Get Mystery Box with random crypto!

በራስ ሃሳብ ማበድ _______//________ 'ኧረ ባሏ ባሏ - የፊተኛው ባሏ እስኪ ልጠይቅህ ም | ግጥም ከገጣሚያን

በራስ ሃሳብ ማበድ
_______//________
"ኧረ ባሏ ባሏ - የፊተኛው ባሏ
እስኪ ልጠይቅህ ምንድን ነው አመሏ?"
ብዬ ብጠይቀው የፊተኛው ባልሽ፣
"ደግ ሴት ናት" አለኝ፤
"ኩሩ ሴት ናት " አለኝ ፤
"ብልህ ሴት ናት" አለኝ፤
ቀንቼ ነው መሰል ራሴን አመመኝ።
ለተፈታች ሴት ለገባች ከሌላ፣
አቅፋ ለምታድር የሌላ ሰው ገላ ፣
እንዴት የድሮ ባል በጎ ይናገራል?
መጠርጠር አለብኝ...
በመካከላችሁ አንድ እውነት ይኖራል።
_____________________________
ደሱ ፍቅርኤል
ተይው ፖለቲካውን ዝም ብለሽ ሳሚኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
◦◦✧join
.. @habtamu39
@habtamu39
@habtamu39