Get Mystery Box with random crypto!

ግጥም ከገጣሚያን

የቴሌግራም ቻናል አርማ habtamu39 — ግጥም ከገጣሚያን
የቴሌግራም ቻናል አርማ habtamu39 — ግጥም ከገጣሚያን
የሰርጥ አድራሻ: @habtamu39
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.21K
የሰርጥ መግለጫ

👋🏽እንኳን ደህና መጡ በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ አዝናኝና አስተማሪ ግጥም እንዲሁም ፅሁፎች ከገጣሚያን ለእርሶ ተዝናኖት ሲባል ከእራሳችንም እንዲሁም ከየቦታው ተሰባስበው ለእናንተ የሚቀርብበት አውድ ነው!!
🙄ጊዜዎትን ስለሰጡን እናመሰግናለን🙏
ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
ግጥም ለመላክ @Habtemaryam16 ላይ አድረሱን

Ratings & Reviews

4.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-29 11:59:02 ማፍቀሬን እንደ ቀልድ አይተሽው
የፍቅሬን ጅማሬ በእንጥልጥል ተውሽው
አልወድቅ አልነሳ አለሁ እንደተንጠለጠልሁ
መልስሽን ጥበቃ አመሽ አነጋለሁ

ፈራሁ ትያለሽ ማፍቀርን መጀመር
ልብሽ ምን ይል ይሆን ስለኔ ሲነገር
እውነት አትወጂኝም እውነቱን ንገሪኝ
ልብሽን ተከተይ የሚልሽን አውሪኝ
መውደዴ ሲጨምር ያንቺው ከቀነሰ
የኔ ማፍቀር ላንቺ እንዲህ ከረከሰ

ያ ሁላ ለምን አስፈለገ
ስደውል ሳስቅሽ
ደውለሽ ሳወራሽ
በሳቅሽ ልቤን ወስደሽ
በፎቶ ቀልቤን ነስተሽ
በላይ በላይ ፎቶ ልከሽ
ለምን ቀሰቀሽው ተዳፍኖ የቀረውን
ልቤን ነካካሽው ማፍቀር ያቆመውን

ያ ሁላ ለምን አስፈለገ
በተደዋወልን ልክ ቃል የገባሽልኝ
በመሀላ መዐት ያንተው ነኝ ያልሽኝን
ስመጣ እያልሽኝ እንዲያ አጓግተሽኝ
የመጣሽ ግዜ ነው አረ እንደው የራቅሽኝ
አፈቅርሻለው በለኝ ብለሽ እንዳላልሽኝ
አፈቅርሻለው ስልሽ አንቺው ሸሸሺኝ።
fari

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
◦◦✧join
.. @habtamu39
@habtamu39
@habtamu39
308 viewsⒽⓐⓑ ²¹ , 08:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 10:21:37
"...የዝሆኖች እርግጫ የሚጎዳው ' #ሳሩን ' ነው"
ይናገራል ፎቶ https://t.me/habtamu39
596 viewsⒽⓐⓑ ²¹ , 07:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 10:20:46
በራስ ሃሳብ ማበድ
_______//________
"ኧረ ባሏ ባሏ - የፊተኛው ባሏ
እስኪ ልጠይቅህ ምንድን ነው አመሏ?"
ብዬ ብጠይቀው የፊተኛው ባልሽ፣
"ደግ ሴት ናት" አለኝ፤
"ኩሩ ሴት ናት " አለኝ ፤
"ብልህ ሴት ናት" አለኝ፤
ቀንቼ ነው መሰል ራሴን አመመኝ።
ለተፈታች ሴት ለገባች ከሌላ፣
አቅፋ ለምታድር የሌላ ሰው ገላ ፣
እንዴት የድሮ ባል በጎ ይናገራል?
መጠርጠር አለብኝ...
በመካከላችሁ አንድ እውነት ይኖራል።
_____________________________
ደሱ ፍቅርኤል
ተይው ፖለቲካውን ዝም ብለሽ ሳሚኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
◦◦✧join
.. @habtamu39
@habtamu39
@habtamu39
827 viewsⒽⓐⓑ ²¹ , 07:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 10:20:29
"እምዬ ኢትዮጵያ ፣ ሞኝ ናት ተላላ"
በችግር ሚኖሩ ፣ ሚሊዮኖች አዝላ
ለጥቂቶች ስልጣን ፣ ለጥቂቶች ተድላ
ለጥቂቶች ብላ
ዘመናቶች ሲያልፉ ፣ አቅሟን እየናደው
ልጇን ታስበላለች ፣ ለመጣ ለሔደው!!! Belay Bekele Weya

