Get Mystery Box with random crypto!

በሲዳማ ክልል ከ3 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ለከፍተኛ የረሃብ አደጋ ተጋልጧል መባሉን የክልሉ ግብርና ቢ | ሁሌ አዲስ ሚዲያ (Hule Addis Media)

በሲዳማ ክልል ከ3 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ለከፍተኛ የረሃብ አደጋ ተጋልጧል መባሉን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስተባበለ

በሲዳማ ክልል ወቅቱን የጠበቀ ዝናብ ባለመዝነቡ ከሶስት ሚሊዮን በላይ ህዝብ ለከፍተኛ የረሃብ አደጋ ተጋልጧል የተባለዉ መረጃ ሀሰት እንደሆነ የክልሉ ግብርና ቢሮ ገልጿል።

የሰብል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አለሙ በጉዳዩ ላይ በሰጡት አስተያየት በ 17 ወረዳዎች በአየር ንብረት ለዉጥ ምክንያት በተከሰተዉ አደጋ ከ 3 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ለረሃብ ተጋልጧል መባሉ “የተሳሳተ እና መሰረተ ቢስ መረጃ ነዉ" ብለዋል።

እንደ ዳይሬክተሩ ገለፃ በወቅቱን ዝናብ ባለመዝነቡ ምክንያት በክልሉ በሚገኙ 15 ወረዳዎች ከ 25 ሺህ ሄክታር በላይ በቆሎ እና የቦለቄ ምርት መውደሙን በማንሳት "በዚህም ምክንያት ከ62 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች እና በቤተሰብ ደረጃ ደግሞ ከ 30 ሺህ በላይ ሰዎች ለአደጋዉ ተጋላጭ" መሆናቸውን ጨምረዉ ገልፀዋል ።

የሲዳማ ክልል የግብርና ቢሮ ከክልሉ መንግስት ጋር በመተባበር ለችግሩ ተጋላጭ ለሆኑ አርሶ አደሮች ማካካሻ የሚሆን 47 ሚሊዮን ብር በመበጀት ዘር እንዲገዛ መደረጉ የተነገረ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ ለሰብአዊ እርዳታ የሚዉል 50 ሚሊዮን ብር በአጠቃላይ 97 ሚሊዮን ብር ተመድቦ ወደ ስራ መገባቱን አዲስ ዘይቤ ዘግቧል ።

ለወቅታዊ እና ለፈጣን መረጃዎች የሁሌ አዲስ ሚዲያ የማህበራዊ ሚዲያዎችን ይቀላቀሉ።

Facebook : https://www.facebook.com/Huleadissmedia/
Telegram : https://t.me/Hulaadiss
YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCk934znIu60LV3czcIVZ9Bg
Twitter: https://twitter.com/Huleaadis_Media