Get Mystery Box with random crypto!

እውቀትን ፍለጋ

የቴሌግራም ቻናል አርማ ewiketinfilega — እውቀትን ፍለጋ
የቴሌግራም ቻናል አርማ ewiketinfilega — እውቀትን ፍለጋ
የሰርጥ አድራሻ: @ewiketinfilega
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 145
የሰርጥ መግለጫ

👍 join @EwiketinFilega
👍 አስተያየት ለመስጠት @Eshetu21bot
👉 join Facebook page :👇👇👇https://www.facebook.com/profile.php?id=100027751276659
👉 Twitter :👇👇👇👇👇 https://mobile.twitter.com/EshetuAyalewMo1

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-09 03:52:32 ሕይወት ረጅም ጉዞ ነው! ዘመን ጎዳና ነው!

ሕይወት ረጅም ጉዞ ነው፤ ሠው መንገደኛ ነው፡፡ ዘመን ጎዳና ነው፡፡ ወሳጁ አዕምሮ ነው፡፡ ተሳፋሪው ልብ ነው፡፡ ሠው በየዕለቱ፣ በየሠዓቱና በየደቂቃው ጉዞ ላይ ነው፡፡ ጉዞውን በአቋራጭ ለመሄድ የሚሞክር አለ፡፡ ቀጥተኛውን መንገድ ይዞ ሳይታክትና ሳይደክም የአስተሳሰብ ውሃ ጥሙን፣ የአመለካከት በረሃውን ችሎ፣ አደናቃፊውን ሽፍታ ሃሳብ እያለፈ ወደዕጣፋንታው የሚነጉድም ብዙ ነው፡፡ የዘመንን ጎዳና አሳምሮ የሚመላለስ አለ፡፡ በዚያው ልክ ደግሞ የሕይወት መንገዱን እያበላሸ፣ ድልድዩን ሃሳብ እያፈረሠ፣ የትውልድ ባህሩን እያደፈረሠ፤ እኔ ብቻ ልለፍ እንጂ ሌላኛው የራሱ ጉዳይ ብሎ ኋላውንና ጎኑን ሳያይ፣ ሌላውን መንገደኛ ትቶና ንቆ ፊቱን ብቻ እያየ የሚጓዝ አለ፡፡ የሕይወት ጎዳና ማለቂያውና መጨረሻው ሞት መሆኑን የተረዳ ግን የሕይወት እርምጃው የተስተካከለ ይሆናል፡፡

ጋሊኖስ የተባለ ፈላስፋ እንዲህ ይለናል፡-

‹‹በዚህ ዓለም የሚኖሩ ሠዎች ሁሉ አኗኗራቸው የመንገደኛ አኗኗር መሆኑን ሊያውቁ ይገባቸዋል፡፡ መንገደኛ ከደረሠበት ሐገር አድሮ ሲነጋ ተነሥቶ እንደሚሄድ ሁሉ እነሱም ከዚች ዓለም በሞት ተለይተው ይሄዳሉ፡፡›› በማለት የዓለም እንግድነታችንን ይናገራል፡፡

ብልህ ሠው ጉዞውን በድንብርብር አይጀምርም፡፡ አስቀድሞ በደመነፍስ ከመድፈር ይልቅ በመጠንቀቅ ጉዞውን ያጠናል፡፡ ጥንቁቅነት ፍራቻ አይደለምና ጥንቃቄው እንዲማር ያደርገዋል፡፡ ከተማረም ያያል፤ ካየም ያስተውላል፡፡ ካስተዋለም ዕውቀት ይኖረዋል፡፡ ዕውቀት ካለውም ይሠራል፡፡ ከሠራም ስጋዊ ዓለሙን አሸንፎ የወዲያኛው ዓለሙን በዕውቀትም፣ በግብርም፣ በእምነትም፣ በምክንያትም ይገነባል፡፡ ‹‹ካልተማሩ አያውቁ፣ ካላወቁ አይጸድቁ›› እንዲሉ አበው የሕይወት ጉዞው ስኬታማ ይሆናል፡፡

ሠው በውስጡም በውጪም ተጓዥ ነው፡፡ ሞኝ ሠው በራሱ ባልሆነ መንገድ የሌላን ሠው ዳና እየተከተለ ገደል ይገባል፡፡ ብልሕ ሠው ግን ራሱንና የራሱን መንገድ ለማግኘት ይጓዛል፡፡ ውስጣዊው ጉዞው የነፍስ ሲሆን፤ ውጫዊው ጉዞ የስጋ ነው፡፡ የነፍስ ጉዞው አሻጋሪ ሲሆን፤ የስጋው ጉዞው ግን የሆነ ጊዜ ላይ አላቂ ነው፡፡ ዕድሜ ገደብ አለው፡፡ የነፍስ ጉዞ የሃሳብ ሸንተረሩን አልፎ፣ ዳገትና ቁልቁለቱን ወርዶ ሠብዓዊነቱ ጋር ይደርሳል፡፡ የስጋዊ ጉዞ ግን ማጠናቀቂያው ሞት ነው፡፡

ከነገስታት አንዱ ዘመን እንዴት ያለ ነው ብሎ አንዱን ፈላስፋ ቢጠይቅ፡- ‹‹ዘመን ማለት አንተ ነህ፡፡ አንተ ሠላማዊ ስትሆን ዘመን ሠላማዊ ይሆናል፡፡ አንተ የከፋህ እንደሆነ እንዲሁ ይከፋል›› አለው ይባላል፡፡

