Get Mystery Box with random crypto!

እንዲህ እንዳሁኑ...ውስጤን ባዶነት ሲሰማው..ተስፋ ሲርቅብኝ..ሆዴን ሆድ ሲብሰው..በዙርያዬ ያሉት | ኹሉድ ✍️

እንዲህ እንዳሁኑ...ውስጤን ባዶነት ሲሰማው..ተስፋ ሲርቅብኝ..ሆዴን ሆድ ሲብሰው..በዙርያዬ ያሉት ነገሮች ውስጥ ውስጤን ሲያቆስሉት..የብቸኝነት ስሜት ወርሶኝ ቁስሌን ሲያመረቅዘው..ካገኘውት ያጣውት በዝቶብኝ እኔነቴን ጨለማ ሲወርሰው.....
    በእነዚህ ሁሉ ስሜቶች...አንተን ማስታወሱ..የእኔ እንደሆንክ ማሰቡ..የአንተን ድምፅ መስማቱ..ሕመሞቼን ያሽርልኛል..ቁስሎቼን ያድንልኛል..በባዶ ተስፋ የከሰመው ልቤ ያብብልኛል..አንተን ማሰቡ ብቻ የብቸኝነት ስሜቴን አጥፍቶ የጨለመው እኔነቴን ዳግመኛ በብርሃን ይሞላልኛል......
    እንዴት?....እንጃ ብቻ ሰው መሆንክን እስኪያጠራጥረኝ የመልአክ ስብዕና የተላበስ ይመስል ለኔ ፍፁም ትመስለኛለክ..ከተፍጥሮም ልታጋጨኝ ትዳዳለክ..የማናደድ ወድያው ደግሞ የማስደሰት ስልጣን በእኔ ላይ አለክ..ራሴን መከልከል አልቻልኩም..ድምፅክን አለመስማቴ ያስከፋኛል ደግሞ ሳገኝክ የዱንያን አስቀያሚ ጎኑን ረስቼ ባንተ የተዋበችዋን ደቂቃዋን አጣጥማታለው..ስለይክ..አውርቼክ ስልኩን ስዘጋው ደሞ ይቺህ ገአነብ ምድር ትታወሰኛለች...የእሳቷ ነበልባል ታነደኛለች..ብቻ ብቻ ግን አሁን አሁን የመኖሬ ምክንያት ሆነከኛል..እንዴት?..እንጃ