Get Mystery Box with random crypto!

እናቴ'ተበዳይ ዝም ሲል ተከሳሽ ይሆናል'ትለኝ ነበር..እህምምም ሁሉም አባባሎች በቦታቸው ልክ ይሆና | ኹሉድ ✍️

እናቴ"ተበዳይ ዝም ሲል ተከሳሽ ይሆናል"ትለኝ ነበር..እህምምም ሁሉም አባባሎች በቦታቸው ልክ ይሆናሉ..እና እንዳልኩህ ውዴ የበደልክ ዱላ የክህደትክ ውርጅብኝ መላ እኔነቴን ካሳመመኝ በላይ ያንተ መልስ እጅጉኑ ያቆስላል..ረጅም መንገደኛ ስንቁን ሳይቋጥር መንገድ አይጀምርም እኮ...ሊያውም መድረሻውን አውቆ..እንደኔ ተገፊ መነሻ ዬን እንጂ መድረሻዬን የማላውቅ..ያንተዋ ከርታታ ታዲያ በምን አፏ ምክንያትክን ትጠይቅ..ለኔ የመኖሬ..ካንተ ውጭ ያሉትን ሰዎች አይን ላፈር ብዬ ሙሉ እኔነቴን የሰጠውበት ምክንያቴ እኮ አንተው ነክ ታዲያ አንተ እኔን ለመተው አጥጋቢ ምክንያት እንዴት አለክ ብዬ እንዴት ለምን ልበልክ..ደግሞስ አንተ የልቤ ንጉስ እኔ ያንተ ታዛዥ ሂጂ ስትለኝ ወዴት ከማለት ውጪ ለምን ብል ነውርም አይደል...ይልቁኑም"ካንጀት ካለቀሱ እንባ አይገድብም"አይደል የሚለው የአበው ተረቱ ይሁንን ግድ የለም..መግፋትን እንጂ መገፋትን አልጠላውም...ፍቅሬ አንሶብክ ውበቴ ቀንሶ አንተን አንተን ስል ሌላው ሁሉን ነገር መዘንጋቴም አደል የሰለቸክ እኔን ለማስቀመጥ ምክንያት የጠፋክ ከራስክ አልፈክ የኔን ፍላጎትና ስሜት ባንተው እይታ ወስነክልኝ እንዲው እንደዘበት እንዲው እንደ ቀላል " ሂጂ በመኖሬ ከምትጠቀሚው የምትጎጅው ስለሚበልጥ ሂጂ ጠልቼሽ አይደለም ሂጂ ምልሽ ራስወዳድ ስላልሆንኩ እንጂ አዎ ለእኔ ብለሽ ከተጋጨሽው አለም ጋር ዳግም ታረቂ ሂጂ ማለቴን የምታመሠግኝበት ቀን ቅርብ ነው ሂጂ"ያልከኝም..መሄዱን ልሄድ ነው ንጉስ ሆይ ካዘዙ ምን አደርጋለሁ.. ስንቄም ክህደትክ ነው ብርታቴም መገፋቴ ነው..ግን ውዴ ስሞትልክ ሁለት ነገሮችን ልጠይቅክ...አንደኛው ጥያቄ ያው እንደምታውቀው የኔ ዓለም ያንተ ግዛት ነበር ይህች አንተ የሌለክባትን ዓለም እኔ አላውቃትምና  ወስደክ ከሷ አገናኝተክ አስማማኝ..ሁለተኛው ጥያቄ መድረሻዬን ንገረኝ ማረፍያዬን ጠቁመኝ..
ኹሉድ...
ለ Nedir ፅሁፍ የተሰጠ መልስ