Get Mystery Box with random crypto!

ሽሽት ወይንስ በቀል በመغፊራ ቢንት ፉላን ክፍል አስራ8 መጨረሻ | ኹሉድ ✍️

ሽሽት ወይንስ በቀል
በመغፊራ ቢንት ፉላን

ክፍል አስራ8
መጨረሻ 4 (ሀይሚ)

በቤተሰቧቿ ለውጥ በጣም ተደንቃለች። በቤታቸው የነበረው ቁጥጥር ሁሉ ቀንሷል...... ከቤት አልወጣም ብሎ በሱሱ የጀዘበው ወንድሟ አባቷ በሼር በሚሰራው መስሪያቤት ውስጥ ዝቅ ብሎ በተላላኪነት ተቀጥሮ እየሰራ ነው። የማታ ትምህርት እየተማረ ቤተሰቡን የሚንከባከብ ጠንካራ ወጣት ሆኗል..... ታናናሾቿም እንደሷ ነፃነታቸውን ተነፍገው ሳይሆን እሷ ከአመታት በፊት ትኖረው የነበረውን ኑሮ እየኖሩ ነው። በዚ በጣም ደስተኛ ናት፤ በሀኒ ግን በጣም አዝናለች..... ምን ማድረግ እንዳለባት እንኳን አታውቅም....... ለማንም እንዳትናገሪ ስላለቻት እንጂ ሁሉንም ነገር ለአህመድ ልትነግረው ፈልጋለች። ሀሰተኛ የውጭ ት/ት እድል ሰርተክፌት አሰርታ፣ ቤተቦቿን ዋሽታ፣ የአረብሀገር ፕሮሰሷን በአጭር ጊዜ ውስጥ ጨርሳ ወደአረብ ሀገር ስለሄደችው ሀኒ ምንም ማድረግ አለመቻሏ ቀንበቀን ውስጧን በፀፀት እየቀጣት ነው። ማሜን ጠልታዋለች፣ "ግን ስላፈቀራት ነው" ብላ ስላሰበች ያንን ያህልል አልፈረደችበትም...... እሷም አፍቃሪ ናትና...... እሷም በሱ ቦታ ብትሆን እንደምታደርገው እርግጠኛ ነበረች። ማንም ዳጊን ሊቀማት አይችልም..... ለዚያውም በዚ ጊዜ...... ለወንድሟ ነግራው፣ ፎቶ አሳይታው፣ ለምርቃቷ እንደሚመጣ እና ከቤተሰቦቿ ጋ ልታስተዋውቀው በጓጓችበት በዚ ጊዜ......... "በቃ ማሜ ጥፋተኛ አደለም! ግን ሀኒ ታሳዝናለች።" ስትል ደምድማለች........
የአራተኛ አመት እረፍት አልቆ በደቤቷ ሰትትመጣ እረፍት ተሰምቷታል። ጊቢውን ጠልታዋለ፣ ሀኒን የሌለችበት ጊቢ ያስጠላል....... ለዳጊ ልትነግረው ብትፈልግም ግን ሀኒ ቃል ስላስገባቻት ለማንም ትንፍሽ አላለችም። "ሁሉንም ጊዜ ይፈታዋል።" ብላ ሁሉንም በውስጧ ይዛ ተቀምጣለች። ዛሬ ዳጊ አልደወለላትም...... "ምን ሆኖ ይሆን?" ብላ ተጨንቃለች። ስትደውል ስልኩ ዝግ ነው። ስራ በዝቶበት ይሆናል ብላ ማታን እየተጠባበቀች ነው.......:መሸ ግን አልደወለም እየጠበቀችው ነው። social media ላይም ብዙ አደለችም እስከዚም ናት፤ በቃ ሁሉም ነገር ያለሀኒ አስጠልቷታል። "ምን አልባት ይደውል ይሆናል" ብላ ስልኳን ትራሷ ውስጥ ከታ እንቅልፏን ተኛች።........ ከለሊቱ 8 ሰዐት የስልኳ ቫይብሬት ቀሰቀሳት፤ "ዳጊ ይሆናል" ብላ ከትራሷ ውስጥ ስታወጣው እሱ አደለም። "ማሜ" ነው ደነገጠች! "ምን ሆኖ ነው በዚሰዐት? ላንሳው? አላንሳው?" እያለች ስልኩ ተዘጋ........ ወዲያው ወዲያው ግን ዳጊ ደወለ። የማሜን ሰልክ ባለማንሳቷ ደስ አላት። አንስታው ቢሆን ኖሮ ዳጊ ሲደውል "ተይዟል" ይለዋል። "በዚ ለሊት ከማንጋ እያወራው ነው" ልለው ነበር? የእፎይታ ስሜት ተሰማት........ ስልኩን አነሳችው፤ ቀኑን ሙሉ ስላልደወለ እንደማኩረፍ ነገር ብላ ነው።
"ሄለው" ያለችው ረጅም ሳቅ ተሰማት።
"ሀኒን ተበቀልኳት አ? ሀዩንስ ብትይ? አረ ምን እነሱን ብቻ አንቺንስ?" ረጅም ሳቅ.......... ግራ ገባት ስልኳን ደግማ አይችው። የደወለው ዳጊ ድምፁ ግን የማሜ ነው....... አልገባትም! "የት ተገናኙ ቆይ?" ግራ ገባት......... ሜማ ጥንብዝ ብሎ መስከሩ ከድምፁ ያስታውቃል። "ሰክረሀል? የት ነው ያለሀው?" አለችው
"አልሰከርኩም! እኔ አልሰከርኩም!" ይስቃል..... "ባይሆን ስሚ፣ምስኪኗ ልጅ! አፍቃሪዋ ልጅ!" ረጅም ሳቅ..... "ማን እነደሚያናግርሽ ታቂያለሽ? የሀኒ ማሜ፣ ያንቺ ዳጊ፣ ዋዋዋዋው..... ዳጊ! ተሳክቶልኛል ባክሽ! ሰው እንዴት አራት አመት ሙሉ ይሸወዳል? ሀሀሀሀሀ....... ሀይሚ ለማንኛውም ተስፋሽን ቁረጪ! እኔ አልመጣም! ግን ግን የላኩልሽ ፎቶ ልጁ አያምርም በናትሽ? ምን አለ እሱን ብመስል? ግን ማን ያምራል?" ደንግጣለች........ "አሁን እኔ እስር ቤት ሄጄ እጄን ልሰጥ ነው። ገደልኳት ኮ! እማማ ዝናሽን ገደልኳት።" ረጅም ሳቅ......... "ስለዚ ያው እንዳልጠፋብሽ ልንገርሽ ብዬ ነው። ሀሀሀሀ.......
ስልኳን ለቀቀችው........ የሰማችውን ማመን አልቻለችም። ግራ ገባት! ይህንን ሁላ አመት ማሜ ነበር ሲያታልላት የነበረው። አጠገቧ ሆኖ፣ አብራው እየበላች፣ አብራው እየዋለች፣ አላመነችም........... እንባዋ ከአይኗ ኩልል እያለ ወረደ...........


ክፍል አስራ9 ይቀጥላል

በTelegram Channel ማግኘት ለምትፈልጉ
https://t.me/bintfulen
ለአስተያየት
https://t.me/AmMegfi

Graphics designed by
https://t.me/joinchat/PpyhlRRD7XZkYTg8