Get Mystery Box with random crypto!

የምንፈልገውን ለማግኘት ብቻ ከመማሰን ያገኘነውን በመውደድና በማመስገን ቀናችንን እናስውብ ፡፡ | እውቀትን ፍለጋ

የምንፈልገውን ለማግኘት ብቻ ከመማሰን ያገኘነውን በመውደድና በማመስገን ቀናችንን እናስውብ ፡፡

ከመጸለይህ በፊት ተመስገን በል። ስለሁሉም ነገር አመስግን...በረከቶችህን ቁጠር! ጠዋት ገና ከእንቅልፍህ ስትነቃ....አይኖችህን ስትገልጥ.....አየሩን ስትተነፍስ <<ተመስገን>> በል!!!...ሞተህ ልታድር ትችል ነበርና!!! ደግሞ ከአልጋህ ወርደህ መሬት ስትቆም……‹‹ተመስገን>> በል! በሆነ ምክንያት የአልጋ ቁራኛ ሆነህ ልትቀር ትችል ነበርና!!! ውለህ ስትገባ ተመስገን በል፣ ብዙዎች እንደወጡ የቀሩ አሉና።

በየትኛውም መንገድህ ላይ አመስግን። ምስጋና ቢስ አንደበቶች ልመናን ሲያሻግሩ ለዛቸውን ያጣሉ!

( ደራሲ ስብአት ገ/ እግዚአብሔር)

ውብ ዛሬ!!!

@Ewiketinfilega
@Ewiketinfilega