Get Mystery Box with random crypto!

ሽሽት ወይንስ በቀል በመغፊራ ቢንት ፉላን ክፍል አስራ5 መጨረሻ 1 | ኹሉድ ✍️

ሽሽት ወይንስ በቀል
በመغፊራ ቢንት ፉላን

ክፍል አስራ5
መጨረሻ 1 (ሀዩ)
ከአክስቷ ልጅ አሊ ጋር ለማሜ ክረምት ላይ ለእረፍት ሲመጣ እውነቱን ማወቅ እንዳለበት ወስነዋል። በዚህም ሀዩ ለመናገር ስለፈራች ለማሜ እውነቱን አሊ እራሱ ደውሎ እንዲነግረው ተስማምተዋልና የማሜን መምጣት በጉጉት ነበር ሲጠብቁ የነበረው............ እንዳፈቀረችው እርግጠኛ የሆነው ማሜ የበቀሉን 90% ስራ አጠናቆ በድል በመወጣቱ ውስጡን ኩራት እየተሰማው ነው። አሁን የቀረው አንድ ነገር ብቻ ነው....... ከሶስት አመት በፊት የ12ኛ ክፍል ተማሪ እያለ ከጓደኞቹ በሰማው የሷ ዝና መሰረት "ማን ስለሆነች ነው?" በሚል ንቀት "እኔ አስቁሜ አናግራታለው!" ብሎ በጉራ ከት/ት ቤቱን ከግማሽ የሚበልጡ ተማሪዎች ሰብስቦ ተወጣጥሮ ሄዶ ሲያናግራት አዋርዳው እንደሄደች እሷንም ህዝብ ሰብስቦ ማዋረድ!.......... የሀዩ ነገር አብቅቶ ውስጡን ላነደደችውና ላስለቀሰችው እንስት ብዙ ስራ እንደሚጠብቀው ስላወቀ የሀያትን ነገር ከዚ ክረምት ሌላ ጊዜ ሊሰጠው አልፈለገም። ከሀዩ "አፈቅርሀለው" ሚለውን ቃል ብቻ ስለሆነ ሚፈልገው ለሱም ትንሽ መስዋዕትነት ብቻ እንደሚያስከፍለው ስለሚያውቅ በድል እንደሚወጣው በራሱ ተማምኖ ወደ ሸገር አቅንቷል። ሸገር ላይ የጠበቀውም ስራውን በእጥፍድርብ የሚያቀል ስራ ነበር............
ወደ ሸገር በገባ በሶስተኛው ቀን ስራውን በእጥፍ ያቀለለት ነገር ተከሰተ። አሊ ደውሎ ከሀዩ ጋ ስላወሩት ነገር፤ ሀዩ ምን ያህል እንዳፈቀረችውም፤ ቤተሰቡ ምን ያህል እንደወደደው እና አሊ ስለወደፊት ህይወታቸው ስላሰበው ነገር ሁሉ ነገረው። ማሜ ደስ አለው! የፈለገው ነገር ተሳካለት! አሊ ጋ ባለማመን አይነት አስመሰለ። ይሄ እንደማይገባው ምናምን ቀባጠረ፤ ተሳካለት! አሊን "አንድ ነገር ላላስቸግረህ ይህን ነገር መስማት ምፈልገው ከሀዩ ራሷ ነው። ካለበለዛ አላምንም።" ብሎ ለመነው አሊ በዚ ምንም ስጋት እንዳይገባው ሁሉንም እሱ እንደሚጨርስለት ቃል ገባለት።
ማሜ የዛን ቀን በደስታ ሲጠጣና ሲጨፍር አደረ ነገ ከነገ ወድያ ብዙ ስራ ይጠብቀዋል...........
ሀዩም በበኩሏ አሊ ከማሜ ጋር ያወሩትን ሙሉ ቀድቶ ልኳላት ስለነበረ በደስታ ስትፈነጥዝ አድራለች። ማሜን ግን ማግኘት ፈርታለች...... አሊ እያደፋፈራት ነው።
ማሜ በጠዋት ነበር ስራውን የጀመረው፤ ከተኛበት አልጋ ተስፈንጥሮ ተነስቶ እስኪሪቢቶ እና ወረቀት ፈልጎ አመጣ። በፊት አብረውት ሲማሩ የነበሩ፡ በተለይ ደሞ በሱ ስር ሲያንዣብቡ የነበሩትን ሁሉ እያስታወሰ ፃፈ። በተለይም ደሞ ያኔ ሀዩ ሰድባው ስትሄድ በዙርያው ቆመው ሲያሽካኩበት የነበሩትን ተማሪዎች አሰበ... ፃፈ። ከነዛ ከተሰበሰቡ ሰዎች ውስጥ ደሞ ስድስት ተማሪዎችን ለይቶ አወጣ። ማህሌት፣ ኢክራም፣ እዩኤል፣ አሚር፣ ቃል እና ጌች። እዚ እልህ ውስጥ እንዲገባ ያደረጉት እነሱ ናቸው። እሱም ቃል ገብቶላቸዋል። የፈለገ ጊዜው ይረዝማል እንጂ በነሱ ፊት እንደሚያዋርዳት ምሎ ነግሯቸዋል። መገኘት አለባቸው!። ብዙዎቹን social media ላይ ያገኛቸዋልና ከአስር ቀን ቡሀላ አብረው የተማሩ ተማሪዎች ፕሮግራም እንዳለ እና ከድሮ ት/ት ቤታቸው ጀርባ 7 ሰዐት ለይ እንዲገናኙ እና የተለየ ሰርፕራይዝ እንዳለ ነገራቸው። ብዙዎቹ በደስታ ፍቃደኛ እንደሆኑ እና እንደሚያግዙት ቃል ገብተው ስራቸውን ጀምረዋል። ወደ ጊቢ የሄዱት ለእረፍት ስለመጡ፤ አ.አ ያሉትም ብዙም ስላራቁ ለመገናኘት አልተቸገሩም። ሁሉም በየፊናው "ማን ምን ሆኖ ይሆን? ማን አምሮበት? ማን አስጠልቶ? ማን ተመችቶት ይሆን?" እያለ ያሰላስላል። ከሁሉም በላይ ያጓጓቸው ግን ለማንም ያልተነገረው ሰርፕራይዝ ነበር...........
ማሜ ሀዩን ሰበብ እየፈለገ እየቀጣት ነው። አሊ ስለነገረው ቅር እንዳለው አስባለች። ልታገኘው ብትሞክርም ከ10 ቀን ቡሀላ ፕሮግራም እንዳለበት እና ለሱ ብዙ ስራ እንዳለበት እየነገረ ይቀጣታል። ይህንን ያስተዋለው አሊ ማሜን ደውሎ ሲያናግረው "እሷን ሰርፕራይዝ ለማድረግ ፕሮግራም እያዘጋጀ" እንደሆነ እና "የዛን ቀን እንደምታፈቅረው መስማት እንደሚፈልግ አጥብቆ ነግሮታል!" ነገሩ ንገራት አትንገራት የሆነበት አሊ እህቱ መጨነቋን አይቶ እና የዛን ቀን እንደምታፈቅረው ካልነገረችው ነገሩ ይላሻል ብሎ ስላሰበ ለሀዩ ነግሯታል።

