ብዬ የተውኳቸው ጓደኞቼ ጋር?.......... ማንጋ ነው "ሂጂ" ያልከኝ?.......... ጥለሀኝ ሄደህ ድንገት ወደ ህይወቴ መቶ ሁሉንም ነገር አስተካክሎ፡ የራሱ ሊያደርገኝ ሲል እኔም አንተን ለመርሳት፡ የሱ ልሆን ስል ድጋሚ መተህ "ነይ" ስትለኝ የገነባውን ፍቅር አፍርሼ ልምምጡን ረግጬ የመጣሁት ልጅጋ ነው ምሄደው?.......... ንገረኛ "ተይኝ" ያልከኝ አንተን ትቼ ማንን እንድይዝ ነው??

መغፊራ ቢንት ፉላን
310 views09:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-18 20:25:42 እንዲህ እንዳሁኑ...ውስጤን ባዶነት ሲሰማው..ተስፋ ሲርቅብኝ..ሆዴን ሆድ ሲብሰው..በዙርያዬ ያሉት ነገሮች ውስጥ ውስጤን ሲያቆስሉት..የብቸኝነት ስሜት ወርሶኝ ቁስሌን ሲያመረቅዘው..ካገኘውት ያጣውት በዝቶብኝ እኔነቴን ጨለማ ሲወርሰው.....
    በእነዚህ ሁሉ ስሜቶች...አንተን ማስታወሱ..የእኔ እንደሆንክ ማሰቡ..የአንተን ድምፅ መስማቱ..ሕመሞቼን ያሽርልኛል..ቁስሎቼን ያድንልኛል..በባዶ ተስፋ የከሰመው ልቤ ያብብልኛል..አንተን ማሰቡ ብቻ የብቸኝነት ስሜቴን አጥፍቶ የጨለመው እኔነቴን ዳግመኛ በብርሃን ይሞላልኛል......
    እንዴት?....እንጃ ብቻ ሰው መሆንክን እስኪያጠራጥረኝ የመልአክ ስብዕና የተላበስ ይመስል ለኔ ፍፁም ትመስለኛለክ..ከተፍጥሮም ልታጋጨኝ ትዳዳለክ..የማናደድ ወድያው ደግሞ የማስደሰት ስልጣን በእኔ ላይ አለክ..ራሴን መከልከል አልቻልኩም..ድምፅክን አለመስማቴ ያስከፋኛል ደግሞ ሳገኝክ የዱንያን አስቀያሚ ጎኑን ረስቼ ባንተ የተዋበችዋን ደቂቃዋን አጣጥማታለው..ስለይክ..አውርቼክ ስልኩን ስዘጋው ደሞ ይቺህ ገአነብ ምድር ትታወሰኛለች...የእሳቷ ነበልባል ታነደኛለች..ብቻ ብቻ ግን አሁን አሁን የመኖሬ ምክንያት ሆነከኛል..እንዴት?..እንጃ
363 views17:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-25 11:14:20 ሽሽት ወይንስ በቀል
በመغፊራ ቢንት ፉላን
ክፍል አስራ9
የመጨረሻው መጨረሻ

ሀይሚ የሰማችው ነገር ሁላ ህልም ሆነባት...... አሰበች ብዙ ነገር ተሸውዳለች፣ እሷ ብቻ ሳትሆን ጓደኛዋም ሀኒም፣ "ማሜ ይህንን ያደረገው ለበቀል ሆን ብሎ እንጂ በፍፁም ሀኒን አፍቅሯት አደለም" ስትል አሰበች። አምርራ ጠላችው...... ምን ማድረግ እንዳለባት ለሶስት ቀን ከቤቷ ሳትወጣ አሰበችበት ።
ከፖሊስ ሸሽቶ ወደሀዋሳ የሄደው ማሜ ሀዋሳ ከጓደኛው ጋ እየተፍታታ ነው። ሀይለኛ ጠጪ ሆኖል.... ፀፀት እንዲሰማው አይፈልግም..... ሀኒ፣ ሀይሚ፣ በሱ እጅ የተበላሹና ያለቀሱ ሴቶች መካሻ ህይወቱን ያበላሸችውን ሴት ገሏታል። "በቃ ተበቀልኩላቸው! ምን ላድርጋቸው ከዚ በላይ?" ይላል ይጠጣል ይጠጣል......... ሀኒን ሊያገኛት ፈልጎል። በዚ ደሞ ልትረዳው ምትችለው ሀይሚ ነበረች፣ እሱን ደሞ በስካር መንፈስ ሁሉን ነገር ድብልቅልቁን አውጥቶታል። ያለው ምርጫ ሳሚ ነበር....... ለሳሚ የተፈጠረውን ነገር ከመጀመርያ እስከ መጨረሻ ነገረው
"እኔ እስር ቤት ብገባ ና ሀኒ ብትመጣ ንገራት" ብሎ ነው የነገረው።
ሀይሚ ከሶስት ቀን ሀሳብ ቡሀላ ማሜን መበቀል እንዳለበት ወስና ስራዋን ለመስራት በለሊት ከቤት ወጣች። ቤተሰቦቿን ሀኒጋ ልሄድ ነው ብላ ነው የተናገረችው..... ትልቅ ጃኬት፣ ጥቁር ሱሪ፣ ትልቅ ቡትስ ጫማ፣ የወንድሟን ትልቅ ካፖርት፣ በሻንጣዋ ይዛለች። ጉዞ ወደ ሀዋሳ.........
ማሜን ፍለጋ ባደረገችው ፍለጋ መሰረት ያለበትን ቦታ ከነቤቱ አቤል ነግረዋታል። እሱን ለነሱ እንዳይነግራቸው "ሰርፕራይዝ ልታረጋቸው እንዳሰበች፣ ከማሜጋም ለመታረቅ እንዳሰበች፣ ሀኒንም ለማምጣት ማሜ አብሯት እንዲሄድ ስለፈለገች፣" እንደምትሄድ ስለነገረችው በደስታ ነበር ሁሉንም አድራሻ የነገራት። እዛ ከሄደች ቡሀላ አቤል በሰጣት መሰረት ሳሚን ና ማሜን ለሶስት ቀን ተከታተለቻቸው..................
ዛሬ ሀዋሳን ከረገጠች አራተኛ ቀኗ ነው። ስራዋን ልታጠናቅቅ ምሽቱን እየጠበቀች ነው። ከዛ በፊት ግን ለሀኒ አንድ ነገር ማድረግ አለብኝ ብላ ስላሰበች ለአህመድ ስልክ ደወለችለት፤ ድምፃን ሲሰማ አላመነም፣ ጠፍታበት ነበር፣ ልትነግረው ምትፈልገው ነገር ስላለ ከኡስማን ጋ እንዲያዳምጧት አስጠነቀቀችው።
"ምን አልባትም እኔን ከዚ ቡሀላ ላታገኙኝ ትችላላቹ! ስለዚ ስሙኝ" ብላ ጀምራ ስለተፈጠረው ነገር ሁላ ነገረቻቸው........ ዑስሚ በብስጭት "መሀመድ ያለበትን ንገሪኝ" አላት
"ስለሱ ነገ ነግርሀለው። አሁን ለሀኒ ፍጠኑላት" ብላ የደላላውን ስልክ፣ ያለችበትን ሚያቁ ሰዎችን ስልክ፣ ሁላ ሰጠቻቸው። እሷም ሁሉንም ነገር እየደወለች አጣርታ ቀኑን ሙሉ ሀኒን ሲያስሱ እና ሲያፈላልጉ ቆዩ። በመጨረሻም ተሳካላቸው። ሀኒን በስልክ አንድ አረብ ከአህመድ ጋ አገናኛት። ሀኒ አላመነችም ስልኩን ልትዘጋው ፈለገች፤ አህመድ እየደጋገመ "ይቅርታ" ይላታል "እባክሽ ይቅርታ ሀኒ ሁሉ ነገር በኔ ምክንያት ነው የተፈጠረው። የዛን ጊዜ ባልመጣ ይሄ ሁላ አይፈጠርም ነበር። እባክሽ ተመለሺ! እባክሽ!" እየለመናት ነው። ግን እንዴት ብላ ነው አይኑን ምታየው? እንዴት ብላ ነው በሌላ ወንድ የታቀፈው ገላዋን ለሱ ምትሰጠው? ከበዳት !ለመመለስ ፍቃደኛ አልሆነችም። ዑስማን ስልኩን ከአህመድ ተቀበለውና አናገራት ማትመጣ ከሆነ ለእናታቸው እንደሚነግራት፣ እሱም መሀመድ ካለበት ፈልጎ ገድሎ እስርቤት እንደሚገባ በእናቱ እየማለ ነገራት። ምትመጣ ከሆነ ሁሉም ነገር ይስተካከል። እናቷ ይህን ሲሰሙ ግፊታቸው ጨምሮ ሚሞቱ መሰላት..... ኡስሚ እስርቤት እድሜልክ ታስሮ ሲፈረድባት በምናቧ ታያት...... "እሺ መጣለው" አለችው ።

