Get Mystery Box with random crypto!

ህወሓት ሊተላለፍ የነበረ ከ1 ሚሊየን ብር በላይ ተያዘ ከስሃላ ወረዳ ወደ በየዳ ወረዳ በቅብብሎሽ | ሁሌ አዲስ ሚዲያ (Hule Addis Media)

ህወሓት ሊተላለፍ የነበረ ከ1 ሚሊየን ብር በላይ ተያዘ

ከስሃላ ወረዳ ወደ በየዳ ወረዳ በቅብብሎሽ ህወሓት ሊደርስ የነበረ 1 ሚሊየን 253 ሺህ ብር መያዙን የተከዜ ክፍለ ጦር 3ኛ ሻለቃ አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ጀጃው ፈረደ ገልጸዋል፡፡

አሸባሪው ቡድን ሰርጎ ገቦችን በማዘጋጀት ገንዘብና ቁሳቁስ እንዲሻገርለት ቢፈልግም በአማራ ክልል ልዩ ኃይልና በህብረተሰቡ ጥብቅ ክትትል ዕቅዱ ከሽፏል ብለዋል፡፡

ቡድኑ ሊጠቀምበት የነበረ 600 ሊትር አረቂ፣ 10 ጣቃ አቡጀዲ፣ 15 ሺህ 9 የሶላር መብራትና ከአምስት ኩንታል በላይ ጨው እና መሰል ቁሳቁስ ከእነተጠርጣሪዎቹ መያዙን የበየዳ ወረዳ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

ለወቅታዊ እና ለፈጣን መረጃዎች የሁሌ አዲስ ሚዲያ የማህበራዊ ሚዲያዎችን ይቀላቀሉ።

Facebook : https://www.facebook.com/Huleadissmedia/
Telegram : https://t.me/Hulaadiss
YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCk934znIu60LV3czcIVZ9Bg
Twitter: https://twitter.com/Huleaadis_Media