እውነት ነው! ሠው ዘመኑን መፍጠር ባይችልም በዕድሜው ላይ አሉታዊም ሆነ አዎንታዊ ጫና መፍጠር ይችላል፡፡ ሠው የራሱ ሠዓሊ ነው፡፡ ቀለሙ አስተሳሰቡ ነው፡፡ ሠሌዳው ሕይወቱ ነው፡፡ ብሩሹ ምግባርና ግብሩ ነው፡፡ በሕይወት ብሩሹ ዘመኑን አሳምሮ ይቀባል፤ አልያም አበላሽቶ አስጠዪ ያደርጋል፡፡

ዘመን ውበቱ የሚገለጠው በዘመኑ ውስጥ አፍቃሪና ተፈቃሪ አንድ የሚሆኑበት ፍቅር ሕያው ሲሆን ነው፡፡ ታናሽ ታላቁን ሲያከብር፣ ታላቅ ታናሹን ሲመክር፣ አዛውንት፣ አሮጊቶች በልጆቻቸው ተከብረው ሲጦሩ፣ ሠው በሠውነቱ ሲኖር፣ ጥላቻ፣ ጦርነት፣ መካካድ፣ መገዳደል፣ መወጋገዝ፣ መናናቅ፣ መጠላላት ወዘተ ክፉ ነገሮች ሁሉ ሲወገዱና ሲጠፉ ዘመኑ መልካም ዘመን ነው እንላለን፡፡ የዚህ ዘመን አባል የሆነ ትውልድ ጉዞው ስኬታማ ይሆናል።

ወዳጆች የዘመን ክፋቱና ክርፋቱ የሚጀምረው እርስበርስ በመለያየት ነው፡፡ ጥላቻ ፅንሠቱ ካለማወቅ የሚመነጭ ነው፡፡ ዕውቀት በፍቅር ሲሟሽ አዕምሮ በጥላቻ አይሠክርም፡፡ በጥላቻ ናላውን ያጣ ሠው የሚያደርገውን አያውቅም፡፡ አላዋቂ ሠው ዘመኑን እርም የሚያሠኝ ተግባር በገዛ እጆቹ ይፈፅማል፡፡ በፈፀመውም ክፉ ነገር ሲሰቃይ ይኖራል፡፡ በስቃዩም ደስታን ያጣል፡፡ ደስታ በማጣቱም በሕይወት ተስፋ ይቆርጣል፡፡ ተስፋ በመቁረጡም ሕይወቱን ዓላማ የለሽ ይሆናል፡፡

ወዳጄ ሆይ ሕይወት ረጅም ጉዞ ነው፡፡ በዚህ ማለቂያ ባለው ጉዞ ቀሪ ታሪክ ሠርተህ ለማለፍ ልብህን በቅንነት፤ አዕምሮህን በመልካምነት መላልሶ መስራት ያስፈልግሃል፡፡ ቅንነት የጎደለው የሕይወት ጉዞ መጨረሻው አያምርም፡፡ ፍቅር ያነሠው ህይወት ብኩን ነው፡፡ ለትዝታህ የሚሆን እንኳን መልካም ነገር ማድረግ ሕይወትን ያድሳል፡፡ ስታረጅ መልካሙ ትዝታህ ያጫውትሃልና፡፡

‹‹ዘመን ማለት አንተ ነህ፡፡ አንተ ሠላማዊ ስትሆን ዘመን ሠላማዊ ይሆናል፡፡ አንተ የከፋህ እንደሆነ እንዲሁ ይከፋል››

እሸቱ ብሩ ይትባረክ

ቸር ጊዜ!
@Ewiketinfilega
@Ewiketinfilega
93 viewsEshe Man, 00:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-02 05:30:11 ድልድዮቹን ተውልን

መሀል ላይ ተገምሰው ማዶ ለማዶ የሚያተያዩን ሰባራ ድልድዮች እየበዙ ነው… አንዳንዶቹን ሆን ብለን ሰብረናቸዋል... አንዳንዶቹ በሌሎች ሰንኮፎቻችን ዳፋ ተሰብረዋል... ሌሎቹን ግን መሰበራቸውን እንኳ አልተረዳንም...

አንዳንዶች የሚሰብሩትን ድልድይ ፋይዳ በወቅት ስሜታቸው ትኩሳት ውስጥ ብቻ ስለሚመዝኑ የሰባሪነት ወኔ እንጂ የአስተዋይነት ስክነት ከቶም አይታይባቸውም... ሰብረው መሄዳቸውን እንጂ መመለሻ ማጣታቸውን አያስተውሉም...

ጎበዝ... ጊዜው የተሰበሩ ግንኙነቶችን የምንጠግንበት እንጂ ሌሎች የአብሮ መኖር ምልክት የሆኑ ድልድዮችን የምንሰብርበት አይደለም... አዲስ ድልድይ ባትሰራ እንኳ ነባር ድልድይ አለማፍረስ ደግ ነገር ነው...