ቀኑ ለምሽቱ ቦታውን ለቋል..... በቃ የቀራት አንድ ነገር ነበር፣ ሀኒን መመለስ። ሀኒ ደሞ ደላላው ደውሎ ነገውኑ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚልካት ቃል ገብቶላታል። ከዚ ቡሀላ ምንም አጠብቅም። ቤተሰቦቿም እሷን አይፈልጉም፣ ወንድሟ አለ። ከቤት ስትመጣ ይዛ የመጣችውን ልብስ ለበሰ፣ ከትልቁ ጫማ ውስጥ የደበቀችውን የአባቷን ሽጉጥ አወጣች። ወደ ማሜ ሄደች........ ከጭፈራ ቤቱ እስኪወጡ ጠበቀች....... ጭር ያለ ቦታ እስኪደርሱ ተከተለቻቸው.........ስክር ብሎ እየተንገዳገደ ነው። ሳሚ ከውሀላው ከአንዲት ሴት ጋ ይጃጃላል........ ፊትለፊቱ ሄዳ ቆመች አላወቃትም!
"ምን ፈለግሽ ደሞ አንቺ ዞርበይ ከዚ!" ፀጥ ብላው ቆመች ሊገፈትራት እጁን አነሳ፣ ወረወረችው በጣም ስለሰከረ ሄዶ ተዘረጋ። ያኔ ኮፍያዋን አወለቀችው ደነገጠ! በጭራሽ ሀይሚ ትሆናለች ብሎ አልገመተም! ሊሸሽ ፈልጎል! ምን ልታረግ እንደመጣች መጠርጠር ሳይጠበቅበት አውቋል። "ስሚ ሀይሚ" ሽጉጡን አወጣችው
"ማታውቂው ነገር አለ! ስሚኝ ተንተባተበ።
ደነፋች! እልህ ያዛት ሀኒላይ ያደረገው ነገር የእሷ ህይወት ፊቷ ላይ ድቅን አለባት። ግንባሩን አለችው....... አላቆመችም እየጮሀች ጥይቱን አርከፈከፈችበት...... ከዛ ወደጭንቅላቷ ወሰደችው........ ስራዋን ጨርሳለች መሞት አለባት ከጥይቱ በፊት ከውሀላዋ ጠንከር ያለ እጅ ቀደማት ፓሊስ! አንድ ያላስተዋለችው ነገር ይህንን ሁላ ስትፈፅም ከአጠገቧ ፓሊስ ካምፕ ነበር። ቦታውም ጭር ያለው እሷ አላወቀችም እንጂ የፓሊሶች ካምፕ በመሆኑ ማንም ሰው ደፍሮ አይጠጋም ነበር.............................

ጊዜው ነጎደ ሀይሚ ቤተሰቧቿ ባደረጉት ጥረት ወደ አ.አ ፓሊስ ጣቢያ ተሸጋግራለች። ዛሬ የመጨረሻው የፍርድ ቤት ቀጠሮ ሚሰጥበት ቀን ነው.........ሁሉም ቦታውን ይዞ ተቀምጧል........ ሀይሚ ያለምንም ክህደት ማሜን እንደገደለችው በራሷ መስክራለች፤ ዳኛው የቀኝና የግራውን ሰምቷ ክስ አንብቦ ጨርሷል...... ውሳኔውን ማሳለፍ ብቻ ነው የቀረው። ሁሉም በጉጉት ነው ሚጠብቀው......... ሀይሚ 25 አመት ተፈረደባት። የሰማችውን ማመን ያቃታት ሀኒ እሪታዋን ለቀቀችው። ሀኒ በድንጋጤ ዞር አለች...... ሀይሚ፣ አህሚ፣ ኡስሚ ችሎቱ ላይ ተገኝተዋል። ስላየቻቸው ደስ አላት። ሲወጡ ተገናኝተው ተቃቅፈው ተላቀሱ........ "ይቅርታ ሀይሚ" አለቻት "ሀኒ" የሚል ድምፅ አላቀቃቸው። ሳሚ ነው ሀኒን ሊያናግራት እንደሚፈልግ ለሁሉም ነገራቸው። ሀይሚ ወደእስር ቤት ስትሄድ እነሱ ሳሚን ተከተሉት..................
በሰሙት ነገር አዝነዋል....... ግን ምንም መፍጠር አይችሉም። ሁሉም ለማሜ አዝነዋል። ተበድሏል! መጥፎ በደል! ሀኒ ሳሚን ጠየቀችው "የት ተቀበረ?" ያደገበት ማዕከል ጓደኞቹ፣ ያሳደጉት ሞግዚቶች፣ ወደዚ መቶ እኛ እንቀብረዋለን። ስላሉ እዚ መቶ ነው የተቀበረው አላት። ቀብሩን ሊዘይሩ ተያይዘው ሄዱ.................