በጠዋቱ እንደጨረቃ አብርታለች፤ ማሜ ጋር ቀጠሮ አላት..... ቀጠሮውን እሱ አስቀድሞ ባይነግራትም አሊ ስለነገራት ለፕሮግራሙ ይመጥናል ያለችውን ልብስ ለብሳ ያለ ወትሮዋ ተቀባብታ ዘንጣ 9ሰዐትን እየጠበቀች ነው። አስርጊዜ ሰዐቱን ታየዋለች፤ እቤታቸው ላለችው ኢልሀም አስር ጊዜ "አምሮብኛል ግን?" እያለች ትጠይቃታለች.... የመሄጃ ሰዐቷ 15 ደቂቃ ሲቀረው ልቧ በፍርሀት ሲደለቅ ይታወቃታል። ውስጧን ማታቀው ፍርሀት እየወረራት መንገዷን ጀምራለች..............
የሷን መምጣት በጉጉት ሚጠብቀው ማሜ የመናፈሻውን መድረክ በቀይ አፉፋ አድምቆታል። ከሰባት ሰዐት ጀምሮ የተሰበሰቡት ጓደኞቹ የሰርፕራይዙ ሰዐት ስለደረሰ ሰብሰብ አድርጓ እንዲደበቁ ነግሯቸው። ችምችም ካለው ዛፍ ጀርባ ተሰግስገዋል........ ማሜ ለተወሰኑ ጓደኞቹ ነገሩን ስለነገራቸው ባለማመን አይነት ነበር ሲጠብቁት የነበረው።
የተሳፈረችበት ራይድ መኪና በሩ ላይ ስለጣላት አመስግና ሂሳቧን ከፍላ ወደመናፈሻው ገባች። በቀይ አፉፋ ካሸበረቀው ዛፍ ፊት ለፊት ፈገግ ብሎ ቆሟል፤ ያየችው ከጠበቀችው በላይ ነው። ተንደርድራ ሄዳ አቀፈችው። ለረጅም ደቂቃ ካቀፈችው ቡሀላ ከተደደገፈችው ደረቱ ቀና ብላ በስስት እያየችው "አፈቅርሀለው" አለችው ድምጿን ደግማ ስትሰማው ደነገጠች። የለበሰችው ልብስ ላይ ማይክራፎን ነበር። አላስተዋለችውም............ በዛው ቅፅበት የማሜ የፌዝ ሳቅ ተሰማት፤ እሱንም ብዙ ድምፃች ተከተሉት...... ያየችውን ማመን አልቻለችም! "ሰርፕራይዝ" የሚለው ቃል ከገባችበት አባነናት። ሁሉንም ታውቃቸዋለች አብረዋት ተምረዋል፤ ከሁሉ በላይ ያስደነገጣት ማሜ በእጁ የያዘው ሻምፓይን ነበር። በደስታ ከፍቶ ወደ ጉሮሮው ሲያንደቀድቀው አላመነችም....... ሁሉም ነገር ጨለመባት ደንዝዛ ቆመች እየሆነ ያለው ግራ አጋባት........ የማሜ ሳቅ፣ መጠጥ፣ አብረዋት የተማሩ ጓደኞቿ፣ ...........ምንም አልገባትም ...........
"ጀግና ነህ! ተበቀልካት" የሚለው ድምፅ ሁሉንም ነገር በቅፅበት ገለፀላት። ውሸት መሆኑን አመነች። ሳታስበው እንደተሸነፈች ገባት። እግሯ ተንቀጠቀጠ መሄድ አቃታት.......
"በቀል ደስ ይላል ሀሀሀሀሀሀሀሀሀ" የማሜ ድምፅ ነው።


ክፍል አስራ6 ይቀጥላል

በTelegram Channel ማግኘት ለምትፈልጉ
https://t.me/bintfulen
ለአስተያየት
https://t.me/AmMegfi

Graphics designed by
https://t.me/joinchat/PpyhlRRD7XZkYTg8