ድልድዮቻችንን እንያቸው እስኪ... ተጎምደው የቆዩንም ሆነ በእኛው የተገመደሉት ቅን ልቦቻችንን ይናፍቃሉ... መሰረታቸው ጠንካራ የሆኑትን ባሉበት እንጠግናቸው… የስብራታቸው ዳፋ ለሕልውናቸው ስጋት ከመሰለን ደግሞ በአዲስ መልክ እንስራቸው… ደግመው የማይሰሩትን ማፍረስ ግን መመለሻ ያሳጣል... የሰበሩትን ዳና ማጥፋት የልጆችን ወኔ ይሰልባል…

ግንባታ ላይ እንጠመድ ጎበዝ… የቤተሰብን ሰባራ እንጠግን፣ የሕብረተሰብን ሰባራ እንጠግን፣ የጓደኝነትን ሰባራ እንጠግን… የትውልድን ሰባራ እንጠግን፣ የግለሰብን ሰባራ እንጠግን፣ የተቋምን ሰባራ እንጠግን፣ የጉርብትና ሰባራ እንጠግን፣ የአስተሳሰብን ሰባራ እንጠግን፣ የልጅነትን ሰባራ እንጠግን፣ የወጣትነትን ሰባራ እንጠግን፣ የአዛውንትነትን ሰባራ እንጠግን…

አዎን ግንባታ ላይ እንጠመድ… የምድሪቱ ሰባራ መጠገን ይሻል፣ የሰላም ሰባራ መጠገን ይሻል፣ የአንድነት ሰባራ መጠገን ይሻል፣ የእውነት ሰባራ መጠገን ይሻል፣ የፍቅር ሰባራ መጠገን ይሻል...

እንዳይፈርስ የመጠበቁን ያህል አዲስ ግንባታችን ደግሞ የትናንት ሰንኮፎቻችንን ለማሻገር አይሁን… ውድቀቶቻችንን ለማሻገር አይሁን… እንክርዳዱን ለማሻገር አይሁን… ቂምና ቁርሾ ለማሻገር አይሁን… ያልኖርንበትን ዘመን እንከን ለተለገስነው ዛሬም ሆነ ለምናወርሰው ነገ ለማሻገር አይሁን…

ክፋትን ለማስረጽ የቀየስነውን አፍርሰን የመልካምነት መሸጋገሪያ የሆነውን እንገንባ… ነባር ማፍረሱን ትተን ለሕልውናው እንትጋ...

"Problems cannot be solved at the same level of awareness that created them" _ Albert Einstein

ፍቅርን ከመስጠት በላይ ዕዳ አይኑርባችሁ!!

@Ewiketinfilega
@Ewiketinfilega
120 viewsEshe Man, 02:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-22 06:56:15 ኩርፊያ፣ ቂም፣ ጥላቻና ብቀላ ጊዜ ገዳይና የስኬታማ ህይወት ጠላት ናቸው። ልዩነት ተፈጥሯዊ ነው። ልዩነት ሁሌም ይኖራል። በልዩነት አትበሳጭ። ከልዩነት ጋር መኖርን እወቅበት።

ዓለም የምትሽከረከረው፣ የምትሾረው፣ ወደፊት የምትራመደው በልዩነት ነው። ልዩነት የእድገት ምንጭ ነው። አላዋቂዎች ግን ልዩነትን የኩርፊያ ምንጭ ያደርጉታል። ያ ትልቅ ስህተት ነው!

ልዩነትን የምትፈታው በንግግር እንጂ በኩርፊያ አይደለም። ነገርን በልብ ይዞ ማመንዥክ ለራስም ለሌላውም አይጠቅምም። ኩርፊያ ጊዜን፣ ጤናን ሀብትን ይበላል። ኩርፊያ የቂም እናትና አባት ነው።

አመለካከትህ ቅንና በጎነትን የተላበሰ ይሁን። ካንተ የተለየ አመለካከት ያለው ሰው ሁሉ የተሳሳተ ነው ብለህ አትደምድም። በልዩነትም ይሁን በስምምነት ውስጥ ሁሌም የሌላውን ፍላጎት ለመረዳት ሞክር።

በተቻለህ ዓቅም የሌላውን ሰው ስሜት ላለማስቀየም ሞክር። እውነት ስለሆነ ብቻ ሌላውን የሚያስቀይም ንግግር አትናገር። በስሜት አትነዳ፣ ስሜትህን ተቆጣጠር።

ልዩነት ሁሉ በአንድ ጊዜ ካልተፈታ አትበል። ለጊዜ እድል ስጠው።
ልዩነትን በውይይት ፍታና ህይወትን ፍክት ብለህ ኑር!አለዚያም ከልዩነት ጋር በሰላም መኖርን ተለማመጂ!
ለማን ጀቴ/ብለህ ታኮርፋለህ/ታኮርፊያለሽ?
ፈታ በል ወዳጄ!
Toughe g.kebede
@Ewiketinfilega
@Ewiketinfilega
135 viewsEshe Man, 03:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-04 04:54:37 ጉንዳኖች ውሀ ሲሻገሩ አይተህ ታውቅ ከሆነ በውሃው ላይ ተያይዘው ተያይዘው ይቆማሉ። ጉንዳኖች ተያይዘው በወንዝ ላይ በሚሰሩበት መንገድ ሌሎች ብዙ ጉንዳኖች ይሻገራሉ። ተያይዘዉ ይሻገራሉ። ተደጋግፈው አስፈሪውን ወንዝ ይሻገሩታል። ባይያያዙና ባይደጋገፉ ግን አይቻላቸውም። አንዲት ጠብታ ዝናብ ለአንድ ጉንዳን ውቅያኖስ ብትሆንም ብዙ ጉንዳኖች አንድ ላይ ከተያያዙ ግን ውቅያኖስ መሻገር ይችላሉ።..." "ዴርቶጋዳ"