ከአምስት አመት ቡሀላ
ሀዩ የአክስቷን ቤት ለማሻሻጥ ከአሊጋ ወደ ኢትዬጲያ መታለች። ከአምስት አመት ቡሀላ የረገጠቻት ሀገሯ በጣም ናፍቃት ነበር............
441 views08:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-24 11:05:09 ሽሽት ወይንስ በቀል
በመغፊራ ቢንት ፉላን

ክፍል አስራ8
መጨረሻ 4 (ሀይሚ)

በቤተሰቧቿ ለውጥ በጣም ተደንቃለች። በቤታቸው የነበረው ቁጥጥር ሁሉ ቀንሷል...... ከቤት አልወጣም ብሎ በሱሱ የጀዘበው ወንድሟ አባቷ በሼር በሚሰራው መስሪያቤት ውስጥ ዝቅ ብሎ በተላላኪነት ተቀጥሮ እየሰራ ነው። የማታ ትምህርት እየተማረ ቤተሰቡን የሚንከባከብ ጠንካራ ወጣት ሆኗል..... ታናናሾቿም እንደሷ ነፃነታቸውን ተነፍገው ሳይሆን እሷ ከአመታት በፊት ትኖረው የነበረውን ኑሮ እየኖሩ ነው። በዚ በጣም ደስተኛ ናት፤ በሀኒ ግን በጣም አዝናለች..... ምን ማድረግ እንዳለባት እንኳን አታውቅም....... ለማንም እንዳትናገሪ ስላለቻት እንጂ ሁሉንም ነገር ለአህመድ ልትነግረው ፈልጋለች። ሀሰተኛ የውጭ ት/ት እድል ሰርተክፌት አሰርታ፣ ቤተቦቿን ዋሽታ፣ የአረብሀገር ፕሮሰሷን በአጭር ጊዜ ውስጥ ጨርሳ ወደአረብ ሀገር ስለሄደችው ሀኒ ምንም ማድረግ አለመቻሏ ቀንበቀን ውስጧን በፀፀት እየቀጣት ነው። ማሜን ጠልታዋለች፣ "ግን ስላፈቀራት ነው" ብላ ስላሰበች ያንን ያህልል አልፈረደችበትም...... እሷም አፍቃሪ ናትና...... እሷም በሱ ቦታ ብትሆን እንደምታደርገው እርግጠኛ ነበረች። ማንም ዳጊን ሊቀማት አይችልም..... ለዚያውም በዚ ጊዜ...... ለወንድሟ ነግራው፣ ፎቶ አሳይታው፣ ለምርቃቷ እንደሚመጣ እና ከቤተሰቦቿ ጋ ልታስተዋውቀው በጓጓችበት በዚ ጊዜ......... "በቃ ማሜ ጥፋተኛ አደለም! ግን ሀኒ ታሳዝናለች።" ስትል ደምድማለች........
የአራተኛ አመት እረፍት አልቆ በደቤቷ ሰትትመጣ እረፍት ተሰምቷታል። ጊቢውን ጠልታዋለ፣ ሀኒን የሌለችበት ጊቢ ያስጠላል....... ለዳጊ ልትነግረው ብትፈልግም ግን ሀኒ ቃል ስላስገባቻት ለማንም ትንፍሽ አላለችም። "ሁሉንም ጊዜ ይፈታዋል።" ብላ ሁሉንም በውስጧ ይዛ ተቀምጣለች። ዛሬ ዳጊ አልደወለላትም...... "ምን ሆኖ ይሆን?" ብላ ተጨንቃለች። ስትደውል ስልኩ ዝግ ነው። ስራ በዝቶበት ይሆናል ብላ ማታን እየተጠባበቀች ነው.......:መሸ ግን አልደወለም እየጠበቀችው ነው። social media ላይም ብዙ አደለችም እስከዚም ናት፤ በቃ ሁሉም ነገር ያለሀኒ አስጠልቷታል። "ምን አልባት ይደውል ይሆናል" ብላ ስልኳን ትራሷ ውስጥ ከታ እንቅልፏን ተኛች።........ ከለሊቱ 8 ሰዐት የስልኳ ቫይብሬት ቀሰቀሳት፤ "ዳጊ ይሆናል" ብላ ከትራሷ ውስጥ ስታወጣው እሱ አደለም። "ማሜ" ነው ደነገጠች! "ምን ሆኖ ነው በዚሰዐት? ላንሳው? አላንሳው?" እያለች ስልኩ ተዘጋ........ ወዲያው ወዲያው ግን ዳጊ ደወለ። የማሜን ሰልክ ባለማንሳቷ ደስ አላት። አንስታው ቢሆን ኖሮ ዳጊ ሲደውል "ተይዟል" ይለዋል። "በዚ ለሊት ከማንጋ እያወራው ነው" ልለው ነበር? የእፎይታ ስሜት ተሰማት........ ስልኩን አነሳችው፤ ቀኑን ሙሉ ስላልደወለ እንደማኩረፍ ነገር ብላ ነው።
"ሄለው" ያለችው ረጅም ሳቅ ተሰማት።
"ሀኒን ተበቀልኳት አ? ሀዩንስ ብትይ? አረ ምን እነሱን ብቻ አንቺንስ?" ረጅም ሳቅ.......... ግራ ገባት ስልኳን ደግማ አይችው። የደወለው ዳጊ ድምፁ ግን የማሜ ነው....... አልገባትም! "የት ተገናኙ ቆይ?" ግራ ገባት......... ሜማ ጥንብዝ ብሎ መስከሩ ከድምፁ ያስታውቃል። "ሰክረሀል? የት ነው ያለሀው?" አለችው
"አልሰከርኩም! እኔ አልሰከርኩም!" ይስቃል..... "ባይሆን ስሚ፣ምስኪኗ ልጅ! አፍቃሪዋ ልጅ!" ረጅም ሳቅ..... "ማን እነደሚያናግርሽ ታቂያለሽ? የሀኒ ማሜ፣ ያንቺ ዳጊ፣ ዋዋዋዋው..... ዳጊ! ተሳክቶልኛል ባክሽ! ሰው እንዴት አራት አመት ሙሉ ይሸወዳል? ሀሀሀሀሀ....... ሀይሚ ለማንኛውም ተስፋሽን ቁረጪ! እኔ አልመጣም! ግን ግን የላኩልሽ ፎቶ ልጁ አያምርም በናትሽ? ምን አለ እሱን ብመስል? ግን ማን ያምራል?" ደንግጣለች........ "አሁን እኔ እስር ቤት ሄጄ እጄን ልሰጥ ነው። ገደልኳት ኮ! እማማ ዝናሽን ገደልኳት።" ረጅም ሳቅ......... "ስለዚ ያው እንዳልጠፋብሽ ልንገርሽ ብዬ ነው። ሀሀሀሀ.......
ስልኳን ለቀቀችው........ የሰማችውን ማመን አልቻለችም። ግራ ገባት! ይህንን ሁላ አመት ማሜ ነበር ሲያታልላት የነበረው። አጠገቧ ሆኖ፣ አብራው እየበላች፣ አብራው እየዋለች፣ አላመነችም........... እንባዋ ከአይኗ ኩልል እያለ ወረደ...........


