Get Mystery Box with random crypto!

ሽሽት ወይንስ በቀል በመغፊራ ቢንት ፉላን ክፍል አስራ4 ከእውነታው እየሸሸ ነው። በፍ | ኹሉድ ✍️

ሽሽት ወይንስ በቀል
በመغፊራ ቢንት ፉላን
ክፍል አስራ4
ከእውነታው እየሸሸ ነው። በፍፁም እውነታውን መቀበል አልፈለገም። ሀኒ ለሱ ውሸታም ናት! ከሌሎች ሴቶች ምትለይበት ምንም ነገር የለም። በቃ ባያት ቁጥር ውስጡ ሲነድ ይታወቀዋል። ብዙ ሴቶች ላይ ተጫውቶ በሷ መሸነፉ ያበግነዋል። መሸነፍ አይፈልግም ለዚያውም በሴት!
አንድቀን በጓደኞቹ ፊት አዋርዳ፣ አርክሳና ሰድባ ጥላው የሄደችውን ሀዩን እንኳን ከአመታት ቡሀላ እልሁ አልወጣ ብሎት ለበቀል እንዴት እያዘጋጃት እንደሆነ አሰበ። በፍፁም በፍፁም መሸነፍ የለበትም። ያሸነፈውን ባሸነፈው ልክ መቀጣት አለበት። እሱን ማሸነፍ እራስን ወጥመድ ውስጥ መክተት ነው።
ትንሽ ረገብ ብሎለት የነበረው ሱሱ ሁሉ ተነስቶበታል፤ የሴት ስቃይ ሱስ....... ሀኒ አህመድን ካስታዋወቀችበት እለት ጀምሮ ብዙ ሴቶችን ይዞ ተኝቷል። ብዙ ሴቶችን አበላሽቷል። ሴቶች ሁሉ እሷን ነው ሚመስሉት። "ሀናን እና እናቴ አንድ ናቸው! እናቴን ባላገኛት በሷ ምትክ ብዙዎችን ቀጥቻለው! ቀጥላለው! ሀኒን ግን እራሷን ካልቀጣኋት አላርፍም።" ብሎ ቆርጦ ተነስቶላታል። ይህንን የበቀል ሴራውን ማንም እንዲያውቅበት አልፈለገም። ሀኒም ብትሆን እንደጠላት ማወቅ የለባትም። ከበፊቱ የበለጠ እየቀረባትና እያጠመዳት ነው። በምን እንደሚበቀላት ግን እስከአሁን አላወቀም..............
በበቀል ወጥመዱ ሰተት ብላ የገባችለት ሀዩ ቤተሰቦቿ በሙሉ ወደ መጡበት ተበታትነዋል። የአክስቷ ልጆች አብራቸው እንድትሄድ ቢለምኗትም "የጀመርኩትን ት/ት ሳልጨርስ አልሄድም" በሚል ሰበብ ቀርታለች። አሊ የቀረችበትን ምክንያት ስለሚያውቅ አላስጨነቃትም። ማሜን ወዶታል! እህቱ ጥሩ ሰው ላይ እንደወደቀች ነው ያሰበው። ስለዚ አንድ ነገር ለራሱ ቃል ገብቷል። ማሜ ት/ት ሲጨርስ ቤቱን በስሙ ሊያዞርለትና እህቱን ሊድርለት.......
ቀን ማታ ድምፁን ሳትሰማ አትውልም፣ አታድርም። አስርጊዜ ትደውልልለታለች። ያወራታል! እንዳፈቀረችው 100% እርግጠኛ ናት። ልትነግረው ፈልጋለች ግን ፈርታለች። ያፈቅረኛል ብላ እራሷን አሳምናለችና ከሱ እስኪመጣ እየጠበቀች ነው። ደስተኛ ናት! እናትና አባቷን ወስዶ አክስቷን እና የአክስቷን ልጆች ሰጣት። አክስቷን ሲወስድ ደሞ ማሜን...............

የመመረቂያ ጊዜዋ ርቋባታል በዳጊ ተስፋ መቁረጥ አልፈለገችም። መጠበቁን መርጣለች...... እስከምርቃቷ ቀን ብቻ! ከዛ ግን ካልመጣ ልትተወዉ ምላለች። ስታፈቅርም ስትፈቀርም የመጀመርያዋ ነው። ማጣቱ ምን ያህል ሊጓዳት እንደሚችል አስባለች። ለአንድ ቀን እንኳን ካኮረፋት እንዴት እንደምትሆን ታቀዋለች፤ ከተዋት ወይ ከተወችው ት/ት ማቆሟ እንደማይቀር ታውቃለች። ይህ ደሞ መሆን የለበትም! "በማዕረግ ትመረቃለች" ብለው ሚጠብቋትን ቤተሰቦቿ "በማዕረግ መመረቅ ባልችል እንኳን ጋውን ለብሼ ማየት አለባቸው" ብላ ስላሰበች ለሷም ለቤተሰቦቿም ስትል ታምነዋለች፣ ትጠብቀዋለች።......

የሶስተኛ አመት ትምህርታቸውን ጨርሰው ሁሉም ወደቤታቸው ሊሄዱ ዝግጅት ላይ ናቸው። ሀኒ አህመድን ለማግባት ሁለት አመት ብቻ እንደቀራት ስታስብ በደስታ ጮቤ ትረግጣለች። እሱም እንደዛው.........
ከቤታቸው ሲመለሱ ሁሉም ጓደኛሞች ስጦታ ሊሰጣጡ እጣ ጥለዋል። አምስት ስለሆኑ እጣው እኩል እንዲደርስ አንድ ሰው እንደሚያስፈግ ስላሰቡ ሀዩ መጀመርያ ወደ ጊቢ ስትመጣ fb ላይ የተዋወቀሻትን የሀዋሳዋን ሀና ሊያስገቡ ወስነዋል። በዚህም መሰረት እጣው የደረሰው ማሜ ለሀ፤ ሀኒ ለአቤል፤ አቤል ለሀይሚ፤ ሀይሚ ለሳሚ፤ ለሳሚ ማሜ፤ ለማሜ ሀና..............
ማሜ ለሀኒ እሱ እንዲሰጥ ያደረገው እራሱ በሰራው ተንኮል ነው እንጂ ለሀኒ ስጦታ እንዲሰጣት የደረሰው አቤል ነበር።
የማሜ ስጦታግን ምን ይሆን?......


ክፍል አስራ5 ይቀጥላል

በTelegram Channel ማግኘት ለምትፈልጉ
https://t.me/bintfulen
ለአስተያየት
https://t.me/AmMegfi

Graphics designed by
https://t.me/joinchat/PpyhlRRD7XZkYTg8