ፍቅር የበጎ ነገሮች መክፈቻ ነው፡፡ በፍቅር ያልተዘጋ ሴራ የለም፡፡ በፍቅር ያላበቃለት ጦርነት የለም፡፡ በፍቅር አደብ ያልገዛ ጦረኛ የለም፡፡ ፍቅር የነገሮች መጠቅለያ፣ የበጎ ነገሮች መሠረት ነው፡፡ የሠው ልጅ ጭንቅላቱን በፍቅር ከሞላ ክፉ ሃሳቦችና ተልካሻ ሴራዎች ወደእሱ ድርሽ አይሉም፡፡ በፍቅር የተሞላ ጭንቅላት ትርፉ በፍቅር መኖር ነው፡፡

ጦርነት በሕይወትና በቁስ ላይ ከሚያስከትለው ጥፋት የበለጠ የሚያስጠላ ነገር በዚህ ዓለም ያለ አይመስለኝም። የሰው ልጅ በመካከሉ የሚፈጠሩትን ልዩነቶች በውይይትና በሠላም የሚፈታበት ቀን መች ይመጣ ይሆን? ያ ቀን ናፈቀኝ። "በዓሉ ግርማ"

ውብ አሁን
@Ewiketinfilega
@Ewiketinfilega
169 viewsEshe Man, 01:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-01 06:44:37 አለቃ ወይስ መሪ?
(“አመራር A to Z” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ)

መሪ ሁሉ አለቃ ነው፣ አለቃ ሁሉ ግን መሪ አይደለም!

መሪ ባለው ቀደም ብሎ የመራመድ ሚና ፈርን የመቅደድ ሃላፊነቱ ስላለው አለቃም ነው ብንል አንሳሳትም፡፡ ሆኖም፣ በተለያዩ የስልጣን ምንጮች አለቃ የሆኑ ሁሉ መሪዎች ናቸው ለማለት አስቸጋሪ ነው፡፡ አለቃ፣ አለቃ ነው፤ በማስፈራት ይገዛል እንጂ አይመራም፡፡ መሪ አለቃ ነው ተብሎ ቢጠራም እንኳ በተለምዶ አለቆች የሚያሳዩትን ባህሪ አያንጸባርቅም፡፡ ስለዚህ መሪ የአለቅነቱ ዝንባሌ በጎላ ቁጥር የመሪነቱ መልክና ተጽእኖ እየደበዘዘና እየጠፋ ይሄዳል፡፡

ማንኛውም አለቃ መሪ ለመሆን በተከታዮቹ ወይም በሰራተኞቹ ላይ የአብሮ ሰራተኝነትን ስሜት ሊያሳድር ይገባዋል፡፡ “አለቃ ስለሆንኩኝ ብቻ ሊታዘዙኝና ሊያከብሩኝ ይገባል” ከሚል አመለካከት ወጥቶ በሚያስፈልጋቸው ሁኔታ ሁሉ ለመገኘት ራሱን በማቅረብ፣ ብቃቱን በማዳበርና በምሳሌነት በመምራት ተጽእኖን ማሳደር ይጠበቅበታል፡፡

ስለዚህም ሰዎች፣ መሪን በናፍቆትና በአክብሮት ሲታዘዙት፣ አለቃን ግን በፍርሃት ይታዘዙታል፡፡ የሚከተሉትን ንጽጽሮች እንመልከት፡፡

• አለቃ ሰዎችን በኃይል ይነዳል፤ መሪ ሰዎችን በመልካም ተጽእኖ ያነሳሳል፡፡

• አለቃ በስልጣኑ ላይ ይደገፋል፤ መሪ ባዳበረው ተቀባይነት ላይ ይደገፋል፡፡

• አለቃ ፍርሃትን ይለቅቃል፤ መሪ ፍቅርንና አክብሮትን ያስፋፋል፡፡

• አለቃ “እኔ” ማለት ያበዛል፤ መሪ “እኛ” ይላል፡፡

• አለቃ ስህተተኛው ማን እንደሆነ ያውጣጣል፤ መሪ ስህተቱን ፈልጎ ለማረም ይፈጥናል፡፡

• አለቃ ትኩረቱ ስራው መሰራቱ ላይ ብቻ ነው፤ መሪ ስራውን የሚሰሩት ሰዎች ላይም ትኩረቱን ይጥላል፡፡

• አለቃ ካላከበራችሁኝ ይላል፤ መሪ በሁኔታው መከበርን ያነሳሳል፡፡

በነገራችን ላይ የእውነተኛ መሪነት ጉዞ የሚጀምረው የአንድ ድርጅት የበላይ ከመሆን ሳይሆን አሁን ባለንበት ደረጃ ከሚኖረን ትክክለኛ መርህና ዝንባሌ መሆኑን አንዘንጋ፡፡