ክፍል አስራ9 ይቀጥላል

በTelegram Channel ማግኘት ለምትፈልጉ
https://t.me/bintfulen
ለአስተያየት
https://t.me/AmMegfi

Graphics designed by
https://t.me/joinchat/PpyhlRRD7XZkYTg8
342 views08:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-19 14:00:06 ሽሽት ወይንስ በቀል
በመغፊራ ቢንት ፉላን

ክፍል አስራ7
መጨረሻ 3 (ማሜ)

ባደረገው ነገር ቅንጣት ያህል ፀፀት አልተሰማውም። ኩራት ኩራት ብሎታል.... ትልቅ ጀብድ የፈፀመ ነው ሚመስለው.... በቃ ስለ ሀዩ ስለሀኒ በጭራሽ ማሰብ አይፈልግም። ሀዩን እዛ ሁላ ተማሪ ፊት አዋርዷት፣ መራመድ እንኳን አቅቷት፣ በማሜ ስራ የተበሳጩ ሀዩን ሚያውቋት ልጆች ደግፈው እያባበሉ ከመናፈሻው ጊቢ ይዘዋት ከወጡ በውሀላ የት ትሂድ? ምን ትሁን? ምንም አያውቅም። ደሞ ማወቅም አይፈልግም። ስለምን ብሎ ያውቃል....... ደሞ የፈለጋት ለበቀል ነበር፣ ተበቅሎ ጨርሷል.......
ሀኒንም ቢሆን የዛን ቀን አልጋ ላይ ተኝታ፣ አልግጦባት ከወጣ ከትንሽ እርምጃ ቡሀላ ከተከተለው የመኝታ ቤቱን ሆቴል ካናገው ጩሀቷ ቡሀላ አይቷትም፣ ድምጿንም ሰምቶ አያቅም። ሀይሚ የሀኒን ጩሀት ሰምታ ወደሷ ስትሮጥ አይቷል....... በቃ ከዛ ቡሀላ ሁለቱም የሉ። social media ላይም አይታዩም..... ጊቢ ውስጥም.....ክፍልም አይገቡም..... እሱም አልፈለጋቸውም! ግን ብዙ ተማሪዎች እየመጡ ይጠይቁታል! "አላቅም ከኔጋም አይገናኙም"ነው መልሱ........ ሀና ስልካቸው ዝግ እንደሆነ ነግራዋለች። ግድ ያልሰጠው ቢመስልም ሀኒን ግን አለማሰብ አልቻለም። ሰራው አልፀፀተውም...... ግን እሷ ናፍቃዋለች። አንድ ቀን ወደ ክፍል ሲገባ ሀይሚን አያት። ደነገጠ! ሀኒን በአይኑ ፈለጋት.....እሷ ግን የለችም! ሀይሚን ሊጠይቃት ፈለገ፣ "ግን ምን ብሎ?" እሱ ሲገባ ክፍሉን ለቃ ወጣች። ልታየው እንኳን እንደማትፈልግ ተረድቷል..... ዝም አላት። በዚ ሁኔታ የአራተኛ አመት የመጀመርያ ሴሚስተር ት/ት አለቀ። ሀኒን ሳያያት፣ ስለሷ ሳይሰማ፣ ግን ሁለተኛ ሴሚስተር ላይ እንደምትመጣ እርግጠኛ ነበር።
ወደ አ.አ መሄድ አልፈለገም...... ከሳሚ ጋ ወደ ሀዋሳ ሄደ፤ እዛ ቆይቶ ወደ ጊቢ ተመለሰ። አሁንም ግን ሀኒ የለችም...... ሀይሚ ብቻዋን ናት። ግራ ገባው...... ለመጀመርያ ጊዜ በስራው ተፀፀተ "በቃ ሀገሯ ጋ ሄዳ ነው።" ደመደመ ከእውነታው ላለመጋፈጥ ሸሸ.....ግን አልሆነለትም በየደቂቃው ያስባታል...............
አራተኛ አመት አለቀና ወደአምስተኛ አመት መሸጋገሪያው ክረምት መጣ። አሁንም ወደ ሸገር መሄድ አልፈለገም። ሀዋሳ ተመችታዋለ፤ እዛ ማንም አያቀውማ! ወደዛ እንደሚሄድ ሚያቀው እሱና ሳሚ ናቸው። ወደዛ ሚሄዱበትን ትኬት ለመቁረጥ ወደከተማ በወጡበት፣ ከአ.አ ተደውሎ "አሳዳጊው ወይዘሮ ዝናሽ በጣም እንደደከመች እና በጣም እንደምትፈልገው" ተነገረው። ደንግጧል! እናቱን የሚያጣ መሰለው..... ሳያያት ብትሞት ፀፀቱን አይችለውምና ሳሚን "ልብሴን ሙሉ አንተ ይዘሀው ሂድ! እኔ እዛ ያለውን ነገር ጨራርሼ እመጣለው!" ብሎት ወደጊቢም ሳይመለስ እዛው ባገኘው መኪና ተሳፈረ።

