Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ መምህራን ማሕበር ጦርነቱ ቆሞ ድርድር እንዲጀመር ጠየቀ በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም የተቀ | ሁሌ አዲስ ሚዲያ (Hule Addis Media)

የኢትዮጵያ መምህራን ማሕበር ጦርነቱ ቆሞ ድርድር እንዲጀመር ጠየቀ

በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም የተቀሰቀሰው ጦርነት በአስቸኳይ ቆሞ የአፍሪካ ሕብረት ለሰላም የጀመረውን የማደራደር ኃላፊነት እንዲቀጥል የኢትዮጵያ መምህራን ማሕበር ጠየቀ።

ማሕበሩ ዛሬ በሰጠው መግለጫ በኢትዮጵያ የሚከሰቱና የተከሰቱ ግጭቶች ሁሉ በውይይት መፈታት ያለባቸውና የሚችሉ ናቸው ብሏል።

ጦርነቱ ለመምህራን ጥያቄዎች ወቅታዊ ምላሽ ለማግኘት እንቅፋት ሆኖብኛል ያለው ማሕበሩ በተለይ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን የደሞዝ ማሻሻያ እና ሌሎች ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ ግፊት ማድረጌን እቀጥላለሁ ብሏል።

የዩኒቨርሲቲ መምህራን በተለይ ለደሞዝ ጭማሪ ጥያቄዎቻቸው ምላሽ እንዲሰጣቸው ደጋግመው እየጠየቁ ሲሆን ማሻሻያ ካልተደረገ ሥራ በማቆም ጭምር ለጥያቄያቸው ምላሽ መገኘት ግፊት እንደሚያደርጉ እየገለፁ ይገኛሉ።

ለወቅታዊ እና ለፈጣን መረጃዎች የሁሌ አዲስ ሚዲያ የማህበራዊ ሚዲያዎችን ይቀላቀሉ።

Facebook : https://www.facebook.com/Huleadissmedia/
Telegram : https://t.me/Hulaadiss
YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCk934znIu60LV3czcIVZ9Bg
Twitter: https://twitter.com/Huleaadis_Media