ዛሬ በመሪነት ሳይሆን በአለቅነት ዝንባሌ የሚሰሩ የድርጅት አመራሮች ትናንትና በመሪዎቻቸው የአለቅነት ዝንባሌ ሲበሳጩ የነበሩና ከዚያ ሁኔታ ትምህርትን ሳያገኙ ዛሬ ስልጣን ሲይዙ ያንንንው ስህተት የሚደግሙ ናቸው፡፡

አመራር ማለት መልካም ተጽእኖ በማምጣት ሰዎች ራእዩን በመከተላቸው የሚያገኙትን እድገትና ጥቅም በማሳየት ቀዳሚ መሆን ማለት ነው እንጂ ስልጣንን መቆናጠጥ ብቻ አይደለም፡፡

@Ewiketinfilega
@Ewiketinfilega
152 viewsEshe Man, 03:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-29 20:31:16 የአዕምሮ ሠላም የህይወታችን ዋስትና እንዲሁም የደስታችን እርሾ ነው፡፡ ሠው በአዕምሮው ሠላም ከተሠማው ሕይወቱ ፍስሃ የተሞላበት ይሆናል፡፡ ገንዘብ እና ሌሎችም ትርፍ ነገሮች ከአዕምሮ ጤና መሆን በኋላ ሊመጡ የሚችሉ ተቀፅላዎች ናቸው፡፡ ከሁሉ አስቀድሞ አዕምሯችንን ልንንከባከበው ግድ ይለናል፡፡እንኳን ከሌሎች ሠዎች ቀርቶ ከራሳችን ጋር ተስማምተን ለመኖር የአእምሮ ሠላም እና ጤና መሆን በሕይወታችን ላይ ሁሌ አሸናፊ ሆነን መኖር እንድንችል ጉልህ ድርሻ አለው፡፡

ሠዎች ለአዕምሯቸው ሠላምን የሚመግቡት ከሆነ ደስ የማይልና የማይወደድ ትልቅ ነገር በሕይወታቸው ቢያጋጥማቸው እንኳን ከችግሩ መወጣጫ መንገዱን አያጡትም፡፡ እንዴት ነው የአእምሮ ሠላምን ልናገኝ የምንችለው ብለን ስንጠይቅ፤ እንደ እኔ ሃሳብ የዓለምን ተፈጥሮ በደንብ የተረዳ ሠው በዓለም ሳለ ለሚገጥሙት ፈተናዎች መልካም ምላሽ ይኖረዋል እላለሁ፡፡ ሠው ለራሱ ቅን ከሆነ ለሌሎችም ቅን ይሆናል፡፡

ሠው በመሆናችን ብቻ ደስታና ሃዘን፣ ማጣትና ማግኘት፣ መውደቅና መነሣት፣ ማመንና መከዳት እንዲሁም ውጣ-ውረድ የተሞላበት መሠናክል ይፈራረቁብናል፡፡ ዋናው ነገር በነዚህ ነገሮች ተፈትኖና ነጥሮ መውጣት ከሁላችንም ይጠበቃል፡፡ፈጣሪ ይህንን ድንቅ አዕምሮ ወይም ልዩ መክሊት ሲሠጠን በመጣው ወጀብ እንድንወሠድ ሳይሆን በጥበብና በዕውቀት ችግሮችን ፈትተን፣ ትምህርት ወስደን፣ እንደወርቅ በእሳት ተፈትነን በማስተዋል ነጥረን እንድንወጣ ነው፡፡

አስደሳች ፍጻሜ አጠብቅ ፣ህይወት ሁሌም ሁለትዮሽ ናት፣ መኖርን ምሉዕ የምናደርገው ሁለት ተቃራኒዎችን በሚዛን በመከወን ነው፡፡ እንባም ሳቅም፣ ደስታም ኀዘንም ፣ መስጠትም መቀበልም ፡፡ መሙላትም መጉደልም። ሲጠቃለል ፣ ሕይወት ኅብረ ቀለሟ ያማረ ቀስተ ደመና ነች።

At the end of your life, all the things you accumulated and achieved won't make you happy, it is who you have become as a person that really makes you happy.

Don't wait for a happy ending, you don't have forever to live. Let your happy ending starts today. Be happy all along, from now till you draw your final breath.

ውብ ምሽት
@Ewiketinfilega
@Ewiketinfilega
116 viewsEshe Man, 17:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-24 14:29:08 #ትንሳኤ

ውድ የክርስትና እምነት ተከታይና የሌላም እምነት ተከታዮች የእውቀትን ፍለጋ አባላት በሙሉ እንኳን ለትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ ፤ አደረሰን።

በዓሉ የሰላም ፣ የደስታ ፣ የፍቅር ፣ የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ እንመኛለን።

በዓሉን ስናከብር ፤ የተቸገሩ ወገኖቻንን አለንላችሁ በማለት ፣ የወደቁትን በማንሳት ፣ በሀዘን ላይ ያሉ ወገኖችን በማፅናናት፣ ከክፉ ድርጊት እና ሀሳብ ርቀን ሊሆን ይገባል።


የሰላም፣ የመተሳሰብና የበረከት በዓል ያድርግልን !
ፈጣሪ ሀገራችን ሰላም ያድርግልን ፤ በምድር ላይ ያሉ የሰው ልጆችን ሁሉ ይጠብቅልን።

መልካም በዓል !