ወደ ማሳደጊያው ጊቢ ሲገባ እንደተባለው ነበር። እንደ እናትም እንደ አባትም ሆና ያሳደገችው ወይዘሮ ዝናሽ ደክማለች። ሀኪሞቹ ለማዳን ስላልቻሉ "ወደቤት ውሰዷትና ተንከባከቧት" ስላሉ ነው ወደዚ ተመልሳ የመጣችው። ተንደርድሮ ሄዶ አቀፋት። ስታየው ፈገግ አለች.... ሊጠይቋት ተሰብስበው የነበሩ ሰዎች ሁሉ ክፍሉን ለቀው ወጡ።
በእጇ ይዛው የነበረውን የማሜን የአንገት እያሳየችውና በእጁ እያስጨበጠችው ንግግራን ጀመረች "ይሀውልህ የኔ ልጅ ይህ የአንገት ያንተ ነው። ገና ወደዚ ማሳደጊያ ሰትመጣ አንገትህ ላይ ተንጠልጥሎ ነበር፣" ከዚ በፊት ስለነገረችው ደግማ ለምን እንደምትነግረው ግራ ገብቶታል! "ይሀውልህ እኔ የነገርኩህ ታሪክ እውነቱ ትንሽ ነው። በጊዜው ልጅ ስለነበረክ እና አብዝተህ ትጠይቀኝ ስለነበረ አብረውኝ እናንተን ከሚንከባከቡ ሞግዚቶች ጋር ተመካክሬ እንጂ ስለአንተ ምንም የማውቀው እውነት የለም፤ ይህንን ያደረኩት ለክፋት አደለም ያኔ ልጅ ነበርክ አላቅም ብልህም የባሰ ትጨነቃለህ ብዬ አስቤ ነው። አሁን ግን ትልቅ ሰው ስለሆንክ ቤተሰቦችህን ማግኘት አለብህ። እስክትመረቅ እየጠበኩ ነው ያልነገሩክህ፣ ግን ይሀው ካንተ ምርቃት የኔ ሞት ቀደመ.... እባክህ ይቅርታ አድርግልኝ...... ልጄ እያለች እያለቀሰች ለመነችው።
የሰማውን ማመን አልቻለም ከልጅነቱ ጀምሮ የተጫወተባቸውን ሴቶች አሰበ፣ ሀዩን አስታወሰ.... ከሁሉም ግን ሀኒን አሰባት..... ያፈቀራትን ሴት ምን እንዳረጋት አስታወሰ..... ዘገነነው፣ በውሸት ታሪክ ህይወቱን ሙሉ ያበላሸችው ሴት እያለቀሰች ይቅርታ እያለችው ነው። ሁሉም በሷ ምክንያት ነው፣ ከሁሉም ሴቶች በላይ የሀኒ ነገር አንገበገበው። ከተቀመጠበት ወንበር አጠገብ ያለው አልጋ ላይ የተኛችውን ሴት አብዝቶ ጠላት....... ስሜቱን መቆጣጠር አልቻለም። የተኛችበትን ትራስ ጎትቶ ሲጣጣር የነበረውን ትንፋሿን ቆረጠው። ፀጥ አለች፣ ትራሱን ወደዛ ወርውሮ እዛው ጥሏት ወጣ....................
ኡኡኡኡኡ ዝናሽ ሞተች የለቅሶ ድምፅ አስተጋባ እሱም ጊቢውን ለቆ ወጣ ሸሸ...............


ክፍል አስራ8 ይቀጥላል

በTelegram Channel ማግኘት ለምትፈልጉ
https://t.me/bintfulen
ለአስተያየት
https://t.me/AmMegfi

Graphics designed by
@amiGFX
315 views11:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-18 11:24:17 ሽሽት ወይንስ በቀል
በመغፊራ ቢንት ፉላን

ክፍል አስራ6
መጨረሻ 2 (ሀኒ)
ልትመረቅ ሁለት አመት ብቻ ቀርቷታል። የአህመድ ሙሽራ.... የእናቷን ምኞት ልታሳካ ሁለት አመት ብቻ..... ጎትታ ብታሳልፋቸው ደስ ይላታል።
መመረቋን በጉጉት ሚጠብቁት እናቷ ወደ አራተኛ አመት ለተሸጋገረችው ልጃቸው የሚያስፈልጋትን ነገር እያዘጋጁላት ነው። እሷም በፊናዋ ከጊቢ ስትመጣ ከጓደኞቿ ጋር በጣለችው እጣ መሰረት የተጣለባትን ስጦታ ለመግዛት ሽርጉድ እያለች ነው። ስጦታውን ግን ለአቤል ብቻ ማድረግ አልፈለገችም፤ ሶስትአመት አብረዋት ለቆዩ ጓደኞቿ ማስታወሻ እንዲሆን ብላ ለአምስቱም መስጠት ፈልጋለች። ከነአህመድ ጋ በተስማማችው መሰረት ለሀይሚ የአንገት ሀብል፤ ለማሜ ሸሚዝና ሰዐት፣ ለተቀሩት ለሶስቱ መፅሀፍ ገዝታለች።............ አህመድ እና ማሜ ጥሩ ተቀራርበዋል ማሜ ሀኒጋ ሲደውል አንድላይ ካሉ ያወራዋል እሱን በመጥፎ መጠርጠሩ በጣም ፀፅቷታል።

ሀሙስ እና አርብ ስለተጠሩ ሁሉም ተነጋግረው በተስማሙት መሰረት ሀሙስ ገብተው አርብ ቀደም ብለው በጠዋት መመዝገቢያው ጋ ተገናኝተው የምዝገባ ሂደታቸውን አጠናቀዋል። የስጦታቸው ቀን ደሞ ነገ ነው። ሁሉም ስጦታውን ይዞ የማሜን ልደት ያከበሩበት ቦታ ሊገናኙ ሰዐት ቆርጠዋል........ ሁሉም ማን ለማን ምን ስጦታ ሊሰጥ እንደሆነ ሊያይ ቋምጧል።
ሀይሚ አምሽታ ስለተኛች ከእንቅልፏ በመከራ ነው የተነሳችው ሀኒ ለሁሉም ስለሆነ ስጦታ የገዛችው እስክትሰጣቸው ቸኩላለች። የተቀጣጠሩት 9 ሰዐት ነው ያሰቡት አዳር ነው። ልክ እንደማሜ ልደት......... ሀይሚና ሀኒ ብዙም አልፈሩም ባለፈውም ምንም ስላላጋጠማቸው ከነ ማሜጋ መሆኑ ነፃነታቸውን አልወሰደውም።
ሁሉም አምሮባቸዋል፤ ሁሉም በእጃቸው ፌስታል አንጠልጥለዋል።ማሜ ግን ባዶ እጁን ነው................
ቤት ውስጥ ያሉት ስድስቱ ብቻ ነበሩ እንደለመዱት ቤቱን አዘግተው ጭፈራውን አድምቀውታል።
ድንገት ዲጄው ዘፈኑን አቀመው። ሁሉም ድንገት ዘወር አሉ። ማሜ ማይኩን ይዞ ቆሟል። "ዛሬ ቀናችን ነው ጓደኞቼ በጣም ነው ምወዳቹ ማከብራቹ" ............. ብዙ አወራእና የስጦታውን ዝግጅት አስጀመረው። ሁሉም ፌስታሉን ይዞ መጣ፤ ከሁሉም የሀኒ ትልቅ ነበር ።ሁሉም ስጦታውን ይሰጣጥ ጀመሯል። ሁሉም ጨርሶ ሀኒ እና ማሜ ቀ። ማሜ ስጦታውን ተቀብሏል ግን አልሰጠም....... ሀኒ አልተቀበችም አልሰጠችም....... ራመድ ብላ ሄደ ማይኩን ተቀበችና "ሁላችሁንም ወዳቹሀለው አንዳቹን ከአንዳቹ ማስበለጥ ስለማልችል ለሁላቹም ነው ስጦታ ያመጣሁላቹ" ቤቱ በፋጨትና በጩሀት ተናጋ.... ዲጄው ዘፈኑን ለቀቀው። ሁሉም አቅፈው እየሳሙ ስጦታቸውን ተቀበሏት። ማሜ ግን እዛው ቆሟል ሄዳ ያመጣችለትን ሸሚዝና ሰዐት ሰጠችው። ተቀበላት.... "ከዛ በጆሮዋ ስጦታሽን ቡሀላ ማንም ሳያይ" ብሎ አንሾካሾከላት። ፈገግ ብላ አንገቷን ነቅንቃ እሺታዋን ተቀበለች።
ከእንቅልፏ ያባነናት የተሰማት ሀይለኛ የህመም ስሜት ነው። ምኗን እንደሚያማት አታውቅም። ደክሟታል..... ሰውነቷ ሙሉ ዝሏል..... ሁሉ ነገሯ ተሳስሮባታል..... እግሯንም እጇንም ማንቀሳቀስ አልቻለችም....... ቀስ ብላ ወደ ጓኗ ዞረች.... ማንም የለም ብቻዋን አልጋ ላይ ተዘርራለች። ምን ልታረግ መጣች? የማታውን ክስተት ለማስታወስ እየተፍጨረጨረች ነው። ስጦታ ሲሰጣጡ ሲጨፍሩ ከዛ ሲጠጡ ...... ከዚ በላይ ማስታወስ አልቻለችም....... ድንገት በሩ ሲከፈት ሰማች። ቀና ማለት አልቻለችም። አጠገቧ ማሜ ቆሞል ፊቱ ተቀያይሯል አይታው ማታቀው አይነት አስፈሪ ፊት አየች። ተፈጣጡ፤ ድንገት ከጣራ በላይ ሳቀና "ስጦታሽን ወደደድሽው?" አላት "ማለት?" አለችው ደንዝዛለች አሁንም ጮክ ብሎ ሳቀ። ይሄ ያንቺ የውሸትሽ ውጤት ለባልሽ ደሞ ጥርጣሬውን ማረጋገጫ ነው። እሺ! ደደብ ውሸታም" ብሎ በተኛችበት ጥሏት ወጣ። ከመቅፅበት መጥፎ ነገር እንደተፈጠረ ጠረጠረች። እንደምንም ተጣጥራ ከላይ ላዮ ያለውን ብርድልብስ ወረወረችው። ጥርጣሬዋ ልክ ነበር....... "ማሜ
ደፍሮኝ? አብሬው ተኝቼ? ወይስ?" ስልኳን ልታነሳ ዞር ስትል የኪኒን ብልቃጥ አየች። ትዝ አላት ስጦታሽን ልስጥሽ ብሎ መኝታ ቤት ይዟት ገብቶ የሰጣትን መጠጥ አስታወሰች።
አዎ ማሜ ለባሏ ያቆየችውን ንፅህናዋን እሱ በመድሀኒት አደንዝዞ ወስዶባታል ...........
"ኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡ.........." ከጣራ በላይ

