2022-04-19 05:45:14
የመኖርን ጥበብ በእጅጉ የሚሻ አንድ ሰው ወደ አንድ ታላቅ ጠቢብ ዘንድ ይሄዳል። ግራ መጋባት የሚታይበት ይህ ሰው ጠቢቡ ጋር እንደ ደረሰ የጥያቄ መዕት ያወርድበታል። ጠቢቡም ሰው ሁሉንም ጥያቄ በጥሞና ከሰማ ቡአላ " የመኖርን ጥበብ አውቅ ዘንድ ካንተ ዘንድ መጣው። ቢቻልህስ ንገረኝ።" አለው።
ጠቢቡም ሰው እንዲ ሲል መለሰለት። "በ አንድ ወቅት ሰው ሁሉ የሚገረምበት አንድ ትልቅ ከመስታወት የተሰራ ትልቅ ቤት ነበር። ሁሉም ጥበብን የሚሻ የሚሄድበትና ጥበብን የሚማርበት። እናልህ ሁለት ሰዎች ይሄን ሰምተው ወደዛ ቤት ይሄዳሉ። ሁለቱም እጅግ የተለያዩ ናቸው። አንዱ ደስተኛ ተጫዋች ቅለል ያለ ህይወት የሚመራ ሲሆን ሁለተኛው በአንፃሩ ንዴታምና ብስጩ፥ ህይወትንም መክበድ የሌለባትን ያህል አክብዶ የሚያይ ነበር።
ወደ መስታወት ቤት ሲደርሱ ደስተኛው ሰው ቀድሞ ገባ። ወደ ቤቱም ሲገባ በጣም ተማረከበት። ፊታቸው እጅግ የበራ፥ ህይወትን በእጅጉ የሚያጣጥሙ አይላፍ ህዝብ ተመለከተ። ከበፊቱም በላይ እጅግ ተደስቶም ከመስታዎት ቤቱ ወጣ። ውጪ ቆሞ ላለው ለሌለኛው ሰውም ያየውን ነገረው።
እጅግ ብስጪ ንዴታሙ ሰውም ወደ መስታዎት ቤቱ ገባ። ያጋጠመውም ነገር ከበፊቱ እጅግ የተለየ ነበር። አእላፍ ደስታ የራቃቸውንም ሰዎች ተመለከተ። ቤቱን ከመውደድ ይልቅ ጥላቻ ሞላበት። እጅግ በተበሳጨ ቁጥር ቤቱ ውስጥ ያሉትም አእላፍ ሰዎች ብስጭታቸው ይጨምር ነበር። እሱ የሚያደርገው እያንዳንዱን ነገር እነርሱ በእጥፍ ይመልሱለት ነበር።" አለ ጠቢቡ ሰው።
ቀጥሎም "አየህ ሁለቱ ሰዎች ያዩት ነገር ሌላ ነገር ሳይሆን የራሳቸውን ምስል ነው። መስታወቱ የራሳቸውን ምስል መልሶ እያሳያቸው ነበር። እዚም ምድር ላይ የተለየ የመኖር ጥበብ የለም። አንተ የሆንከውን አከባቢህ ይሆንልሀል። ደስታን ከሰጠኸው እጥፍ አርጎ ይመልስልሃል። ፍቅር ከሰጠኸው አትርፍርፎ ላንተም ይሰጥሀል። ጥበቃ ካረክለት እርሱም መልሶ ይንከባከብሃል። ደግ ስትሆንለት ደግነት ታገኛለህ።
ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ እንደሚባለው ሰው በ አሉታዊ ሀሳብ ተብትቦ ደግ ነገርን ከሰው ይጠብቃል። እየገደለ መኖርን ይፈልጋል። እያደማ መዳንን ይሽል። እየሱስ ይሄን ባንድ አርፍተ ነገር " የዘራኸውን ታጭዳለህ። " በማለት ገልፆታል። "ሊደረግልህ የምትፈልገውን አንተ ለሰው አድርግ ይላል።" ደግሞም እንዲህ ይባላል " አለም ላይ ማየት የምትፈልገውን ነገር አንተ ደግሞ እርሱን አርግ።"
አዎ ሰው ነገሮችን ሁለት ጎን እንዳላቸው ሳያቅ ይኖርና በመጨረሻም ይጎዳል። አሸናፊነትን እንጂ በሌላ ጎን ያለውን ሽንፈትን አይረዳውም። ህይወትና ሞት ፥ ደስታና ሀዘን ፤ መግደልና መሞት ፥ መውደድና ጥላቻ...... ወዘት የአንድ ነገር ሁለት ጎኖች ናቸው። አንዱን ብቻ ስንረዳ የእውነትን ግማሽ ተረዳን ማለት ነው። ሁለቱንም ስንረዳ ግን ሁሉም ይገባናል። ሀዘንን ለመሸሽ በሌሎች ሀዘንን አናመጣም። መውደድን ለማቆየት ሌሎችን አንጠላም።
ነገር ግን ተቃራኒ የሌለው አንድ ነገር አለ። እርሱም በ ፈጣሪ ተመስሏል። ይህ ተቃራኒ የሌለው አቻም ያልተገኘለት ነገር ፍቅር ነው። ፍቅር ጊዜን ጠብቆ የማይከዳ የተፈጥሮ ሀብት ነው። ገፅ በረከት ስጣታም ነው። ፍቅር ስንሰጥ ሁሉንም በሁሉ ውስጥ እናገኛለን።
ለዚህ የመኖር ጥበብ በጥቅሉ ያለ ቅድመ ሁኔታ ማፍቀር ነው። የሰው ልጅ ደጋግሞ ከመስማቱ ያልተገበረው ነገር ግን የሰለቸው ቃል። ሰው ተቃራኒ ያለውን ፍቅር ይዞ ይጎዳል። ፍቅር ይበለው እንጂ ይሄ በፍቅር ስም የሚነግድ ሌላ አይነት ስሜት ነው። ግዜን ጠብቆ ወደ ጥላቻ የሚሄድ ፍቅር ፍፁም ፍቅር አይባልም ። ፍፁሙን ፍቅር እሻ"!!!
@Ewiketinfilega
@Ewiketinfilega
280 viewsEshe Man, 02:45