Get Mystery Box with random crypto!

የአዕምሮ ሠላም የህይወታችን ዋስትና እንዲሁም የደስታችን እርሾ ነው፡፡ ሠው በአዕምሮው ሠላም ከተሠ | እውቀትን ፍለጋ

የአዕምሮ ሠላም የህይወታችን ዋስትና እንዲሁም የደስታችን እርሾ ነው፡፡ ሠው በአዕምሮው ሠላም ከተሠማው ሕይወቱ ፍስሃ የተሞላበት ይሆናል፡፡ ገንዘብ እና ሌሎችም ትርፍ ነገሮች ከአዕምሮ ጤና መሆን በኋላ ሊመጡ የሚችሉ ተቀፅላዎች ናቸው፡፡ ከሁሉ አስቀድሞ አዕምሯችንን ልንንከባከበው ግድ ይለናል፡፡እንኳን ከሌሎች ሠዎች ቀርቶ ከራሳችን ጋር ተስማምተን ለመኖር የአእምሮ ሠላም እና ጤና መሆን በሕይወታችን ላይ ሁሌ አሸናፊ ሆነን መኖር እንድንችል ጉልህ ድርሻ አለው፡፡

ሠዎች ለአዕምሯቸው ሠላምን የሚመግቡት ከሆነ ደስ የማይልና የማይወደድ ትልቅ ነገር በሕይወታቸው ቢያጋጥማቸው እንኳን ከችግሩ መወጣጫ መንገዱን አያጡትም፡፡ እንዴት ነው የአእምሮ ሠላምን ልናገኝ የምንችለው ብለን ስንጠይቅ፤ እንደ እኔ ሃሳብ የዓለምን ተፈጥሮ በደንብ የተረዳ ሠው በዓለም ሳለ ለሚገጥሙት ፈተናዎች መልካም ምላሽ ይኖረዋል እላለሁ፡፡ ሠው ለራሱ ቅን ከሆነ ለሌሎችም ቅን ይሆናል፡፡

ሠው በመሆናችን ብቻ ደስታና ሃዘን፣ ማጣትና ማግኘት፣ መውደቅና መነሣት፣ ማመንና መከዳት እንዲሁም ውጣ-ውረድ የተሞላበት መሠናክል ይፈራረቁብናል፡፡ ዋናው ነገር በነዚህ ነገሮች ተፈትኖና ነጥሮ መውጣት ከሁላችንም ይጠበቃል፡፡ፈጣሪ ይህንን ድንቅ አዕምሮ ወይም ልዩ መክሊት ሲሠጠን በመጣው ወጀብ እንድንወሠድ ሳይሆን በጥበብና በዕውቀት ችግሮችን ፈትተን፣ ትምህርት ወስደን፣ እንደወርቅ በእሳት ተፈትነን በማስተዋል ነጥረን እንድንወጣ ነው፡፡

አስደሳች ፍጻሜ አጠብቅ ፣ህይወት ሁሌም ሁለትዮሽ ናት፣ መኖርን ምሉዕ የምናደርገው ሁለት ተቃራኒዎችን በሚዛን በመከወን ነው፡፡ እንባም ሳቅም፣ ደስታም ኀዘንም ፣ መስጠትም መቀበልም ፡፡ መሙላትም መጉደልም። ሲጠቃለል ፣ ሕይወት ኅብረ ቀለሟ ያማረ ቀስተ ደመና ነች።

At the end of your life, all the things you accumulated and achieved won't make you happy, it is who you have become as a person that really makes you happy.

Don't wait for a happy ending, you don't have forever to live. Let your happy ending starts today. Be happy all along, from now till you draw your final breath.

ውብ ምሽት
@Ewiketinfilega
@Ewiketinfilega