Get Mystery Box with random crypto!

ሁሌ አዲስ ሚዲያ (Hule Addis Media)

የቴሌግራም ቻናል አርማ hulaadiss — ሁሌ አዲስ ሚዲያ (Hule Addis Media)
የቴሌግራም ቻናል አርማ hulaadiss — ሁሌ አዲስ ሚዲያ (Hule Addis Media)
የሰርጥ አድራሻ: @hulaadiss
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.80K
የሰርጥ መግለጫ

ትክክለኛዉ የሁሌ አዲስ ሚዲያ ገፆች
Facebook : bit.ly/42rUuKj
Telegram: bit.ly/3NBQbro
YouTube : bit.ly/3p7kj3N
Twitter : bit.ly/3NVMRrB
Website : bit.ly/3ntuxuZ
ለጥቆማ ና አስተያየት እንዲሁም ለማስታወቂያ ስራ ተከታዮን አድራሻ ይጠቀሙ
bit.ly/3VMy7x7 ወይም 251939758767

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1

የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-31 20:54:55 የኢትዮጵያ መምህራን ማሕበር ጦርነቱ ቆሞ ድርድር እንዲጀመር ጠየቀ

በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም የተቀሰቀሰው ጦርነት በአስቸኳይ ቆሞ የአፍሪካ ሕብረት ለሰላም የጀመረውን የማደራደር ኃላፊነት እንዲቀጥል የኢትዮጵያ መምህራን ማሕበር ጠየቀ።

ማሕበሩ ዛሬ በሰጠው መግለጫ በኢትዮጵያ የሚከሰቱና የተከሰቱ ግጭቶች ሁሉ በውይይት መፈታት ያለባቸውና የሚችሉ ናቸው ብሏል።

ጦርነቱ ለመምህራን ጥያቄዎች ወቅታዊ ምላሽ ለማግኘት እንቅፋት ሆኖብኛል ያለው ማሕበሩ በተለይ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን የደሞዝ ማሻሻያ እና ሌሎች ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ ግፊት ማድረጌን እቀጥላለሁ ብሏል።

የዩኒቨርሲቲ መምህራን በተለይ ለደሞዝ ጭማሪ ጥያቄዎቻቸው ምላሽ እንዲሰጣቸው ደጋግመው እየጠየቁ ሲሆን ማሻሻያ ካልተደረገ ሥራ በማቆም ጭምር ለጥያቄያቸው ምላሽ መገኘት ግፊት እንደሚያደርጉ እየገለፁ ይገኛሉ።

ለወቅታዊ እና ለፈጣን መረጃዎች የሁሌ አዲስ ሚዲያ የማህበራዊ ሚዲያዎችን ይቀላቀሉ።

Facebook : https://www.facebook.com/Huleadissmedia/
Telegram : https://t.me/Hulaadiss
YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCk934znIu60LV3czcIVZ9Bg
Twitter: https://twitter.com/Huleaadis_Media
431 viewsEyasu Zekarias1, 17:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 20:51:09 የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት ይቆያል፦ የንግድ እና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ከነሐሴ 26 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ መስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም በነበረበት እንደሚቆይ የንግድ እና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር አስታወቀ።

ለወቅታዊ እና ለፈጣን መረጃዎች የሁሌ አዲስ ሚዲያ የማህበራዊ ሚዲያዎችን ይቀላቀሉ።

Facebook : https://www.facebook.com/Huleadissmedia/
Telegram : https://t.me/Hulaadiss
YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCk934znIu60LV3czcIVZ9Bg
Twitter: https://twitter.com/Huleaadis_Media
454 viewsEyasu Zekarias1, edited  17:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 15:31:15
በመቀሌ ከተማ የአየር ድብደባ መፈፀሙ ተገለፀ

የህወሓት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ በትዊተር ገፃቸው እንዳስታወቁት በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ ትናንት እኩለ ሌሊት በሰው አልቫ አውሮፕላን ድብደባ ተፈፅሟል።ድብደባው ያደረሰዉ ጉዳት ስለመኖር-አለመኖሩ ግን ቃል አቀባዩ አልገለፁም።