ክፍል አስራ7 ይቀጥላል

በTelegram Channel ማግኘት ለምትፈልጉ
https://t.me/bintfulen
ለአስተያየት
https://t.me/AmMegfi

Graphics designed by
@amiGFX
272 views08:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-16 11:33:40 ሽሽት ወይንስ በቀል
በመغፊራ ቢንት ፉላን

ክፍል አስራ5
መጨረሻ 1 (ሀዩ)
ከአክስቷ ልጅ አሊ ጋር ለማሜ ክረምት ላይ ለእረፍት ሲመጣ እውነቱን ማወቅ እንዳለበት ወስነዋል። በዚህም ሀዩ ለመናገር ስለፈራች ለማሜ እውነቱን አሊ እራሱ ደውሎ እንዲነግረው ተስማምተዋልና የማሜን መምጣት በጉጉት ነበር ሲጠብቁ የነበረው............ እንዳፈቀረችው እርግጠኛ የሆነው ማሜ የበቀሉን 90% ስራ አጠናቆ በድል በመወጣቱ ውስጡን ኩራት እየተሰማው ነው። አሁን የቀረው አንድ ነገር ብቻ ነው....... ከሶስት አመት በፊት የ12ኛ ክፍል ተማሪ እያለ ከጓደኞቹ በሰማው የሷ ዝና መሰረት "ማን ስለሆነች ነው?" በሚል ንቀት "እኔ አስቁሜ አናግራታለው!" ብሎ በጉራ ከት/ት ቤቱን ከግማሽ የሚበልጡ ተማሪዎች ሰብስቦ ተወጣጥሮ ሄዶ ሲያናግራት አዋርዳው እንደሄደች እሷንም ህዝብ ሰብስቦ ማዋረድ!.......... የሀዩ ነገር አብቅቶ ውስጡን ላነደደችውና ላስለቀሰችው እንስት ብዙ ስራ እንደሚጠብቀው ስላወቀ የሀያትን ነገር ከዚ ክረምት ሌላ ጊዜ ሊሰጠው አልፈለገም። ከሀዩ "አፈቅርሀለው" ሚለውን ቃል ብቻ ስለሆነ ሚፈልገው ለሱም ትንሽ መስዋዕትነት ብቻ እንደሚያስከፍለው ስለሚያውቅ በድል እንደሚወጣው በራሱ ተማምኖ ወደ ሸገር አቅንቷል። ሸገር ላይ የጠበቀውም ስራውን በእጥፍድርብ የሚያቀል ስራ ነበር............
ወደ ሸገር በገባ በሶስተኛው ቀን ስራውን በእጥፍ ያቀለለት ነገር ተከሰተ። አሊ ደውሎ ከሀዩ ጋ ስላወሩት ነገር፤ ሀዩ ምን ያህል እንዳፈቀረችውም፤ ቤተሰቡ ምን ያህል እንደወደደው እና አሊ ስለወደፊት ህይወታቸው ስላሰበው ነገር ሁሉ ነገረው። ማሜ ደስ አለው! የፈለገው ነገር ተሳካለት! አሊ ጋ ባለማመን አይነት አስመሰለ። ይሄ እንደማይገባው ምናምን ቀባጠረ፤ ተሳካለት! አሊን "አንድ ነገር ላላስቸግረህ ይህን ነገር መስማት ምፈልገው ከሀዩ ራሷ ነው። ካለበለዛ አላምንም።" ብሎ ለመነው አሊ በዚ ምንም ስጋት እንዳይገባው ሁሉንም እሱ እንደሚጨርስለት ቃል ገባለት።
ማሜ የዛን ቀን በደስታ ሲጠጣና ሲጨፍር አደረ ነገ ከነገ ወድያ ብዙ ስራ ይጠብቀዋል...........
ሀዩም በበኩሏ አሊ ከማሜ ጋር ያወሩትን ሙሉ ቀድቶ ልኳላት ስለነበረ በደስታ ስትፈነጥዝ አድራለች። ማሜን ግን ማግኘት ፈርታለች...... አሊ እያደፋፈራት ነው።
ማሜ በጠዋት ነበር ስራውን የጀመረው፤ ከተኛበት አልጋ ተስፈንጥሮ ተነስቶ እስኪሪቢቶ እና ወረቀት ፈልጎ አመጣ። በፊት አብረውት ሲማሩ የነበሩ፡ በተለይ ደሞ በሱ ስር ሲያንዣብቡ የነበሩትን ሁሉ እያስታወሰ ፃፈ። በተለይም ደሞ ያኔ ሀዩ ሰድባው ስትሄድ በዙርያው ቆመው ሲያሽካኩበት የነበሩትን ተማሪዎች አሰበ... ፃፈ። ከነዛ ከተሰበሰቡ ሰዎች ውስጥ ደሞ ስድስት ተማሪዎችን ለይቶ አወጣ። ማህሌት፣ ኢክራም፣ እዩኤል፣ አሚር፣ ቃል እና ጌች። እዚ እልህ ውስጥ እንዲገባ ያደረጉት እነሱ ናቸው። እሱም ቃል ገብቶላቸዋል። የፈለገ ጊዜው ይረዝማል እንጂ በነሱ ፊት እንደሚያዋርዳት ምሎ ነግሯቸዋል። መገኘት አለባቸው!። ብዙዎቹን social media ላይ ያገኛቸዋልና ከአስር ቀን ቡሀላ አብረው የተማሩ ተማሪዎች ፕሮግራም እንዳለ እና ከድሮ ት/ት ቤታቸው ጀርባ 7 ሰዐት ለይ እንዲገናኙ እና የተለየ ሰርፕራይዝ እንዳለ ነገራቸው። ብዙዎቹ በደስታ ፍቃደኛ እንደሆኑ እና እንደሚያግዙት ቃል ገብተው ስራቸውን ጀምረዋል። ወደ ጊቢ የሄዱት ለእረፍት ስለመጡ፤ አ.አ ያሉትም ብዙም ስላራቁ ለመገናኘት አልተቸገሩም። ሁሉም በየፊናው "ማን ምን ሆኖ ይሆን? ማን አምሮበት? ማን አስጠልቶ? ማን ተመችቶት ይሆን?" እያለ ያሰላስላል። ከሁሉም በላይ ያጓጓቸው ግን ለማንም ያልተነገረው ሰርፕራይዝ ነበር...........
ማሜ ሀዩን ሰበብ እየፈለገ እየቀጣት ነው። አሊ ስለነገረው ቅር እንዳለው አስባለች። ልታገኘው ብትሞክርም ከ10 ቀን ቡሀላ ፕሮግራም እንዳለበት እና ለሱ ብዙ ስራ እንዳለበት እየነገረ ይቀጣታል። ይህንን ያስተዋለው አሊ ማሜን ደውሎ ሲያናግረው "እሷን ሰርፕራይዝ ለማድረግ ፕሮግራም እያዘጋጀ" እንደሆነ እና "የዛን ቀን እንደምታፈቅረው መስማት እንደሚፈልግ አጥብቆ ነግሮታል!" ነገሩ ንገራት አትንገራት የሆነበት አሊ እህቱ መጨነቋን አይቶ እና የዛን ቀን እንደምታፈቅረው ካልነገረችው ነገሩ ይላሻል ብሎ ስላሰበ ለሀዩ ነግሯታል።

