Get Mystery Box with random crypto!

ማፍቀሬን እንደ ቀልድ አይተሽው የፍቅሬን ጅማሬ በእንጥልጥል ተውሽው አልወድቅ አልነሳ አለሁ እንደተ | ግጥም ከገጣሚያን

ማፍቀሬን እንደ ቀልድ አይተሽው
የፍቅሬን ጅማሬ በእንጥልጥል ተውሽው
አልወድቅ አልነሳ አለሁ እንደተንጠለጠልሁ
መልስሽን ጥበቃ አመሽ አነጋለሁ

ፈራሁ ትያለሽ ማፍቀርን መጀመር
ልብሽ ምን ይል ይሆን ስለኔ ሲነገር
እውነት አትወጂኝም እውነቱን ንገሪኝ
ልብሽን ተከተይ የሚልሽን አውሪኝ
መውደዴ ሲጨምር ያንቺው ከቀነሰ
የኔ ማፍቀር ላንቺ እንዲህ ከረከሰ

ያ ሁላ ለምን አስፈለገ
ስደውል ሳስቅሽ
ደውለሽ ሳወራሽ
በሳቅሽ ልቤን ወስደሽ
በፎቶ ቀልቤን ነስተሽ
በላይ በላይ ፎቶ ልከሽ
ለምን ቀሰቀሽው ተዳፍኖ የቀረውን
ልቤን ነካካሽው ማፍቀር ያቆመውን

ያ ሁላ ለምን አስፈለገ
በተደዋወልን ልክ ቃል የገባሽልኝ
በመሀላ መዐት ያንተው ነኝ ያልሽኝን
ስመጣ እያልሽኝ እንዲያ አጓግተሽኝ
የመጣሽ ግዜ ነው አረ እንደው የራቅሽኝ
አፈቅርሻለው በለኝ ብለሽ እንዳላልሽኝ
አፈቅርሻለው ስልሽ አንቺው ሸሸሺኝ።
fari

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
◦◦✧join
.. @habtamu39
@habtamu39
@habtamu39