Get Mystery Box with random crypto!

ሽሽት ወይንስ በቀል በመغፊራ ቢንት ፉላን ክፍል አስራ7 መጨረሻ | ኹሉድ ✍️

ሽሽት ወይንስ በቀል
በመغፊራ ቢንት ፉላን

ክፍል አስራ7
መጨረሻ 3 (ማሜ)

ባደረገው ነገር ቅንጣት ያህል ፀፀት አልተሰማውም። ኩራት ኩራት ብሎታል.... ትልቅ ጀብድ የፈፀመ ነው ሚመስለው.... በቃ ስለ ሀዩ ስለሀኒ በጭራሽ ማሰብ አይፈልግም። ሀዩን እዛ ሁላ ተማሪ ፊት አዋርዷት፣ መራመድ እንኳን አቅቷት፣ በማሜ ስራ የተበሳጩ ሀዩን ሚያውቋት ልጆች ደግፈው እያባበሉ ከመናፈሻው ጊቢ ይዘዋት ከወጡ በውሀላ የት ትሂድ? ምን ትሁን? ምንም አያውቅም። ደሞ ማወቅም አይፈልግም። ስለምን ብሎ ያውቃል....... ደሞ የፈለጋት ለበቀል ነበር፣ ተበቅሎ ጨርሷል.......
ሀኒንም ቢሆን የዛን ቀን አልጋ ላይ ተኝታ፣ አልግጦባት ከወጣ ከትንሽ እርምጃ ቡሀላ ከተከተለው የመኝታ ቤቱን ሆቴል ካናገው ጩሀቷ ቡሀላ አይቷትም፣ ድምጿንም ሰምቶ አያቅም። ሀይሚ የሀኒን ጩሀት ሰምታ ወደሷ ስትሮጥ አይቷል....... በቃ ከዛ ቡሀላ ሁለቱም የሉ። social media ላይም አይታዩም..... ጊቢ ውስጥም.....ክፍልም አይገቡም..... እሱም አልፈለጋቸውም! ግን ብዙ ተማሪዎች እየመጡ ይጠይቁታል! "አላቅም ከኔጋም አይገናኙም"ነው መልሱ........ ሀና ስልካቸው ዝግ እንደሆነ ነግራዋለች። ግድ ያልሰጠው ቢመስልም ሀኒን ግን አለማሰብ አልቻለም። ሰራው አልፀፀተውም...... ግን እሷ ናፍቃዋለች። አንድ ቀን ወደ ክፍል ሲገባ ሀይሚን አያት። ደነገጠ! ሀኒን በአይኑ ፈለጋት.....እሷ ግን የለችም! ሀይሚን ሊጠይቃት ፈለገ፣ "ግን ምን ብሎ?" እሱ ሲገባ ክፍሉን ለቃ ወጣች። ልታየው እንኳን እንደማትፈልግ ተረድቷል..... ዝም አላት። በዚ ሁኔታ የአራተኛ አመት የመጀመርያ ሴሚስተር ት/ት አለቀ። ሀኒን ሳያያት፣ ስለሷ ሳይሰማ፣ ግን ሁለተኛ ሴሚስተር ላይ እንደምትመጣ እርግጠኛ ነበር።
ወደ አ.አ መሄድ አልፈለገም...... ከሳሚ ጋ ወደ ሀዋሳ ሄደ፤ እዛ ቆይቶ ወደ ጊቢ ተመለሰ። አሁንም ግን ሀኒ የለችም...... ሀይሚ ብቻዋን ናት። ግራ ገባው...... ለመጀመርያ ጊዜ በስራው ተፀፀተ "በቃ ሀገሯ ጋ ሄዳ ነው።" ደመደመ ከእውነታው ላለመጋፈጥ ሸሸ.....ግን አልሆነለትም በየደቂቃው ያስባታል...............
አራተኛ አመት አለቀና ወደአምስተኛ አመት መሸጋገሪያው ክረምት መጣ። አሁንም ወደ ሸገር መሄድ አልፈለገም። ሀዋሳ ተመችታዋለ፤ እዛ ማንም አያቀውማ! ወደዛ እንደሚሄድ ሚያቀው እሱና ሳሚ ናቸው። ወደዛ ሚሄዱበትን ትኬት ለመቁረጥ ወደከተማ በወጡበት፣ ከአ.አ ተደውሎ "አሳዳጊው ወይዘሮ ዝናሽ በጣም እንደደከመች እና በጣም እንደምትፈልገው" ተነገረው። ደንግጧል! እናቱን የሚያጣ መሰለው..... ሳያያት ብትሞት ፀፀቱን አይችለውምና ሳሚን "ልብሴን ሙሉ አንተ ይዘሀው ሂድ! እኔ እዛ ያለውን ነገር ጨራርሼ እመጣለው!" ብሎት ወደጊቢም ሳይመለስ እዛው ባገኘው መኪና ተሳፈረ።

