Get Mystery Box with random crypto!

የማብድ ቢመስለኝ ፣ ድንገት አንቺን ሳጣ አረቄ ቤት ሔጄ ፣ አረቄ ስጠጣ አንድ ግጥም ሰማሁ ፍቅርሽ | ግጥም ከገጣሚያን

የማብድ ቢመስለኝ ፣ ድንገት አንቺን ሳጣ
አረቄ ቤት ሔጄ ፣ አረቄ ስጠጣ
አንድ ግጥም ሰማሁ
ፍቅርሽን ከልቤ ፣ ነቅሎ የሚያወጣ፡፡
ያውም መንገድ በሚል...
ለመንገደኛ ሰው ፣ ሰካራም የፃፈው
እዛ ጋ ቁጭ ብሎ...
"ከዳችኝ" እያለ ፣ የሚለፈልፈው
መንገድ የሚል ግጥሙ ፣ጆሮዬን ገረፈው፡፡
ጆሮዬ ሲገረፍ ፣
ጠባሳ ጣለብኝ ፣ ግጥሙን እንዳልረሳ
"መንገድ አያደርስም
መንገድ አይመልስም ፣ እግር ካልተነሳ!!!"
እያለ ይገጥማል...
ደጋግሞ ደጋግሞ ፣ ሌላ አይናገርም
እሱም ልክ እንደኔ ...
አንዷን በመሔዷ ፣ ሳያጣት አይቀርም፡፡
ብቻ ሰክሪያለሁ
ለመንገደኛ ሴት ፣
የተፃፈ ግጥምን ፣ ጆሮዬ ያደሞጣል
መሔድሽን ያየ
እንደሌሌሽኝ ሲያውቅ ፣ ሊኖረኝ ይመጣል
ይህ ነው መንገድ ማለት!
የሰካራም ግጥምን ሰክሬ ስረዳው
ማፍቀረ ሳይሆን ለኔ ፣ መርሳት ነው ሚጎዳው!!!

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
◦◦✧join
.. @habtamu39
@habtamu39
@habtamu39