በፌደራል መንግሥት እና በሕወሃት መካከል በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ግጭት ካገረሸ ወዲህ፣ በመቀሌ የአየር ድብደባ እንደተፈጸመ ሕወሃት ሲገልጽ የአሁኑ ሁለተኛው ነው።

ለወቅታዊ እና ለፈጣን መረጃዎች የሁሌ አዲስ ሚዲያ የማህበራዊ ሚዲያዎችን ይቀላቀሉ።

Facebook : https://www.facebook.com/Huleadissmedia/
Telegram : https://t.me/Hulaadiss
YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCk934znIu60LV3czcIVZ9Bg
Twitter: https://twitter.com/Huleaadis_Media
525 viewsEyasu Zekarias1, edited  12:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 13:38:36 በሰሜን ኢትዮጵያው ውጊያ ሳቢያ በሰሜን ወሎ ዞን 30 ሺህ ሰዎች መፈናቀላቸውን ተመድ አስታወቀ

በኢትዮጵያ ዳግም በተቀሰቀሰው ውጊያ ሳቢያ በአማራ ክልል በሰሜን ወሎ ዞን ተጠልለው የነበሩ 30 ሺህ ሰዎች ለሁለተኛ ጊዜ ለመፈናቀል መዳረጋቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) አስታወቀ። በተመሳሳይ ሁኔታ በአፋር ክልል ካሉ ሶስት ወረዳዎች በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንደተፈናቀሉ ሪፖርት እንደደረሰው የመንግስታቱ ድርጅት ገልጿል።

የተመድ ቃል አቃባይ ስቴፈን ዱጃሪች ትላንት ማክሰኞ ነሐሴ 24 ምሽት በሰጡት ዕለታዊ መግለጫቸው፤ በሰሜን ኢትዮጵያ የተቀሰቀሰው ግጭት በመቀጠሉ ሁኔታ በአካባቢው ያለው ሁኔታ ውጥረት የተሞላበት እንደሆነ ተናግረዋል። በተለያዩ አካባቢዎች ሰዎች እየተፈናቀሉ ነው መባሉ፤ የሰብዓዊ መብት ፍላጎትን እንደጨመረውም ጠቁመዋል።

ቃል አቃባዩ በዚሁ መግለጫቸው፤ የአፋር ክልል ከትግራይ ጋር በሚዋሰንባቸው ቦታዎች በሚገኙት በያሎ እና ጉሊና ወረዳዎች እየተካሄደ ባለው ውጊያ ሳቢያ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንደተፈናቀሉ ሪፖርት መደረጉን ጠቅሰዋል። በአፋር እና አማራ አዋሳኝ ቦታ በሚገኘው ጭፈራ ወረዳም፤ ሰዎች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን የሚያመለክት ሪፖርት እንዳለ ዱጃሪች ለጋዜጠኞች አስረድተዋል።

ለወቅታዊ እና ለፈጣን መረጃዎች የሁሌ አዲስ ሚዲያ የማህበራዊ ሚዲያዎችን ይቀላቀሉ።

Facebook : https://www.facebook.com/Huleadissmedia/
Telegram : https://t.me/Hulaadiss
YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCk934znIu60LV3czcIVZ9Bg
Twitter: https://twitter.com/Huleaadis_Media
507 viewsEyasu Zekarias1, 10:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 13:00:07 ሕወሓት በዋግ፣ በወልቃይት አቅጣጫና በሱዳን ድንበር አካባቢ ወረራ መክፈቱ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የሕወሓት ቡድን በዋግ፣ በወልቃይት አቅጣጫና በሱዳን ድንበር አካባቢ ወረራ መክፈቱ አስታውቋል።

አገልግሎቱ ባወጣው መግለጫ “መንግሥት ለሰላም አማራጭ ዕድል ለመስጠት ሲል የሕዝብ ማዕበል አስነሥቶ ሕጻናትን፣ ወጣቶችንና አረጋውያንን ለመማገድ የመጣውን የአሸባሪው ሕወሓት ታጣቂ፣ በምሥራቅ አማራ በኩል በጀግንነት ሲከላከል ቆይቷል።” ሲል ገልጿል።

