Get Mystery Box with random crypto!

በሰሜን ኢትዮጵያው ውጊያ ሳቢያ በሰሜን ወሎ ዞን 30 ሺህ ሰዎች መፈናቀላቸውን ተመድ አስታወቀ በ | ሁሌ አዲስ ሚዲያ (Hule Addis Media)

በሰሜን ኢትዮጵያው ውጊያ ሳቢያ በሰሜን ወሎ ዞን 30 ሺህ ሰዎች መፈናቀላቸውን ተመድ አስታወቀ

በኢትዮጵያ ዳግም በተቀሰቀሰው ውጊያ ሳቢያ በአማራ ክልል በሰሜን ወሎ ዞን ተጠልለው የነበሩ 30 ሺህ ሰዎች ለሁለተኛ ጊዜ ለመፈናቀል መዳረጋቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) አስታወቀ። በተመሳሳይ ሁኔታ በአፋር ክልል ካሉ ሶስት ወረዳዎች በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንደተፈናቀሉ ሪፖርት እንደደረሰው የመንግስታቱ ድርጅት ገልጿል።

የተመድ ቃል አቃባይ ስቴፈን ዱጃሪች ትላንት ማክሰኞ ነሐሴ 24 ምሽት በሰጡት ዕለታዊ መግለጫቸው፤ በሰሜን ኢትዮጵያ የተቀሰቀሰው ግጭት በመቀጠሉ ሁኔታ በአካባቢው ያለው ሁኔታ ውጥረት የተሞላበት እንደሆነ ተናግረዋል። በተለያዩ አካባቢዎች ሰዎች እየተፈናቀሉ ነው መባሉ፤ የሰብዓዊ መብት ፍላጎትን እንደጨመረውም ጠቁመዋል።

ቃል አቃባዩ በዚሁ መግለጫቸው፤ የአፋር ክልል ከትግራይ ጋር በሚዋሰንባቸው ቦታዎች በሚገኙት በያሎ እና ጉሊና ወረዳዎች እየተካሄደ ባለው ውጊያ ሳቢያ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንደተፈናቀሉ ሪፖርት መደረጉን ጠቅሰዋል። በአፋር እና አማራ አዋሳኝ ቦታ በሚገኘው ጭፈራ ወረዳም፤ ሰዎች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን የሚያመለክት ሪፖርት እንዳለ ዱጃሪች ለጋዜጠኞች አስረድተዋል።

ለወቅታዊ እና ለፈጣን መረጃዎች የሁሌ አዲስ ሚዲያ የማህበራዊ ሚዲያዎችን ይቀላቀሉ።

Facebook : https://www.facebook.com/Huleadissmedia/
Telegram : https://t.me/Hulaadiss
YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCk934znIu60LV3czcIVZ9Bg
Twitter: https://twitter.com/Huleaadis_Media