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
◦◦✧join
.. @habtamu39
@habtamu39
@habtamu39
547 viewsⒽⓐⓑ ²¹ , 07:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 10:20:15 አንቺን ማቀፍ
ከሰው መግዘፍ
አንቺን መሳም
አድሮም መጣም
አንቺን ማፍቀር አለው የደስ ደስ
ፍቅርሽ እኔ ላይ ዘላለም ይንገስ
የፍቅሬ ቅኔ በዚህ ግጥም ይድረስ fari

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
◦◦✧join
.. @habtamu39
@habtamu39
@habtamu39
395 viewsⒽⓐⓑ ²¹ , 07:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 10:20:15 ልጅቱ

ወይ ግሩም ይደንቃል የጊዜው ሁኔታ፤
ለምን አስጨነቃት ልጅቱ ውበቷ?
ገና ልጅ ስትሆን በእድሜዋ ጨቅላ፤
ዘላ ሣትጠግብ በደንብ ሳትበላ ፤
በቅጡ ሣይበስል ያ የህፃን ገላ፤
የጓደኛን ዳሌ ማየቱ ያጓጓት፤
ከዉስጧ ፈንቅሎ እንዲያ ያናገራት፤
ብሶባት ይሆን ወይ ስሜቷ አይሎባታ!?
ተስፋዬ ላቀው

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
◦◦✧join
.. @habtamu39
@habtamu39
@habtamu39
426 viewsⒽⓐⓑ ²¹ , 07:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 21:10:55
እንጀራ ተይዞ እንጀራ ፍለጋ https://t.me/habtamu39
682 viewsⒽⓐⓑ ²¹ , 18:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 21:08:15 """"እየጠሉ ማግኘት"""
( በላይ በቀለ ወያ )
.
.
አለ ወዶ ማጣት ፣ አለ ጠልቶ ማግኘት
የሚሆን አልሆን ሲል ፣ የማይሆን መመኘት
ቀጥ ያለ ሲታጣ
መመልመል ጎባጣ
አለ ጠልቶ ያገኘ ፣ አለ አፍቅሮ ያጣ፡፡
አለ ቡዙ ብዙ .. .
ምንም ብርቄ አይደለም !
ኖሬ ያለፍኩት ነው ፣ ስንኖር ያየሽኝ
ወድጄሽ አጣሁሽ ፣ ጠልተሽ አገኘሽኝ፡፡
ብኖር የለሁሽም ፣ ባትኖሪም አለሽኝ!!!

( በላይ በቀለ ወያ )

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
◦◦✧join
.. @habtamu39
@habtamu39
@habtamu39
620 viewsⒽⓐⓑ ²¹ , 18:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 21:08:15 ላልቅስበት

ከ ቴዲ አፍሮ

*በነገር ፍም እሳት እያቃጠላቹ
*ለማዘኔ ምክንያት እናንተው ሆናቹ
*አታልቅስ አትበሉኝ ከፍቶኝ እያያቹ
ሁሉም እየጫረ እሳት ሲለኩሰው
ሻማ እንኳን ያነባል እንባ አውጥቶ እንደሰው!!

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
◦◦✧join
.. @habtamu39
@habtamu39
@habtamu39
847 viewsⒽⓐⓑ ²¹ , 18:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 20:55:23 ባሎችሽ ዘጠኝ እኔ አስረኛ
በየት በኩል አቅፌሽ ልተኛ
#አለ_አንዱ


ቻናላችንን ይቀላቀሉ
◦◦✧join
.. @habtamu39
@habtamu39
@habtamu39
133 viewsⒽⓐⓑ Bl@ck H@besh@ , 17:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