ቡድኑ በምሥራቅ አማራ በኩል በቆቦና አካባቢው የከፈተው ወረራ በመከላከያ ሠራዊትና በደጀኑ ሕዝብ ጠንካራ የመከላከል ብቃት የተነሣ ባሰበው ልክ እንዳልሄደለትም አገልግሎቱ አስታውቋል።

”በዚህም ምክንያት ለሰላም የተሰጠውን ሁለንተናዊ አማራጭ አሽቀንጥሮ ጥሎ ወረራውን ወደ ሌሎች አካባቢዎች እያስፋፋ ይገኛል።” ያለው የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ቡድኑ በዋግ፣ በወልቃይት አቅጣጫና በሱዳን ድንበር አካባቢ ወረራ መክፈቱን ገልጿል።

ይሄንን የሕወሐት ወረራ የመከላከያ ሠራዊት በተሟላ ዝግጅትና በጽኑ ቁመና እየተከላከለ እንደሚገኝም የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በመግለጫው አስታውቋል።

”ለሰላም የተዘረጋው እጅ በሕወሓት ዕብሪታዊ ወረራ ምክንያት እንዳይታጠፍ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የሚቻለውን ያድርግ“ ሲልም አሳስቧል።

በተጨማሪም ”ወገን የሆነው የትግራይ ሕዝብም ይሄንን የዕብሪት ወረራ በማውገዝ ሕወሓት ከሚያስከትልበት መከራ ራሱን ነጻ ያውጣ” ሲል ጥሪ አቅርቧል።

ለወቅታዊ እና ለፈጣን መረጃዎች የሁሌ አዲስ ሚዲያ የማህበራዊ ሚዲያዎችን ይቀላቀሉ።

Facebook : https://www.facebook.com/Huleadissmedia/
Telegram : https://t.me/Hulaadiss
YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCk934znIu60LV3czcIVZ9Bg
Twitter: https://twitter.com/Huleaadis_Media
515 viewsEyasu Zekarias1, edited  10:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 18:04:48 ወደ ትግራይ የሚደረገው የሰብአዊ እርዳታ ጉዞ መቆሙን የተመድ አስታወቀ

የተባበሩት መንግስት ድርጅት (ተመድ) የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ እንዳስታወቀው በየብስ እና በአየር ወደ ትግራይ ሲደረግ የቀየው የሰብአዊ እርዳታ ጉዞ መቆሙን አስታውቋ።

በየብስ የሰብአዊ እርዳታ ከባለፈው ሀሙስ ጀምሮ የቆመ ሲሆን በአየር የሚደረገው እርዳታ ደግሞ አርብ ጀምሮ መቆሙን ቢሮ ገልጿል።

ቢሮው እንቅስቃሴ በመቆሙ ምክንያት የእርዳታ ሰራተኞችን እንቅስቃሴ አስተጓጊሏል ብሏል።

አስቸኳይ ተኩስ አቁም እንዲደረግ የጠየቀው ቢሮው የጸጥታው ሁኔታ የሚፈቅድ ከሆነ ቢሮው ከአጋሮቹ ጋር በመሆን ለተጎዱ ሰዎች እርዳታ እንደሚያቀርብ መግለፁን ዐልአይን ዘግቧል

ለወቅታዊ እና ለፈጣን መረጃዎች የሁሌ አዲስ ሚዲያ የማህበራዊ ሚዲያዎችን ይቀላቀሉ።

Facebook : https://www.facebook.com/Huleadissmedia/
Telegram : https://t.me/Hulaadiss
YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCk934znIu60LV3czcIVZ9Bg
Twitter: https://twitter.com/Huleaadis_Media
338 viewsEyasu Zekarias1, 15:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 18:02:23 በጎንደር ከተማ ለተነሳው ግጭት ምክንያት በነበረው በእምነት ተቋማት መካከል ባለው ቦታ የወሰን ማካለል ተደረገ