@Ewiketinfilega
@Ewikeyinfilega
124 viewsEshe Man, 11:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-22 08:59:58 ለመላው ለሰው ፍጥረት በሙሉ እንኳን ለጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል አደረሰን፥ አደረሳችሁ!

*የክርስቶስ ፍቅር ሳያስለቅሰን የዶሮ የበሬ የስጋ ዋጋ ያሳስበናል።


የዘመናችን ክርስቶስ የምንሰቅልበት መሳሪያ:

በዘረኝነት: ከማይጠፋው ዘር ተፈጥረን የሚጠፋውን ዘር ፍለጋ።
በመለያየት : መክልል በቋንቋ በዘር በሀይማኖት እንዱሁም በቀለም ።
⓷ በስልጣን : ፍትህን በማጉደል እውነትን በመሸሽ ወንበርን በመተማመን ።
በሙስና:

የሰው ልጅ ሁሉ እንኳ አደረሳችሁ። ፍቅርን:ፍትህን:እውነትን:አንድነትን አምላካችን ለፍጥረት ሁሉ ይስጥልን። እንኳን የሰው ልጅ የአእዋፍ እንኳ በሰላም የሚበሩበት አለምን ይስጠን አሚን።


(1ኛ የዮሐንስ መልእክት ምዕ. 3)
----------
17፤ ነገር ግን የዚህ ዓለም ገንዘብ ያለው፥ ወንድሙም የሚያስፈልገው ሲያጣ አይቶ ያልራራለት ማንም ቢሆን፥ የእግዚአብሔር ፍቅር በእርሱ እንዴት ይኖራል?

18፤ ልጆቼ ሆይ፥ በሥራና በእውነት እንጂ በቃልና በአንደበት አንዋደድ።
@Ewiketinfilega
127 viewsEshe Man, edited  05:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-22 06:42:37 መረጋጋት መልካም ነው።

ለመሮጥ የተገባ ቀን አለ። አዎ! ለመሮጥ፣ ለመትጋት፣ ለመበርታት የተገባ ቀን አለ። አንዳንድ ቀን ደግሞ ረጋ ለማለት፣ ለማሰብ፣ ለመቀዝቀዝ የተገባ ነው።

ዛሬ በዓል ነው - የእረፍት ቀን። እስኪ ረጋ፣ ሰከን፣ ዝም በልና አስብ።

ስለኑሮህ፣ ስለጤናህ፣ ስለጓደኞችህ፣ ስለቤተሰብህ፣ ስለሥራህ፣ ስለ ሥራ ባልደረቦችህ፣ ስለደንበኞችህ፣ ስለአለቆችህ፣ ስለመምህሮችህ፣ ስለአገርህ፣ ስለመሪዎችህ፣ ስለዜናው፣ ስለዓለም፣ ስለፈጣሪህ አስብ። ስለፖለቲካው፣ ስለሃይማኖት፣ ስለኢኮኖሚው፣ ስለቴክኖሎጂ፣ ስለምታስበው፣ ስለአጀንዳህ፣ ስለአዋዋልህ አስብ። የቱ ትኩረትህን ያዘው?

ሰማዩን ተመልከተው። ፀሓዩዋን እያት፣ ዛፎቹን እያቸው። ነፋሱን አስተውል። በመንገድ የሚጓዙትን የሚተምሙትን መኪኖችና ሰዎች ልብ በል። ወፎቹን አዳምጥ። ሌሎች እንሰሳቶችንም ተመልከት። ምን ይሰማኃል?

ወዳጄ ዓለም እና የሰው ልጅ ተፈጥሮ በብዙ ስንክሳር የተሞሉ ናቸው። ባሳለፍከው ህይወት ብዙ ክስተቶች ታይተዋል። የሚያሳዝንም የሚያስደስቱም ሁኔታዎች የህይወት ገጾች ናቸው። ሁሉ ይመጣል፣ ሁሉም ይሄዳል። ያለፈውና የሚሄደውን በሰላም ሸኘው። አሁን ካለው ጋር በሰላም ተከባብረህና ተሳስበህ ኑር። ታመን፣ እመንም። የሚመጣውን በልከኛ ተስፋ ተቀበለው። ዘልዓለማዊ ክስተት የለም፣ ለውጥ እንጂ። ከሁኔታዎች በላይ መሆንን እወቅበት። መረጋጋት መልካም ነው።

ይህ ሁሉ ሲሆን፣ ነገሮች ሲለዋወጡ ህይወትን በእርጋታ ማጣጣም የቻሉ ግን ጥቂቶች ናቸው። ህይወትን ለማጣጣም ሀብት የግድ አይደለም፣ ቢኖር ግን ጥሩ ነው፣ ግን በልክ። ህይወትን ለማጣጣም ዘመድና ጓደኛ ቢኖሩ ጥሩ ነው፣ ግን በልክ። ህይወትን ለማጣጣም ጊዜ ማግኘት አስፈላጊ ነው። ጊዜህን መጠበቅና መቆጣጠርን እወቅበት።

ህይወትን ለማጣጣም ጊዜ ማግኘት ብቻውን በቂ አይደለም፣ መልካም ሃሳብም እንጂ። መልካም አስብ!