በጠዋቱ እንደጨረቃ አብርታለች፤ ማሜ ጋር ቀጠሮ አላት..... ቀጠሮውን እሱ አስቀድሞ ባይነግራትም አሊ ስለነገራት ለፕሮግራሙ ይመጥናል ያለችውን ልብስ ለብሳ ያለ ወትሮዋ ተቀባብታ ዘንጣ 9ሰዐትን እየጠበቀች ነው። አስርጊዜ ሰዐቱን ታየዋለች፤ እቤታቸው ላለችው ኢልሀም አስር ጊዜ "አምሮብኛል ግን?" እያለች ትጠይቃታለች.... የመሄጃ ሰዐቷ 15 ደቂቃ ሲቀረው ልቧ በፍርሀት ሲደለቅ ይታወቃታል። ውስጧን ማታቀው ፍርሀት እየወረራት መንገዷን ጀምራለች..............
የሷን መምጣት በጉጉት ሚጠብቀው ማሜ የመናፈሻውን መድረክ በቀይ አፉፋ አድምቆታል። ከሰባት ሰዐት ጀምሮ የተሰበሰቡት ጓደኞቹ የሰርፕራይዙ ሰዐት ስለደረሰ ሰብሰብ አድርጓ እንዲደበቁ ነግሯቸው። ችምችም ካለው ዛፍ ጀርባ ተሰግስገዋል........ ማሜ ለተወሰኑ ጓደኞቹ ነገሩን ስለነገራቸው ባለማመን አይነት ነበር ሲጠብቁት የነበረው።
የተሳፈረችበት ራይድ መኪና በሩ ላይ ስለጣላት አመስግና ሂሳቧን ከፍላ ወደመናፈሻው ገባች። በቀይ አፉፋ ካሸበረቀው ዛፍ ፊት ለፊት ፈገግ ብሎ ቆሟል፤ ያየችው ከጠበቀችው በላይ ነው። ተንደርድራ ሄዳ አቀፈችው። ለረጅም ደቂቃ ካቀፈችው ቡሀላ ከተደደገፈችው ደረቱ ቀና ብላ በስስት እያየችው "አፈቅርሀለው" አለችው ድምጿን ደግማ ስትሰማው ደነገጠች። የለበሰችው ልብስ ላይ ማይክራፎን ነበር። አላስተዋለችውም............ በዛው ቅፅበት የማሜ የፌዝ ሳቅ ተሰማት፤ እሱንም ብዙ ድምፃች ተከተሉት...... ያየችውን ማመን አልቻለችም! "ሰርፕራይዝ" የሚለው ቃል ከገባችበት አባነናት። ሁሉንም ታውቃቸዋለች አብረዋት ተምረዋል፤ ከሁሉ በላይ ያስደነገጣት ማሜ በእጁ የያዘው ሻምፓይን ነበር። በደስታ ከፍቶ ወደ ጉሮሮው ሲያንደቀድቀው አላመነችም....... ሁሉም ነገር ጨለመባት ደንዝዛ ቆመች እየሆነ ያለው ግራ አጋባት........ የማሜ ሳቅ፣ መጠጥ፣ አብረዋት የተማሩ ጓደኞቿ፣ ...........ምንም አልገባትም ...........
"ጀግና ነህ! ተበቀልካት" የሚለው ድምፅ ሁሉንም ነገር በቅፅበት ገለፀላት። ውሸት መሆኑን አመነች። ሳታስበው እንደተሸነፈች ገባት። እግሯ ተንቀጠቀጠ መሄድ አቃታት.......
"በቀል ደስ ይላል ሀሀሀሀሀሀሀሀሀ" የማሜ ድምፅ ነው።