በጎንደር ከተማ ሚያዚያ 18 ቀን 2014 ዓ.ም ለቀብር የሚሆን ድንጋይ "እንወስዳለን፣ አትወስዱም" በሚል ተጀምሮ ግጭት እንዲቀሰቀስ መነሻ ምክንያት በነበረው አበራ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ፀበል ቦታና የሃጅ ኤሊያስ ቀብር ስፍራ መካከል ባለው ቦታ የወሰን ማካለል ተደረገ።

የአራዳና የማራኪ ክፍለ ከተሞች በጋራ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ከሁለቱም እምነት አባቶች ጋር ሰፊ ምክክር በማድረግ የወሰን ማካለሉ ስራ በሁለቱም ወገኖች መግባባትና መተማመን መጠናቀቁ ተገልጿል።

በዚህም መሰረት ዛሬ ነሃሴ 24 ቀን 2014 ዓ.ም ለአበራ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ፀበል ቦታና ለሃጅ ኤሊያስ ቀብር ቦታ የካርታ ርክክብ ጎንደር በሚገኘው ሃይሌ ሪዞርት ተካሄዷል።

ሚያዚያ 18 ቀን 2014 ዓ.ም በተነሳው ግጭት የጎንደር ከተማ ነዋሪና አንጋፋ አባት የነበሩት ሼኽ ከማል ለጋስ ሥርዓተ ቀብር እየተፈጸመ በነበረበት ወቅት ከቀብር ቦታው ጋር ድንበርተኛ ከሆነው ቤተ ክርስቲያን ስፍራ ለቀብር የሚሆን ድንጋይ "እናነሳለን የመስጊዱ ክልል ነው፤ አታነሱም የቤተ ክርስቲያኑ ቅጥር ነው" በሚል በተወሰኑ ግለሰቦች መካከል በተጀመረው ግጭት የሰው ህይወት መጥፋቱ፤ የአካል ጉዳት መድረሱ እንዲሁም የተለያዩ ንብረቶችና ተቋማት ውድመት ማስከተሉ ይታወሳል።

በርክክቡ የተገኙት የሁለቱም ኃይማኖት ተወካዮችና ተከታዮች ችግሩ በዚህ አይነት ሰላማዊ መንገድ በመፈታቱ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል።(አዲስ ዘይቤ)

ለወቅታዊ እና ለፈጣን መረጃዎች የሁሌ አዲስ ሚዲያ የማህበራዊ ሚዲያዎችን ይቀላቀሉ።

Facebook : https://www.facebook.com/Huleadissmedia/
Telegram : https://t.me/Hulaadiss
YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCk934znIu60LV3czcIVZ9Bg
Twitter: https://twitter.com/Huleaadis_Media
321 viewsEyasu Zekarias1, 15:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 17:26:16 ህወሓት ሊተላለፍ የነበረ ከ1 ሚሊየን ብር በላይ ተያዘ

ከስሃላ ወረዳ ወደ በየዳ ወረዳ በቅብብሎሽ ህወሓት ሊደርስ የነበረ 1 ሚሊየን 253 ሺህ ብር መያዙን የተከዜ ክፍለ ጦር 3ኛ ሻለቃ አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ጀጃው ፈረደ ገልጸዋል፡፡

አሸባሪው ቡድን ሰርጎ ገቦችን በማዘጋጀት ገንዘብና ቁሳቁስ እንዲሻገርለት ቢፈልግም በአማራ ክልል ልዩ ኃይልና በህብረተሰቡ ጥብቅ ክትትል ዕቅዱ ከሽፏል ብለዋል፡፡

ቡድኑ ሊጠቀምበት የነበረ 600 ሊትር አረቂ፣ 10 ጣቃ አቡጀዲ፣ 15 ሺህ 9 የሶላር መብራትና ከአምስት ኩንታል በላይ ጨው እና መሰል ቁሳቁስ ከእነተጠርጣሪዎቹ መያዙን የበየዳ ወረዳ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