ዛሬ ለራስህ የጽሞና ጊዜ መድብ። አንድ ሰዓት በቂ ነው። ማንም የማይረብሽህ፣ ሬድዮ የማትሰማበት፣ ቴሌቪዥን የማታይበት፣ ስልክ የምትዘጋበት፣ ብቻህን የምታስብበት። ሃሳብህን የምታበራይበት፣ የምታጠራበት።

በሃሳብህ ራስህን በዘላቂ ደስታ ስለመምራት አስብ። ለራስህና ለሌሎች ስለ መኖር አስብ። የፖለቲካ መሪዎች፣ የሀብት ልዩነት፣ የሃይማኖት ልሂቃን፣ የብሔር ብሔረሰብ ልዩነት፣ የጾታ ልዩነት፣ ዝምድና፣ ጋብቻ፣ ቅጥር ባንተ ላይ ተጽዕኖ እንደማይፈጥሩ አስብ። ከማንም ከምንም ተጽዕኖ የነጻ ተፈጥሮ እንዳለህ አስብ። የሰዎች ወዳጅ መሆንህን አስብ።

ሁሉን ማድረግ እንደምትችል አስብ። ትችላለህ!

አየሩን ሳብ፣ ወድ ውስጥ ሳብ። ሳትጣደፍ ቀስ ብለህ ወደ ውጭ ተንፍስ። አተነፋፈስህን ተቆጣጠር። ውኃ ጠጣ። ሳትቸኩል ጠጣ።

መልካም ቃላትን አስብ። ወዳጅነት፣ ፍቅር፣ ሰላም፣ ተስፋ፣ እድገት፣ እረፍት፣ በጎነት፣ ነጻነትን አስብ። ሁሉ መልካም እንደሆነ አስብ። ስለሁሉ ነገር ፈጣሪህን አመስግን።

ዓለም ላንተ ምቾትና ደስታ የተሠራች ናት። ደስ ይበልህ!

በሩጫ ቀን በትጋት እንድትሮጥ፣ በእረፍት ቀን ጥሩ እረፍ።
ነገን መልካም ለማድረግ፣ ነገ ጥሩ ለመሥራት፣ ዛሬን እረፍ።

መረጋጋት መልካም ነው። እረፍት ከሃሳብ መረጋጋት ይጀምራል። ሃሳብህን አረጋጋ! እረፍ። እርፍ በል!

ዛሬ ያንተ ቀን ነው።



@Ewiketinfilega
@Ewiketinfilega
113 viewsEshe Man, 03:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-22 06:35:29 አቧራውን ማስጨስ ስታቆም መንገዱ በግልጽ ይታይሃል!


እንደ ሳይንሳዊው መረጃ ከሆነ የሰው ልጅ ከ50,000-80,000 ሃሳቦች በቀን በአይምሮዋችን ይመላለሳሉ። ከዚህ ሁሉ ሃሳቦች ውስጥ አብዛኛዎቹ በቀን በቀን የምንደጋግማቸው ተመሳሳይ ሃሳቦች ናቸው። ለዚህም ነው ህይወታችን የአስተሳሰባችን ነጸብርቅ የሚሆነው። በእውን ሆኖ የምናየው ነገር ሁሉ  በመጀመሪያ በአይምሮው ውስጥ የተቀነባበረ ነው። በራሳችን  ህይወት ላይም ሆነ በመላው አለም ላይ የተከወኑ ነገሮች ሁሉ መጀመሪያ ሃሳቦች ነበሩ።

ከ50,000 በላይ ሃሳቦች አይምሮዋችንን ውስጥ ይመላለሳሉ ካልን፤ ምን ያህሉ ይሆን የሚጠቅሙን? እራሳችንን የመቀየር ሀሳብ ካለን ቅድሚያ አስተሳሰባችን ምን እንደሚመስል መቃኘት አለብን። ረጋ ብለን ለደቂቃ በጥሞና ውስጣችንን ብንሰማ፤ እጅግ እንገረማለን። ሃሳባችን አንዴ ከትላንት፤ አንዴ ከዛሬ አንዴ ከነገ፤ ሳያቋርጥ ይጋልባል። ልክ ያለማቋረጥ እንደሚማሰል ኩሬ መንፈሳችንን  ያደፈርሰዋል ። ለዚህ ነው የምንፈልገውን ነገር ማግኘቱ የሚከብደን፤ የምንመኘውን ኑሮ መኖር ያቃተን፤ መረጋጋት የተሳነን፤ አይምሮዋችን አለማቋረጥ የማይጠቅሙንን  ሃሳቦችን ስለሚያመነጭ ነው።

ላዎ ትዙ “ለተረጋጋ አይምሮ አለም ትገዛለታለች” ያለው፤ አይምሮዋችን እረጋ ሲል እና በዛሬ ላይ ትኩረታችንን ስናደርግ፤ ነገሮች ያለብዙ ልፋት እና ጭንቀት እውን ይሆኑልናል ማለቱ ነው። ጭንቀት እና መረበሽ መንስኤአቸው ዛሬ ላይ አለመኖር ነው። ትላንትን የሚያስብ ሰው እንዴት ዛሬን ማለፍ ይችላል? በአይምሮዋችን የምንሸከመው የትላንት ቅራቅንቦ እንዴት ዛሬን በረጋ መንፈስ ያሳየን? ያለጊዜው ስለነገ ስናስብ እና ስንጨነቅ፤ ዛሬን በደመነፍ እየኖርን ነው።

