Get Mystery Box with random crypto!

ኩርፊያ፣ ቂም፣ ጥላቻና ብቀላ ጊዜ ገዳይና የስኬታማ ህይወት ጠላት ናቸው። ልዩነት ተፈጥሯዊ ነው። | እውቀትን ፍለጋ

ኩርፊያ፣ ቂም፣ ጥላቻና ብቀላ ጊዜ ገዳይና የስኬታማ ህይወት ጠላት ናቸው። ልዩነት ተፈጥሯዊ ነው። ልዩነት ሁሌም ይኖራል። በልዩነት አትበሳጭ። ከልዩነት ጋር መኖርን እወቅበት።

ዓለም የምትሽከረከረው፣ የምትሾረው፣ ወደፊት የምትራመደው በልዩነት ነው። ልዩነት የእድገት ምንጭ ነው። አላዋቂዎች ግን ልዩነትን የኩርፊያ ምንጭ ያደርጉታል። ያ ትልቅ ስህተት ነው!

ልዩነትን የምትፈታው በንግግር እንጂ በኩርፊያ አይደለም። ነገርን በልብ ይዞ ማመንዥክ ለራስም ለሌላውም አይጠቅምም። ኩርፊያ ጊዜን፣ ጤናን ሀብትን ይበላል። ኩርፊያ የቂም እናትና አባት ነው።

አመለካከትህ ቅንና በጎነትን የተላበሰ ይሁን። ካንተ የተለየ አመለካከት ያለው ሰው ሁሉ የተሳሳተ ነው ብለህ አትደምድም። በልዩነትም ይሁን በስምምነት ውስጥ ሁሌም የሌላውን ፍላጎት ለመረዳት ሞክር።

በተቻለህ ዓቅም የሌላውን ሰው ስሜት ላለማስቀየም ሞክር። እውነት ስለሆነ ብቻ ሌላውን የሚያስቀይም ንግግር አትናገር። በስሜት አትነዳ፣ ስሜትህን ተቆጣጠር።

ልዩነት ሁሉ በአንድ ጊዜ ካልተፈታ አትበል። ለጊዜ እድል ስጠው።
ልዩነትን በውይይት ፍታና ህይወትን ፍክት ብለህ ኑር!አለዚያም ከልዩነት ጋር በሰላም መኖርን ተለማመጂ!
ለማን ጀቴ/ብለህ ታኮርፋለህ/ታኮርፊያለሽ?
ፈታ በል ወዳጄ!
Toughe g.kebede
@Ewiketinfilega
@Ewiketinfilega