Get Mystery Box with random crypto!

''''እየጠሉ ማግኘት''' ( በላይ በቀለ ወያ ) . . አለ ወዶ ማጣት ፣ አለ ጠልቶ ማግኘት የሚ | ግጥም ከገጣሚያን

""""እየጠሉ ማግኘት"""
( በላይ በቀለ ወያ )
.
.
አለ ወዶ ማጣት ፣ አለ ጠልቶ ማግኘት
የሚሆን አልሆን ሲል ፣ የማይሆን መመኘት
ቀጥ ያለ ሲታጣ
መመልመል ጎባጣ
አለ ጠልቶ ያገኘ ፣ አለ አፍቅሮ ያጣ፡፡
አለ ቡዙ ብዙ .. .
ምንም ብርቄ አይደለም !
ኖሬ ያለፍኩት ነው ፣ ስንኖር ያየሽኝ
ወድጄሽ አጣሁሽ ፣ ጠልተሽ አገኘሽኝ፡፡
ብኖር የለሁሽም ፣ ባትኖሪም አለሽኝ!!!

( በላይ በቀለ ወያ )

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
◦◦✧join
.. @habtamu39
@habtamu39
@habtamu39