በሀሳብ የሚተራመስን አይምሮ ይዞ መኖር፤ በበረሃ ውስጥ ከነፋስ ጋር እንደመጓዝ ነው። ነፋሱ አሸዋውን እያንቦለቦለው መንገዳችንን ጥርት ባለ መልኩ እንዳንመለከተው ያደርገናል። ችግሮቻችን በህሊናችንን ውስጥ ከመጠን በላይ ሲመላለሱ፤ መፍትሄውን እንዳንመለከት አቧራውን እያስጨሱብን ነው። ታዲያ መፍትሄው ምንድን ነው? የሚከተሉት አራት ነጥቦች እረፍት ያጣን አይምሮ ለማረጋጋት ይረዳሉ

ኛ ከሁሉም በፊት የሚቀድመው ማስተዋል ነው። አይምሮዋችንን እንደታዛቢ መመልከት መጀመር አለብን። አሁን የማስበው ምንድን ነው? እያልን እራሳችንን መጠየቅ ስንጀምር፤ ሃሳባችን ያለቦታው ሲረግጥ እንይዘዋለን፤ ይህ  ደግሞ ሃሳባችንን መቆጣጠር እና መስመር ማስያዝ እንድንችል ያደርገናል።

ኛ ለራሳችን ግልጽ መሆን መጀመር መቻል- እንደ ግልጽነት ህይወትን የሚያቀል ምንም ነገር የለም። ግልጽነት ሲባል ለሌሎች ሰዎች እውነትን መናገር ብቻም ሳይሆን እራስንም ጭምር ማወቅ ነው። ለራሳችን ግልጽ መሆን ስንችል የምናስባቸው ሀሳቦችን በጠራ መልኩ ማየት እንችላለን።

ኛ ነገሮችን ጨርሰን እንጀምር-በአብዛኛው ጊዜ አይምሮዋችን ትርምስምስ የሚለው፤ የምንፈልጋቸውን ነገሮች አስቀድመን እንዴት ማድረግ እንዳለብን ሳናውቅ ስንጀምራቸው ነው። ልክ የቤቱን ካርታ ሳይዝ ቤት መስራት እንደሚጀምር ነው።የምንሰራውን ቤት ሳናውቅ፤ ሲሚንቶ እና አሸዋችንን ብናላውስ ትርፉ ድካምና መረበሽ ይሆንብናል። በመኝታ ክፍሉ ቦታ ሳሎኑ፤ በሳሎኑ ፈንታ ሽንት ቤቱን እየጠፈጠፍን ለኛ የማይመች ቤት የምንገነባው በመጀመሪያ የቤታችን ካርታ ተነድፎ ስላለቀ ነው። ስለዚህ አስቀድምን የምንሄድበትን ማወቅ ከቻልን፤ እራሳችንን ከብዙ ጭንቀት ልናድነው እንችላለን።

ኛ በመጨረሻ በጭንቀት የምንለውጠው ነገር እንድሌለ እንወቅ፤ ለውጥ በጠንካራ ሃሳብ እና በተግባር እንጂ በጭንቀት እውን ሆኖ አያውቅም።

ሃሳባችንን እናቅልል፤ ዛሬን ለዛሬ፤ ነገን ለነገ እናውለው። አይምሮዋችን  ሲረጋጋ እና የሃሳብ ኩሬያችንን ማማሰሉን ስናቆም፤ ጭቃው ወደታች መዝቀጡ አይቀርም። መንፈሳችን እረጋ ሲል ችግሮቻችን ለብቻ ወደታች ይዘቅጣሉ፤ መፍትሄዎቻችን ደግሞ ከላይ ይንሳፈፋሉ። ያኔ ሁሉም ነገር ግልጽ ይሆንልናል።ያለማቋረጥ የምናሰብ እና የምንጨነቅ ከሆነ ግን ችግሮቻችንን እና መፍትሄዎቻችንን እያማሰልናቸው ነው። የተረጋጋ  አይምሮ ላለው ሰው አለም ትገበርለታለች የተባለውም ለዚህ ነው።

አይምሮዋችንን ካልተቆጣጠርነው ፤ እንዳሻው መጋለቡ አይቀርም። ከትላንት ዛሬ፤ ከዛሬ ነገ እየጋለበ መሄጃ እንዳያሳጣን እንጠንቀቅ። ትኩረታችንን ዛሬ ላይ አናድርግ፤ ሃሳቦታችት  ሁሉ እናጢናቸው፤ የሚጠቅሙንን አናሳድጋቸው፤ የማይጠቅሙንን በጊዜ እናሰናብታቸው። 

በህሊናችን በር ላይ ዘብ መቆምንም መማር አለብን። ድፎ ዳቦ መድፋት የሚፈልግ ሰው፤ ወደ ማቡኪያው የዳቦ ዱቄት እንጂ ሽሮ አይከትም። የእኛም ኑሮ እንደዛው ነው፤ የምፈልገውን ውጤት ለማግኘት፤ ውጤቱን ሊሰጡን የሚችሉ አስተሳሰብ እና እውቀቶችን ወደ አይምሮዋችን እንከታለን እንጂ፤ ምኑንም ምኑንም ማግበስበስ የለብንም።



@Ewiketinfilega
@Ewiketinfilega
99 viewsEshe Man, 03:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