ወደ ማሳደጊያው ጊቢ ሲገባ እንደተባለው ነበር። እንደ እናትም እንደ አባትም ሆና ያሳደገችው ወይዘሮ ዝናሽ ደክማለች። ሀኪሞቹ ለማዳን ስላልቻሉ "ወደቤት ውሰዷትና ተንከባከቧት" ስላሉ ነው ወደዚ ተመልሳ የመጣችው። ተንደርድሮ ሄዶ አቀፋት። ስታየው ፈገግ አለች.... ሊጠይቋት ተሰብስበው የነበሩ ሰዎች ሁሉ ክፍሉን ለቀው ወጡ።
በእጇ ይዛው የነበረውን የማሜን የአንገት እያሳየችውና በእጁ እያስጨበጠችው ንግግራን ጀመረች "ይሀውልህ የኔ ልጅ ይህ የአንገት ያንተ ነው። ገና ወደዚ ማሳደጊያ ሰትመጣ አንገትህ ላይ ተንጠልጥሎ ነበር፣" ከዚ በፊት ስለነገረችው ደግማ ለምን እንደምትነግረው ግራ ገብቶታል! "ይሀውልህ እኔ የነገርኩህ ታሪክ እውነቱ ትንሽ ነው። በጊዜው ልጅ ስለነበረክ እና አብዝተህ ትጠይቀኝ ስለነበረ አብረውኝ እናንተን ከሚንከባከቡ ሞግዚቶች ጋር ተመካክሬ እንጂ ስለአንተ ምንም የማውቀው እውነት የለም፤ ይህንን ያደረኩት ለክፋት አደለም ያኔ ልጅ ነበርክ አላቅም ብልህም የባሰ ትጨነቃለህ ብዬ አስቤ ነው። አሁን ግን ትልቅ ሰው ስለሆንክ ቤተሰቦችህን ማግኘት አለብህ። እስክትመረቅ እየጠበኩ ነው ያልነገሩክህ፣ ግን ይሀው ካንተ ምርቃት የኔ ሞት ቀደመ.... እባክህ ይቅርታ አድርግልኝ...... ልጄ እያለች እያለቀሰች ለመነችው።
የሰማውን ማመን አልቻለም ከልጅነቱ ጀምሮ የተጫወተባቸውን ሴቶች አሰበ፣ ሀዩን አስታወሰ.... ከሁሉም ግን ሀኒን አሰባት..... ያፈቀራትን ሴት ምን እንዳረጋት አስታወሰ..... ዘገነነው፣ በውሸት ታሪክ ህይወቱን ሙሉ ያበላሸችው ሴት እያለቀሰች ይቅርታ እያለችው ነው። ሁሉም በሷ ምክንያት ነው፣ ከሁሉም ሴቶች በላይ የሀኒ ነገር አንገበገበው። ከተቀመጠበት ወንበር አጠገብ ያለው አልጋ ላይ የተኛችውን ሴት አብዝቶ ጠላት....... ስሜቱን መቆጣጠር አልቻለም። የተኛችበትን ትራስ ጎትቶ ሲጣጣር የነበረውን ትንፋሿን ቆረጠው። ፀጥ አለች፣ ትራሱን ወደዛ ወርውሮ እዛው ጥሏት ወጣ....................
ኡኡኡኡኡ ዝናሽ ሞተች የለቅሶ ድምፅ አስተጋባ እሱም ጊቢውን ለቆ ወጣ ሸሸ...............


ክፍል አስራ8 ይቀጥላል

በTelegram Channel ማግኘት ለምትፈልጉ
https://t.me/bintfulen
ለአስተያየት
https://t.me/AmMegfi

Graphics designed by
@amiGFX