ክፍል አስራ6 ይቀጥላል

በTelegram Channel ማግኘት ለምትፈልጉ
https://t.me/bintfulen
ለአስተያየት
https://t.me/AmMegfi

Graphics designed by
https://t.me/joinchat/PpyhlRRD7XZkYTg8
254 views08:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-15 11:36:39 ሽሽት ወይንስ በቀል
በመغፊራ ቢንት ፉላን
ክፍል አስራ4
ከእውነታው እየሸሸ ነው። በፍፁም እውነታውን መቀበል አልፈለገም። ሀኒ ለሱ ውሸታም ናት! ከሌሎች ሴቶች ምትለይበት ምንም ነገር የለም። በቃ ባያት ቁጥር ውስጡ ሲነድ ይታወቀዋል። ብዙ ሴቶች ላይ ተጫውቶ በሷ መሸነፉ ያበግነዋል። መሸነፍ አይፈልግም ለዚያውም በሴት!
አንድቀን በጓደኞቹ ፊት አዋርዳ፣ አርክሳና ሰድባ ጥላው የሄደችውን ሀዩን እንኳን ከአመታት ቡሀላ እልሁ አልወጣ ብሎት ለበቀል እንዴት እያዘጋጃት እንደሆነ አሰበ። በፍፁም በፍፁም መሸነፍ የለበትም። ያሸነፈውን ባሸነፈው ልክ መቀጣት አለበት። እሱን ማሸነፍ እራስን ወጥመድ ውስጥ መክተት ነው።
ትንሽ ረገብ ብሎለት የነበረው ሱሱ ሁሉ ተነስቶበታል፤ የሴት ስቃይ ሱስ....... ሀኒ አህመድን ካስታዋወቀችበት እለት ጀምሮ ብዙ ሴቶችን ይዞ ተኝቷል። ብዙ ሴቶችን አበላሽቷል። ሴቶች ሁሉ እሷን ነው ሚመስሉት። "ሀናን እና እናቴ አንድ ናቸው! እናቴን ባላገኛት በሷ ምትክ ብዙዎችን ቀጥቻለው! ቀጥላለው! ሀኒን ግን እራሷን ካልቀጣኋት አላርፍም።" ብሎ ቆርጦ ተነስቶላታል። ይህንን የበቀል ሴራውን ማንም እንዲያውቅበት አልፈለገም። ሀኒም ብትሆን እንደጠላት ማወቅ የለባትም። ከበፊቱ የበለጠ እየቀረባትና እያጠመዳት ነው። በምን እንደሚበቀላት ግን እስከአሁን አላወቀም..............
በበቀል ወጥመዱ ሰተት ብላ የገባችለት ሀዩ ቤተሰቦቿ በሙሉ ወደ መጡበት ተበታትነዋል። የአክስቷ ልጆች አብራቸው እንድትሄድ ቢለምኗትም "የጀመርኩትን ት/ት ሳልጨርስ አልሄድም" በሚል ሰበብ ቀርታለች። አሊ የቀረችበትን ምክንያት ስለሚያውቅ አላስጨነቃትም። ማሜን ወዶታል! እህቱ ጥሩ ሰው ላይ እንደወደቀች ነው ያሰበው። ስለዚ አንድ ነገር ለራሱ ቃል ገብቷል። ማሜ ት/ት ሲጨርስ ቤቱን በስሙ ሊያዞርለትና እህቱን ሊድርለት.......
ቀን ማታ ድምፁን ሳትሰማ አትውልም፣ አታድርም። አስርጊዜ ትደውልልለታለች። ያወራታል! እንዳፈቀረችው 100% እርግጠኛ ናት። ልትነግረው ፈልጋለች ግን ፈርታለች። ያፈቅረኛል ብላ እራሷን አሳምናለችና ከሱ እስኪመጣ እየጠበቀች ነው። ደስተኛ ናት! እናትና አባቷን ወስዶ አክስቷን እና የአክስቷን ልጆች ሰጣት። አክስቷን ሲወስድ ደሞ ማሜን...............

የመመረቂያ ጊዜዋ ርቋባታል በዳጊ ተስፋ መቁረጥ አልፈለገችም። መጠበቁን መርጣለች...... እስከምርቃቷ ቀን ብቻ! ከዛ ግን ካልመጣ ልትተወዉ ምላለች። ስታፈቅርም ስትፈቀርም የመጀመርያዋ ነው። ማጣቱ ምን ያህል ሊጓዳት እንደሚችል አስባለች። ለአንድ ቀን እንኳን ካኮረፋት እንዴት እንደምትሆን ታቀዋለች፤ ከተዋት ወይ ከተወችው ት/ት ማቆሟ እንደማይቀር ታውቃለች። ይህ ደሞ መሆን የለበትም! "በማዕረግ ትመረቃለች" ብለው ሚጠብቋትን ቤተሰቦቿ "በማዕረግ መመረቅ ባልችል እንኳን ጋውን ለብሼ ማየት አለባቸው" ብላ ስላሰበች ለሷም ለቤተሰቦቿም ስትል ታምነዋለች፣ ትጠብቀዋለች።......

የሶስተኛ አመት ትምህርታቸውን ጨርሰው ሁሉም ወደቤታቸው ሊሄዱ ዝግጅት ላይ ናቸው። ሀኒ አህመድን ለማግባት ሁለት አመት ብቻ እንደቀራት ስታስብ በደስታ ጮቤ ትረግጣለች። እሱም እንደዛው.........
ከቤታቸው ሲመለሱ ሁሉም ጓደኛሞች ስጦታ ሊሰጣጡ እጣ ጥለዋል። አምስት ስለሆኑ እጣው እኩል እንዲደርስ አንድ ሰው እንደሚያስፈግ ስላሰቡ ሀዩ መጀመርያ ወደ ጊቢ ስትመጣ fb ላይ የተዋወቀሻትን የሀዋሳዋን ሀና ሊያስገቡ ወስነዋል። በዚህም መሰረት እጣው የደረሰው ማሜ ለሀ፤ ሀኒ ለአቤል፤ አቤል ለሀይሚ፤ ሀይሚ ለሳሚ፤ ለሳሚ ማሜ፤ ለማሜ ሀና..............
ማሜ ለሀኒ እሱ እንዲሰጥ ያደረገው እራሱ በሰራው ተንኮል ነው እንጂ ለሀኒ ስጦታ እንዲሰጣት የደረሰው አቤል ነበር።
የማሜ ስጦታግን ምን ይሆን?......


ክፍል አስራ5 ይቀጥላል

በTelegram Channel ማግኘት ለምትፈልጉ
https://t.me/bintfulen
ለአስተያየት
https://t.me/AmMegfi

Graphics designed by
https://t.me/joinchat/PpyhlRRD7XZkYTg8
226 views08:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