Get Mystery Box with random crypto!

በመገፋት ውስጥ ለካ ፍቅር አለ........ ሰው እንዴት እየተገፋ ያፈቅራል? ተው ሲባል አይተውም | ኹሉድ ✍️

በመገፋት ውስጥ ለካ ፍቅር አለ........ ሰው እንዴት እየተገፋ ያፈቅራል? ተው ሲባል አይተውም እንዴ.............
እውነት እኔ ለሱ የምገባ ሰው አይደለሁምና ነው? "እኔን ተይኝ" ያለኝ ቀለል አድርጎ "እኔን እርሺኝና የራስሽን ኑሮ ኑሪ" ያለኝ?
ሰርክ አዲስ ነኝ! ንግግሩ ጆሮዬ ላይ ያቃጭላል፤ ሳስበው ልቤ ይቆስላል..........
"ወድሻለው! የኔ ሁኚ!" ባለበት አንደበቱ "ሂጂ" ሲለኝ እንዴት አልቁሰል?............
"ሂጂ!" ወዴት ልሂድ?......... ላንተ ብዬ ወደተውኳቸው እልፍ አእላፍ ሰዎች?............ ወይስ አንተን ለማግኘት "ከቤት አትውጪ" እያለችኝ የሷን ትዕዛዝ ጥሼ ወጥቼ ወደተበሳጨችብኝ እናቴ?.......... ወይንስ "ዛሬ ከዚ በር ታልፊና ወይ እኔ ወይ አንቺ!" ብሎ ዝቶብኝ እሱንም እኔንም ትቼ ወደአንተ ከንፌ ወዳኮረፈኝ አባቴ?.......... እኮ ወዴት ልሂድ? "ምንሄድበት ቦታ አለ የትም አትሂጂ" ብላ ቀጥራኝ ልክ አንተ ነይ ስትለኝ እሷን ትቼ ወደአንተ በርሬ መጥቼ ከኔጋ ቀጠሮ መያዝ ያታከታት እህቴጋ ነው?.......... ወይስ "መንገድ ላይ ከወንድ ጋር ባይሽ!" ብሎ አስፈራርቶኝ ፍራቻውን ትቼ መንገድ ለመንገድ ካንተጋ በነፃነት ስበር አይቶኝ እስከአሁን የማያናግረኝ ወንድሜ ጋ?......... የት ነው "ሂጂ" ያልከኝ? የት?.......... ካንተጋ አይተውኝ "የትም ስትንዘላዘል" ብለው ያሙኝ ጎረቤቶቼጋ? .......... ወይንስ "ተይ አይሆንሽም" እያሉ ሲመክሩኝ እንደውም "እናንተ አትሆኑኝም" ብዬ የተውኳቸው ጓደኞቼ ጋር?.......... ማንጋ ነው "ሂጂ" ያልከኝ?.......... ጥለሀኝ ሄደህ ድንገት ወደ ህይወቴ መቶ ሁሉንም ነገር አስተካክሎ፡ የራሱ ሊያደርገኝ ሲል እኔም አንተን ለመርሳት፡ የሱ ልሆን ስል ድጋሚ መተህ "ነይ" ስትለኝ የገነባውን ፍቅር አፍርሼ ልምምጡን ረግጬ የመጣሁት ልጅጋ ነው ምሄደው?.......... ንገረኛ "ተይኝ" ያልከኝ አንተን ትቼ ማንን እንድይዝ ነው??

መغፊራ ቢንት ፉላን