Get Mystery Box with random crypto!

በጎንደር ከተማ ለተነሳው ግጭት ምክንያት በነበረው በእምነት ተቋማት መካከል ባለው ቦታ የወሰን ማካ | ሁሌ አዲስ ሚዲያ (Hule Addis Media)

በጎንደር ከተማ ለተነሳው ግጭት ምክንያት በነበረው በእምነት ተቋማት መካከል ባለው ቦታ የወሰን ማካለል ተደረገ

በጎንደር ከተማ ሚያዚያ 18 ቀን 2014 ዓ.ም ለቀብር የሚሆን ድንጋይ "እንወስዳለን፣ አትወስዱም" በሚል ተጀምሮ ግጭት እንዲቀሰቀስ መነሻ ምክንያት በነበረው አበራ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ፀበል ቦታና የሃጅ ኤሊያስ ቀብር ስፍራ መካከል ባለው ቦታ የወሰን ማካለል ተደረገ።

የአራዳና የማራኪ ክፍለ ከተሞች በጋራ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ከሁለቱም እምነት አባቶች ጋር ሰፊ ምክክር በማድረግ የወሰን ማካለሉ ስራ በሁለቱም ወገኖች መግባባትና መተማመን መጠናቀቁ ተገልጿል።

በዚህም መሰረት ዛሬ ነሃሴ 24 ቀን 2014 ዓ.ም ለአበራ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ፀበል ቦታና ለሃጅ ኤሊያስ ቀብር ቦታ የካርታ ርክክብ ጎንደር በሚገኘው ሃይሌ ሪዞርት ተካሄዷል።

ሚያዚያ 18 ቀን 2014 ዓ.ም በተነሳው ግጭት የጎንደር ከተማ ነዋሪና አንጋፋ አባት የነበሩት ሼኽ ከማል ለጋስ ሥርዓተ ቀብር እየተፈጸመ በነበረበት ወቅት ከቀብር ቦታው ጋር ድንበርተኛ ከሆነው ቤተ ክርስቲያን ስፍራ ለቀብር የሚሆን ድንጋይ "እናነሳለን የመስጊዱ ክልል ነው፤ አታነሱም የቤተ ክርስቲያኑ ቅጥር ነው" በሚል በተወሰኑ ግለሰቦች መካከል በተጀመረው ግጭት የሰው ህይወት መጥፋቱ፤ የአካል ጉዳት መድረሱ እንዲሁም የተለያዩ ንብረቶችና ተቋማት ውድመት ማስከተሉ ይታወሳል።

በርክክቡ የተገኙት የሁለቱም ኃይማኖት ተወካዮችና ተከታዮች ችግሩ በዚህ አይነት ሰላማዊ መንገድ በመፈታቱ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል።(አዲስ ዘይቤ)

ለወቅታዊ እና ለፈጣን መረጃዎች የሁሌ አዲስ ሚዲያ የማህበራዊ ሚዲያዎችን ይቀላቀሉ።

Facebook : https://www.facebook.com/Huleadissmedia/
Telegram : https://t.me/Hulaadiss
YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCk934znIu60LV3czcIVZ9Bg
Twitter: https://twitter.com/Huleaadis_Media