Get Mystery Box with random crypto!

,,,,የማርያም መቀነት,,,, ,, ,, '''ማር ውሃ ጠጥቶ...ጠጅ ሚደገምበት ጉዝጉዞ መሶብ ላይ. | ግጥም ከገጣሚያን

,,,,የማርያም መቀነት,,,,
,,
,,
"""ማር ውሃ ጠጥቶ...ጠጅ ሚደገምበት
ጉዝጉዞ መሶብ ላይ...አይብ ሚታጨቅበት፡
ከማማው ባሻገር
ከተራራው ወዲያ ...ቅር ትዝ የሚለኝ
የሰው ልጅ መገኛ...እኔስ ሐገር አለኝ።""
ብላ ስታወራኝ
""ይኼውልሽ ውዴ
ሐገር ሐገር አትበይ...ግፍ አትናገሪ
እኔም ሐገር አለኝ
አለም ያደነቃት...ሰውን ከአፈር ሰሪ።!""
ብየ ስገልጽላት
ወዴት ናት ያንተ ሐገር
አሳየኝ ትላለች.....ያች የኔ ቀብራራ
በእምየ ማሕጸን...ሠፈር ተገትራ፡
ወትሮም እንደዚህ ነው
የማርያም መቀነት
ሠማይ ላይ እያዩ
ኢትዮጵያን ለማወቅ..... ትእግስቱ ካለቀ
ሐገር አትታይም
በስሟ እየማሉ........ሠፈር ለወደቀ።!!!
,,
,,
@ዘላለም ሞትባይኖር

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
◦◦✧join
.. @habtamu39
@habtamu39
@habtamu39