ለወቅታዊ እና ለፈጣን መረጃዎች የሁሌ አዲስ ሚዲያ የማህበራዊ ሚዲያዎችን ይቀላቀሉ።

Facebook : https://www.facebook.com/Huleadissmedia/
Telegram : https://t.me/Hulaadiss
YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCk934znIu60LV3czcIVZ9Bg
Twitter: https://twitter.com/Huleaadis_Media
338 viewsEyasu Zekarias1, 14:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 13:30:19
በሲዳማ ክልል ከ3 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ለከፍተኛ የረሃብ አደጋ ተጋልጧል መባሉን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስተባበለ

በሲዳማ ክልል ወቅቱን የጠበቀ ዝናብ ባለመዝነቡ ከሶስት ሚሊዮን በላይ ህዝብ ለከፍተኛ የረሃብ አደጋ ተጋልጧል የተባለዉ መረጃ ሀሰት እንደሆነ የክልሉ ግብርና ቢሮ ገልጿል።

የሰብል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አለሙ በጉዳዩ ላይ በሰጡት አስተያየት በ 17 ወረዳዎች በአየር ንብረት ለዉጥ ምክንያት በተከሰተዉ አደጋ ከ 3 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ለረሃብ ተጋልጧል መባሉ “የተሳሳተ እና መሰረተ ቢስ መረጃ ነዉ" ብለዋል።

እንደ ዳይሬክተሩ ገለፃ በወቅቱን ዝናብ ባለመዝነቡ ምክንያት በክልሉ በሚገኙ 15 ወረዳዎች ከ 25 ሺህ ሄክታር በላይ በቆሎ እና የቦለቄ ምርት መውደሙን በማንሳት "በዚህም ምክንያት ከ62 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች እና በቤተሰብ ደረጃ ደግሞ ከ 30 ሺህ በላይ ሰዎች ለአደጋዉ ተጋላጭ" መሆናቸውን ጨምረዉ ገልፀዋል ።

የሲዳማ ክልል የግብርና ቢሮ ከክልሉ መንግስት ጋር በመተባበር ለችግሩ ተጋላጭ ለሆኑ አርሶ አደሮች ማካካሻ የሚሆን 47 ሚሊዮን ብር በመበጀት ዘር እንዲገዛ መደረጉ የተነገረ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ ለሰብአዊ እርዳታ የሚዉል 50 ሚሊዮን ብር በአጠቃላይ 97 ሚሊዮን ብር ተመድቦ ወደ ስራ መገባቱን አዲስ ዘይቤ ዘግቧል ።

ለወቅታዊ እና ለፈጣን መረጃዎች የሁሌ አዲስ ሚዲያ የማህበራዊ ሚዲያዎችን ይቀላቀሉ።

Facebook : https://www.facebook.com/Huleadissmedia/
Telegram : https://t.me/Hulaadiss
YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCk934znIu60LV3czcIVZ9Bg
Twitter: https://twitter.com/Huleaadis_Media
405 viewsEyasu Zekarias1, edited  10:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 11:52:41
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የሰላም ጥረቱ እንዲቀጥል ጥሪ አስተላለፈ

ኮሚሽኑ ባወጣው መግለጫ ተፋላሚ ኃይላቱ «በጦር መሣሪያ ግጭቱ ተጋላጭ የሆኑ ሰላማዊ ዜጎች ሕይወት፣ ደኅንነት፣ አካላዊ እና ሞራላዊ ልዕልና ብሎም ክብራቸውን የመጠበቅ ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል»ም ሲል አሳስቧል።

ኢሰመኮ ስጋቱን ያንጸባረቀበትን መግለጫ ከ3 ወራት በፊትም አውጥቶ ነበር። በወቅቱ በአፋር፤ አማራ እና ትግራይ ክልሎች መጠነ ሰፊ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ስለመፈጸማቸው መረጃዎችን መሰነዱን ዐስታውቆ ነበር።

ለወቅታዊ እና ለፈጣን መረጃዎች የሁሌ አዲስ ሚዲያ የማህበራዊ ሚዲያዎችን ይቀላቀሉ።

Facebook : https://www.facebook.com/Huleadissmedia/
Telegram : https://t.me/Hulaadiss
YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCk934znIu60LV3czcIVZ9Bg
Twitter: https://twitter.com/Huleaadis_Media
392 viewsEyasu Zekarias1, edited  08:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